እንኳን ወደ የመጓጓዣ ፍትኀዊ እኩልነት የስራ ቡድን (TEW) በደህና መጡ!

አማርኛ繁体字简体中文ភាសាខ្មែរ한국어Oromiffaaf-SoomaaliEspañolTagalogትግርኛTiếng việtEnglish

ስለ እኛ

የእኛ ስራ እያንዳንዱ ሰው ሁሉም ደህንነቱ የተጠበቀ እና በተመጣጣኝ ዋጋ የመጓጓዣ አገልግሎት እንዲያገኝ ማረጋገጥ ነው። እኛ በተለይ ከዚህ ቀደም በቂ ድጋፍ ያላገኙ ማህበረሰቦችን በመርዳት ላይ እናተኩራለን።

የመጓጓዣ ፍትሐዊ እኩልነት የሥራ ቡድን (TEW) በፖሊሲ ላይ ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)ን የሚያማክር ገለልተኛ አካል ነው፤ የሱ አባላት የከተማ ሰራተኞች አይደሉም። ሚዲያን/ ዜና ማሰራጫ ጨምሮ፣ ስለ TEW ጥያቄዎች፣ እባክዎን transportationequity@seattle.gov ኢሜይል ያድርጉ

የትርጉም አገልግሎቶች

ማመልከቻዎችን ወይም የድጋፍ ደብዳቤዎችን ለመሙላት እና ለማስገባት የቋንቋ ተደራሽነት አገልግሎት የሚፈልጉ ግለሰቦች፣ የጥምረት ተቋሞች እና ማህበረሰብ መሠረት ያደረጉ ድርጅቶች ወደ transportationequity@seattle.gov ኢሜይል ማድረግ ወይም በ (206) 530-3260 መደወል ይችላሉ።

ማን ማመልከት ይችላል?

ልምድ ካልዎት እና በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ካለው ቡድን ጋር ተዛምዶ ኖሮአቸው የሚከተሉትን የሚያግዙ ክሆነ ማመልከት ይችላሉ:

  • የጥቁር፣ የአገር ተወላጆች እና የቀለም ህዝቦች (BIPOC) ማህበረሰቦች
  • ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ማህበረሰቦች
  • አዲስ ሰፋሪዎች እና ስደተኞች
  • አካል ጉዳተኝነት ያላቸው ሰዎች
  • LGBTQIA+ ሰዎች
  • በመኖሪያ ቤት አጥነት ደህንነት የጐደላቸው ሰዎች
  • በሴትነት እና የሴት-ጾታ የሚለዩ ሰዎች
  • ወጣቶች እና በዕድሜ ገፍተው ያሉ ሰዎች
  • ቀደም ሲል በእስር ላይ የነበሩ ሰዎች
  • ከፍተኛ መፈናቀል የሚያጋጥማቸው ሰፈሮች

ልዩ የመዳረሻ ፍላጎቶች ካሉኝ ምን አይነት እርዳታ ማግኘት እችላለሁ?

የእኛን ቡድኖች ፍላጎቶች ለማስተናገድ ሁሉንም ጥረት እናደርጋለን። የኛ ሰራተኞች ለእርስዎ የተለየ ፍላጎቶች መፍትሄዎችን ለማግኘት ከእርስዎ ጋር አብረው ይሰራሉ። 

ክፍያ ይከፈለኝ ይሆን?

አዎ! በመጀመሪያዎቹ ሶስት የአቅጣጫ ማስያዣ ወራት በሰዓት $50 ዶላር ያገኛሉ። እርስዎ አንዴ የአቅጣጫ ማስያዣ ሂደቱን ካጠናቀቁ፣ በሰአት $75 ዶላር ያገኛሉ እና በዓመት እስከ $7,500 ዶላር ሊያገኙ ይችላሉ። 

ምን አደርጋለሁ?

እርስዎ ለሦስት ዓመታት እንዲያገለግሉ ይጠበቃል፣ እና ከመጀመሪያው የእርስዎ የሥራ ክፍለ ዘመን በኋላ ለሁለት ተጨማሪ ዓመታት ማራዘም ይችላሉ። ከ2-4 ስብሰባዎች ላይ ይገኛሉ (በአብዛኛው በዙም (Zoom) ላይ) እና በየወሩ ከ9-10 ሰአታት አካባቢ ይሰራሉ። በእነዚህ ስብሰባዎች ወቅት ከሌሎች የቡድን አባላት እና የከተማው ሰራተኞች ጋር አብረው ይሰራሉ። 

የምርጫው ሂደት ምንድን ነው?

በምልመላ ሂደት ወቅት የTEW አባላት እና የሲያትል መጓጓዣ መምሪያ (SDOT) ሰራተኞች የቀረቡትን ማመልከቻዎች እና የድጋፍ ደብዳቤዎችን ይገመግማሉ። ከዚያ በኋላ ይህ ቡድን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ እጩዎችን ይመርጣል። ከቃለ መጠይቁ በኋላ፣ ቡድኑ የመጨረሻውን ውሳኔ ያደርግ እና ውጤቱን እጩዎችን ያሳውቃል።

የመጓጓዣ ፍትኀዊ እኩልነት ማዕቀፍ (TEF) ምንድን ነው?

TEF የበለጠ ፍትሃዊ እኩልነት የመጓጓዣ ስርዓት እንዲኖር ለማረጋገጥ ከማህበረሰብ አባላት ጋር ያደረግነው እቅድ ነው። አሁን እኛ ይህንን እቅድ ወደ ተግባር ለመቀየር እየሰራን ነው።


ለበለጠ ዝርዝር መረጃ ወይም ጥያቄዎችን ለመጠየቅ፣ በ transportationequity@seattle.gov ለኛ ኢሜይል ለመላክ ነፃነት ይሰማዎ።  ከእርስዎ ለመስማት በጉጉት እንጠብቃለን!

በአሁን ጊዜ የስራ ቡድን አባላት

ላኬሻ ጆንስ (Lakeisha Jones) (የሥራ ቡድን ተባባሪ ሊቀመንበር)፣ የሞኒካ መንደር ቦታ አንድ (Monica’s Village Place One) 

ኬሻ የሞኒካ መንደር ቦታ አንድን እየወከለች ነው። እነርሱ ብዙ የተለያዩ ስነ-ሕዝቦችን እና በድጎማ የተደገፈ ተንሸራታች ልኬት የሚያቀርቡ ውስብስብ የአፓርታማ ሕንፃዎችን ያገለግላሉ እና ጉዳዮችን ያስተዳድራሉ። ኬሻ በሲያትል መሃል ከተማ በሚገኘው ለትርፍ ያልተቋቋመ ቅድመ ትምህርት ቤት አካታችነት ያለው አስተማሪ ናት። የእርሷ ማዕከል የተለመደ ታዳጊ ህጻናትን ጨምሮ፣ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን፣ አካል ጉዳተኝነት፣ እና የሕመም ምርመራ ችግሮች ያላቸውን የሚያገለግል አካታች ማዕከል ነው። ኪይሻ የመጀመሪያ ዲግሪዋን በልጅ እና የቤተሰብ ጥናቶች ያጠናቀቀች እና በተተገበረ የባህሪ ትንተና ጥናት የማስተርስ ዲግሪዋን ማግኘት ትፈልጋለች። እሷ በፍትሀዊ እኩልነት መጨመር የሚደነቁ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር ለመስራት ወደፊት በጉጉት እየጠበቀች ነው! የዚህ ቡድን አባል መሆኗ ለእሷ ማህበረሰብ የበለጠ ፍትሃዊ እኩልነት ግብዓቶችን የማደራጀት ልምድ እንድታገኝ እድል ይሰጣታል። ኪይሻ በማህበረሰብ ክስተቶች እና ከሁሉም የሕይወት ዘርፎች ከመጡ ሰዎች መማር ያስደስታል። ሥራ እየሰራች በሌለችበት ወቅት፣ ኪይሻ በተለያዩ ከመደበኛ ሥራዋ ውጭ እንቅስቃሴዎች እራሷን እያሳተፈች ነው። እሷም እንዲሁም እጅግ ደስታን የሚሰጣት፣ ደግሞ በትምህርትዋ የላቀች በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የምትገኝ ልጅ እናት ናት።

ጄሲካ ሳልቫዶር (Jessica Salvador)፣ የጋራ ሜትር ካሬ

ዶ/ር ጄሲካ ሳልቫዶር ከማህበረሰቦች ጋር ስለ መተባበር፣ ትርጉም ያላቸው ግንኙነቶችን ስለ መገንባት እና መማርን እና እድገትን ለማጎልበት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። እንደ የአዲስ ሰፋሪ ቤተሰቦች ልጅ እና እንደ አንደኛ ትውልድ የኮሌጅ ምሩቅ፣ ጄሲካ ከተለያዩ የዕውቀት/ የትምህርት፣ የንግድ እና የበጎ አድራጎት ዳራዎች ጋር በጥልቀት ለማህበራዊ ፍትህ እና ነፃነት ቁርጠኝነት ያላቸውን በማወቅ፣ የህይወት ተሞክሮዎችን ኖራለች። ጄሲካ ከካሊፎርኒያ፣ በርክሌይ (Berkeley) ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ምህንድስና BS፣ ከላ ቨርን (La Verne) ዩኒቨርሲቲ ማስተርስ በትምህርት፣ እና በትምህርት አመራር እና የፖሊሲ ጥናቶች ከዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ፣ የፍልስፍና ዶክተር ድግሪ (Ph.D.) አግኝታለች። የእነርሱ ስራ ለፍትሃዊ እኩልነት ስርዓቶች ክፍተቶችን በመፍጠር እምነት እና በታሪክ ተገለው የነበሩ ድምጾች የሚመራ፣ በነፃ አውጪነት መነጽር በኩል ድርጅታዊ ውጤታማነትን በማሳደግ ላይ ስር ያፈራ/ የተመሰረተ ነው።

ዶ/ር ሳልቫዶር በአሁኑ ጊዜ የኪትሳፕ የአዲስ ሰፋሪዎች ድጋፍ ማዕከል (Kitsap Immigrant Assistance Center) ዋና ዳይሬክተር ሆነው ያገለግላሉ። እንዲሁም እነርሱ በሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT) ላይ ያለው የመጓጓዣ ፍትሃዊ እኩልነት የስራ ቡድን (TEW) የጋራ ሜትር ካሬ ተወካይ ናቸው። የኢኮኖሚ መዋዕለ ንዋይ ሽረት፣ የተፈጥሮ አካባቢ ኢፍትሃዊ እኩልነት፣ እና ከመሬቱ ጋር ያለው ግንኙነት መቋረጥ ጋር የረዥም ጊዜ ተፅእኖዎችን ለመፍታት የጋራ ሜትር ካሬ እንዳለ የነበረ ጥበቃ እና የመልሶ ማቋቋም ጥረቶች የጥቁሮች አዲስ ሰፋሪዎች እና የቀለም ሰዎች (BIPOC) የመሬት ሰራተኞች ድምጾችን፣ አመራር፣ እና እውቀት ያማክላል።

አኪራ ኦሂሶ (Akira Ohiso)፣ ባላርድ (Ballard) ሰሜን ምዕራብ የአረጋውያን ማእከል 

አኪራ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ጋር ማህበረሰብ-መሠረት ባደረጉ ፕሮግራሞች ውስጥ የ20 አመት ልምድ በመስራት ፈቃድ የተሰጠው የማህበራዊ ጉዳይ ሰራተኛ ነው። እርሱ ለቀጥታ አገልግሎት እና በእድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር የአካባቢ ስርዓቶች ላይ አዘኔታ ያሳደረበት ለስምንት አመታት የሳውንድ ትውልዶች (Sound Generations) ተቀጣሪ ነበረ። እሱ፣ በመጀመሪያ ከኒውዮርክ ከተማ፣ ከእሳት እልቂት/ ከሆሎኮስት (Holocaust) የተረፉ፣ ከHIV/AIDS ጋር ከሚኖሩ በእድሜ የገፉ ሰዎች እና ከኒውዮርክ ከተማ የመኖሪያ ቤቶች ባለሥልጣን ጋር በተፈጥሮ ለሚሆን የጡረታ ማህበረሰብ (NORC) ነዋሪዎች አገልግሎት በመስጠት ሰርቷል። ከማህበረሰብ ስራ በተጨማሪ፣ በከተማዋ ዙሪያ የህዝብ ቦታዎችን ለማንቃት አኪራ ከኪነ ጥበብ እና ባህል ቢሮ፣ ከሜይናርድ አሌይ (Maynard Alley) አጋርነት እና ከSDOT ጋር አጋርነት ያደረገ አርቲስት ነው። ሌሎች ፕሮጀክቶች የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ፖሊሲ ቤተ ሙከራ፣ አምፕሊፋየር አርት (Amplifier Art)፣ እና አቫዝ (Avaaz)ን ያካትታሉ። የእሱ ኪነ ጥበብ ብዙውን ጊዜ ለእሱ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማህበራዊ ግንዛቤን ለማንሳት ከሱ ማህበራዊ ስራ ስልጠና ጋር ይተላለፋል። 

አንዲ ፋም (Andy Pham)፣ የትንሽ ሳይጎን ጓደኞች

አንዲ ፋም (Andy Pham) (እሱ/እሱን) የትንሽ ሳይጎን ወዳጆች (FLS) የማህበረሰብ ተሳትፎ ስራ አስኪያጅ ነው፣ በትንሽ ሳይጎን ማህበረሰብ ውስጥ ከትናንሽ ንግዶች፣ ነዋሪዎች፣ በጎ ፈቃደኞች እና የማህበረሰብ አጋሮች ጋር በመተባበር የሚሰሩ። በደቡብ ሲያትል ውስጥ ካደገ በኋላ፣ አንዲ ሀብታሞች የወሰዱባቸው የድሆች መኖሪያ (ነዋሪዎች ፈልሰው መተካካት) አካባቢ ኃይሎች እና ወደ መፈናቀል እና ጉልህ የሆኑ ባህላዊ/ ማህበራዊ መልህቆችን እንዲደመሰሱ ስለሚያደርጉት የእድገት የአቅጣጫ ንድፍ እጅጉን በጥልቅ ያስባል።  አንዲ የተለያዩ ሁሉም አስተዳደግ ያላቸው ሰዎች እና የተኖረበት ልምምዶች የሚፈውሱ እና የሚያበለጽጉበትን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ቤተሰብ እና ለደህንነታችን ቅድሚያ የሚሰጠውን ማህበረሰብ ያልማል። ከFLS በፊት፣ እርሱ ኪንግ ካውንቲ በድጎማ የተደገፈ የመኖሪያ ቤት ስርዓት ውስጥ ለሚኖሩ አዲስ ሰፋሪዎች እና ቀለም ያላቸው ስደተኛ ወጣቶች ከትምህርት በኋላ ነፃ ፕሮግራም የሚደረግበት የወጣቶች ልማት ሰራተኛ ሆኖ ሰርቷል። ደግሞም እርሱ በአስተባባሪነት በአጎራባች የቤት የፍትሃዊ እኩልነት እና ብዝሃነት ኮሚቴ ውስጥ አገልግለዋል። አንዲ ከማካሌስተር (Macalester) ኮሌጅ በአለም አቀፍ ልማት ተኮር በኢኮኖሚክስ የቢኤ ዲግሪ አግኝቷል።

ዳልተን ኦወንስ፣ UW ወንድማማችነት ተነሳሽነት

ዳልተን ኦወንስ በአሁኑ ጊዜ በቬንቸር ጄኔራል ኮንትራክቲንግ (Venture General Contracting) LLC እንደ ፕሮጀክት መሐንዲስ ተቀጥሮ የሚሰራ የተገነባ የተፈጥሮ አካባቢ ባለሙያ ነው። እርሱ ከዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ በሁለቱም የትላልቅ ከተማ፣ ንድፍ እና እቅድ ማድረግ፤ እና የፖለቲካል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን (Bachelor's Degree) አግኝቷል። ዳልተን በተገነባው የተፈጥሮ አካባቢ እና በማህበራዊ አወቃቀሮች/ አውታሮች መካከል ስላለው መስቀለኛ መተላለፊያ ጥልቅ ስሜት ያሳያል። እሱ ሁሉንም በተለይም በታሪክ የተገለሉትን ማህበረሰቦች ታሳቢ በማድረግ ንድፍ ማድረግ እና ከግምት ውስጥ በማስገባት መገንባት የሁሉም የተገነቡ የተፈጥሮ አካባቢ ባለሙያዎች (Built Environment Professionals) ኃላፊነት እንደሆነ በጽኑ ያምናል። 

ከቀለም ትምህርት/ የረቀቀ አስተሳሰብ ጋር የተያያዘ እና ሙያዊ ስራው ውስጥ ሁሉ፣ ዳልተን በማህበረሰብ ለሚመሩ ስራዎች ጥልቅ ፍቅር የለው ነው። በአሁን ጊዜ ያለው ሚናዎች ለሲያትል ከተማ የማቀድ ስራ ኮሚሽን እንደ የተሳተፍ ኮሚሽነር በመሆን እና እሱ ለሚወክለው ድርጅት ለወንድማማችነት ተነሳሽነት (Brotherhood Initiative) የቀድሞ ተማሪዎች አማካሪ (Alumni Mentor) በመሆን ለመጓጓዣ ፍትሃዊ እኩልነት የስራ ቡድን ማገልገልን ያጠቃልላል። የወንድማማችነት ተነሳሽነት ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ቀለም ያላቸውን አዋቂ ወንዶች ለመደገፍ የሚፈልግ በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ በቡድን ላይ የተመሰረተ ፕሮግራም ነው። ዳልተን ከድርጅቱ ጋር የተቆራኘ በ2017 ሲሆን እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወጣት አባላትን የበለጠ ለመደገፍ የመሪነት ሚናዎችን ወስዷል። 

ማሪሳ ፓርሾታን (Marisa Parshotam)፣ የሌክ ሲቲ ኮሌክቲቭ

ማሪሳ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ከሌክ ሲቲ ኮሌክቲቭ ጋር ተሳትፎ ታደርግ ነበረች፣ በመጀመሪያ በ2019 የዜጎች በብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወደ ውጭ ማዳረስ ተሳትፎ ፕሮጄክት፣ ከዚያም በተፈጥሮ አካባቢ እና በጸረ-ከቤት የመፈናቀል ጥረቶች ላይ ያተኮረ በ2020 እንደ የድርጅቱ የአመራር ኮሚቴ አባል በመሆን ተሳትፋ ነበር። ከ6 ዓመታት በላይ የእንግሊዘኛ፣ የቴክኖሎጂ፣ የሰራተኛ ኃይል፣ እና የአመራር ፕሮግራሞች አዘጋጅ በመሆን ራሳቸውን ለሚያውቁ እንግሊዘኛ ተማሪዎች (መጀመሪያ ከLiteracy Source ከዚያም ከOneAmerica ጋር) ከተለያዩ አስተዳደግ እና የቋንቋ ቡድኖች ከሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው አዲስ ሰፋሪዎች፣ ስደተኛ እና የጥቁር፣ የተወላጆች እና የቀለም ሰዎች (BIPOC) ማህበረሰብ አባላት ጋር በቀጥታ አስተባባሪ ሆና ሰርታለች። ለማህበረሰብ ተሳትፎ፣ ለቋንቋ ፍትህ እና ለማደራጀት ያላት ፍቅር ከLake City Collective ጋር በነበራት ተሳትፎ ጉልህ በሆነ መልኩ በእሷ ተቀርጿል እና በሲያትል የመርከብ መተላለፊያ ቦይ ሰሜን ያሉ የBIPOC ማህበረሰቦችን የሚነኩ ድምጾችን እና ጉዳዮችን ማዕከል በማድረግ ሆን ተብሎ የነበረው ተሳትፎ ጉልህ የሆነ ቅርፅ ሰጥቶታል። ማሪሳ በሰሜን ምስራቅ ሲያትል ትኖራለች እና ፍትሃዊ እኩልነትን፣ እድሎችን እና ሀይልን በሷ ማህበረሰብ ውስጥ ከአዲስ ሰፋሪዎች እና ከ BIPOC ጋር ለመገንባት ከልብ ስሜት ታሳያለች። እሷ ለማህበረሰቡ ባላት ፍቅር እና ብዙውን ጊዜ በውሳኔ ሰጪነት እና በህይወታቸው ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ተቋማትን ማእከል ከሚያደርጉ ውይይቶች የተገለሉ ሰዎች ያላት ፍላጎት ትመራለች። 

ሼረን ሶበርስ-አውትሎው (Sharon Sobers-Outlaw)፣ Wider Horizons Village

ሼረን ሶበርስ-አውትሎው፣ MSW, MHP, CDP፣ እንደ ክሊኒካል ማህበራዊ ሰራተኛ፣ አማካሪ እና የአናሳ የአእምሮ ጤና አማካሪ የምስክር ወረቀት ያላት የባለ በርካታ ሚናዎች ያሉት ባለ ብዙ ገፅታ ባለሙያ ናት። ለወደፊቱ ባለሙያዎች የጠበብት ዕውቀቷን በማስተላለፍ ቀደም ሲል በሲያትል ሴንትራል ካውንስሊንግ 101 የትርፍ ጊዜ በዩኒቨርሲቲ መምህር ሆና አገልግላለች። ሼረን ውጤታማ ድጋፍ እና ጣልቃገብነት የመስጠት አቅሟን የበለጠ በማጎልበት፣ የባህሪ ማነቃቂያ አስገጋሚ/ ቴራፒስት (Behavior Activation Therapist) ናት። በእርጅና እና እንክብካቤ በመስጠት ላይ ውጤታማ የህዝብ ግንኙነት አድራጊ። በእርጅና ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ንቁ ተሳትፎ ከማድረግ ጋር፣ ጠንካራ ቁርጠኝነት ያለው ወደ ተሟላ እንክብካቤ እና ለእናቷ እንደ የሙሉ ጊዜ ተንከባካቢ ሚናዋ ወደ ተሟጋችነት ይዘረጋል። የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሌቺ (Leschi) 9ኛው የማህበረሰብ ምክር ቤት፣ የማዕከላዊ ወረዳ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የሰፊው ከተማ (City Wide) ሰፈር ምክር ቤቶች አባል፣ በተጨማሪም፣ ለ ONYX Fine Arts Collective Board እና ለመጓጓዣ መምሪያ የመጓጓዣ ፍትሃዊ እኩልነት የስራ ቡድን፣ ባህላዊ ግንዛቤ፣ ፍትሃዊ እኩልነት፣ አካታችነት፣ እና ማህበራዊ ፍትህ የጋለ ስሜት በመመራት የአመራር ክህሎቷን አበርክታለች።

የቀድሞ TEW አባላት

  • ብራያን ቹ (Brian Chu)፣ ሜሪስ ፕሌስ (Mary's Place)
  • ርዝዋን ርዝዊ (Rizwan Rizwi) (ማዕረጉን የያዘ ተባባሪ ሊቀመንበር (Emeritus)፣ የሙስሊም መኖሪያ ቤቶች አገልግሎቶች
  • ዮርዳኖስ ተፈሪ (ማዕረጉን የያዘ ተባባሪ ሊቀመንበር (Emeritus)፣ የብዝሃን አገልግሎት ማዕከል (MSC)
  • ስቲቨን ሶውየር (Steven Sawyer) (ማዕረጉን የያዘ ተባባሪ ሊቀመንበር (Emeritus)፣ በኤድስ አውታረ መረብ ላይ ቀለም ያላቸው ሰዎች (POCAAN)
  • አን ሁይንህ (An Huynh)፣ ሲያትል ቻይናታውን አለም አቀፍ ዲስትሪክት የጥበቃ እና ልማት ባለስልጣን (SCIDpda)
  • ካሪያ ዎንግ (Karia Wong)፣ ቻይና የመረጃ እና አገልግሎት ማዕከል (CISC)
  • አሚር ኑር ሶልኪን (Amir Noir Soulkin)፣ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አገልግሎት (EACS)
  • ቢቢ ጆንስ (BB Jones)፣ አዲስ አድማስ
  • ኤሌና ጆንስ (Ellena Jones) (ማዕረጉን የያዘ ተባባሪ ሊቀመንበር (Emeritus)፣ Passion to Action
  • ሴሳር ጋርሲያ (Cesar Garcia)፣ Lake City Collective
  • ዩ-አን ዩን (Yu-Ann Youn) (ማዕረጉን የያዘ ተባባሪ ሊቀመንበር (Emeritus)፣ UW Robinson ማዕከል 
  • ኤላኒ ኬይስ (Ellany Kayce)፣ Duwamish የጎሳ አገልግሎቶች
  • ካታሚ ቻው (Khatami Chau)፣ የምግብ ማበረታቻ ትምህርት እና ዘላቂነት ቡድን (FEEST)
  • ኪያና ፓርከር (Kiana Parker)፣ የ UW የልምድ ትምህርት እና ዕድል ማዕከል
  • ክሪስቲና ፒርሰን (Kristina Pearson)፣ Duwamish የጎሳ አገልግሎቶች
  • ክሪስ ሮድስ (Chris Rhodes)፣ Rainier Valley Corps
  • ክርስቲና ቶማስ (Christina Thomas)፣ Rainier Valley Greenways
  • ፊልስ ፖርተር Phyllis Porter)፣ Rainier Valley Greenways
  • ሚክያስ ሉሲኛን (Micah Lusignan)፣ የአካል ጉዳተኛ መብቶች WA
  • ጁሊያ ጀነን ሺልድስ (Julia Jannon-Shields)፣ Puget Sound Sage
  • ሶኩንቲያ ኦኬ (Sokunthea Ok)፣ የጎረቤቶች ማህበረሰብ ግንኙነት መምሪያ
  • አናሊያ በርቶኒ (Analia Bertoni)፣ የጎረቤቶች ማህበረሰብ ግንኙነት መምሪያ

Transportation

Adiam Emery, Interim Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.