አሁን ይሳፈሩ
አማርኛ • 简体中文 • 繁体字 • 日本語 • 한국어 • Oromiffa • af-Soomaali • Español • Tagalog • ትግርኛ • Tiếng việt • English
ስለ አሁን ይሳፈሩ (Ride Now)
አሁን ይሳፈሩ (Ride Now) በፀደይ 2022 ለአረጋውያን እና ለአካል ጉዳተኞች እና በነርሱ የተነደፈ የሚሰራ የሙከራ ፕሮግራም ነበር። ዕድሜያቸው 65+ የሆኑ አቅመ-አዳሞች/ሄዋኖች፣ አካል ጉዳተኞች፣ እና ለነርሱ ተንከባካቢዎቻቸው ወይም አገልግሎት ሰጪዎቻቸው በየሎ ካብ፣ በኡበር እና በሊፍት ላይ ለመጠቀም ነፃ የጉዞ ቫውቸሮችን ሊጠይቁ ይችላሉ። ምንም እንኳ አሁን ይሳፈሩ (Ride Now) አሁን ባይገኝም፣ ከሙከራው ብዙ ተምረናል እና ለወደፊት ፕሮግራሞች የተማርናቸውን ትምህርቶች ተግባራዊ እያደረግን ነው። ለበለጠ መረጃ፣ የእኛን ማጠቃለያ የመረጃ ቁሶችን ከዚህ በታች ይመልከቱ።
ሰነዶች እና ግብአቶች
የአሁን ይሳፈሩ (Ride Now) የመረጃ ቁሶች
አካታች የእቅድ መሣሪያ ስብስብ
የመሳፈር አሁን (Ride Now) የሙከራ መርሃ ግብር ተግባራዊ እንዲሆን የረዳው የሕዝብ ማመላለሻ እቅድ ለሁሉ (Transit Planning 4 All) የገንዘብ ድጋፍ፡ የአካል ጉዳተኞችን እና አዛውንቶችን ማመላለሻ እቅድ ውስጥ የተካቱትን ምርጥ ብሔራዊ የትራንስፖርት እቅድ ፕሮጀክት ተሞክሮዎችን የሚዳስስ እና የሚያስተዋውቅ ነው።
እንደ 2018-2019 የሕዝብ ማመላለሻ እቅድ ለሁሉ (Transit Planning 4 All) የስጦታ ስብስብ፣ ሆፕሊንክ (Hopelink) (ኪንግ ካውንቲ፣ ዋሽንግተን WA) አካታች የእቅድ መሣሪያ፣ ከሆፕሊንክ (Hopelink) የተማሩትን ማጠናቀር እና ከኪንግ ካውንቲ ተንቀሳቃሽነት ጥምረት ተሳታፊነት የተገኘው የገንዘብ ድጋፍን ፈጠረ። የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) ይህንን የሙከራ መርሃ ግብር በማቀድ ውስጥ አካታች የእቅድ መሣሪያ (Inclusive Planning Toolkit)ን በሰፊው ተጠቅሟል።
የሆፕሊንክ (Hopelink) አካታች የእቅድ መሣሪያ (Inclusive Planning Toolkit)ን እዚህ ማሰስ ይችላሉ።