Judkins Park Station Access Project

Judkins Park Station መዳረሻ ፕሮጀክት

አጠቃላይ እይታ

የJudkins መናፈሻ ቀላል ባቡር ጣቢያ በ2025 ሊከፈት ተወጥኗል። ለዚህ ዝግጅት፣ በ2019 ውስጥ ህብረተሰቡን እንዴት አካባቢውን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተደራሽነት ያለው ማድረግ እንደሚቻል ጠይቀን ነበር። ስለዚህ የጁድኪንስ መናፈሻ ጣቢያ መዳረሻ ጥናት (Judkins Park Station Access Study) አደረግን። ከሱም ብዙ ነገር ተምረናል። ለምሳሌ፣ ከMountains to Sound Trail ውስጥ ለውስጥ መሄጃ መንገድ በእግር ለሚሄዱ፣ ለሚሮጡ፣ ለሚያንከባልሉ ወይም በብስክሌት ለሚጋልቡ ሰዎች ደህንነት ለመጠበቅ ተጨማሪ ብርሃን ያስፈልገዋል። አሁን ለውጦቻችን ሁሉም ማህበረሰቡ የሚፈልገውን የሚያንፀባርቁ እና የአዲሱን የቀላል ባቡር ጣቢያ ሥራ የሚያሟላ መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን። እና ከ ሳውንድ ትራንዚት ሲስተም ተደራሽነት ፈንድ ፕሮግራም (Sound Transit System Access Fund Program) ባገኘነው ገንዘብ፣ እነዚህን ፕሮጀክቶች መገንባት እንችላለን:

  • ለእግር ጉዞ ቦታዎች የአሜሪካን አካል ጉዳተኝነት ሕግ (ADA) የሚያሟላ ማሻሻያዎች ይደረጋሉ
  • በHiawatha Pl S ላይ አዲስ የደረጃ መውጫ
  • ለMountains to Sound Trail የውስጥ ለውስጥ መንገድ ማብራት

የማህበረሰብ ማዳረስ

ስለፕሮጀክቱ ዝመናዎችን ከፈለጉ ይህንን ድህረ ገጽ ይጎብኙ። እንደ የግንባታ ማሳሰቢያዎች ያሉ ነገሮችን ማየት እንዲችሉ የእኛን የማዳረሻ መረጃዎችን/ ቁሳቁሶችን በዚህ ክፍል ውስጥ እናካትታለን።


የፕሮጀክት ካርታ

Judkins መናፈሻ አዲስ የውስጥ ለውስጥ መሄጃ መብራት እና የሃይዋታ ደረጃ (Hiawatha Stairway) ግንኙነት

በJudkins መናፈሻ አካባቢ ውስጥ የሚጥመለመል የMountains to Sound Trail ካርታ

የካርታ መፍቻ/ መግለጫ

በውስጥ ለውስጥ መሄጃ ጥግ ጥጉን አሁን ያሉ ነባር መብራቶች

አዲስ የውስጥ ለውስጥ መሄጃ መብራት

Judkins መናፈሻ ጣቢያ መግቢያ

የHiawatha ደረጃዎች መገናኛ


መርሐ ግብር

  • እቅድ ማውጣት
    • ከበልግ 2019 - ጸደይ 2021
  • ንድፍ
    • ከጸደይ 2021 - በልግ 2022
  • ግንባታ (በአየር ሁኔታ ላይ ተመስርቶ የጊዜ ሰሌዳ ሊለወጥ የሚችል)
    • ክረምት 2023 - በልግ 2023
  • የJudkins መናፈሻ ጣቢያ መከፈት
    • 2025

የገንዘብ ድጋፍ

  • የሳውንድ ትራንዚት ሲስተም መዳረሻ የገንዘብ ድጋፍ ስጦታ
  • ሲያትልን ለማንቀሳቀስ ቀረጥ

Transportation

Greg Spotts, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.