የሲያትል የትራንስፖርት ፍትሃዊነት ማዕቀፍ
አማርኛ • 繁体字 • 简体中文 • ភាសាខ្មែរ • 한국어 • Oromiffa • af-Soomaali • Español • Tagalog • ትግርኛ • Tiếng việt • English
ዘር ተኮር የሆኑ ፖሊሲዎች እና የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት ቅነሳዎች ታሪክ፣ ባለ ቀለም ቆዳ ያላቸው ማኅበረሰቦች በመፈናቀል ምክንያት ከነጭ ዜጎች የበለጠ ረጅም ጉዞ ማድረግን፣ እና በአብዛኛው ጥራቱን ለልጠበቀ የመጓጓዣ አገልግሎት ያላቸው ዕድል አነስተኛ መሆንን ጨምሮ በመጓጓዣ ሥርዓታችን ውስጥ ኢ-ፍትሃዊነቶችን ፈጥረዋል። ባለቀለም ቆዳ ያላቸው ማኅበረሰቦች ለብክለት ያላቸው አስተዋፅኦ አነስተኛ ቢሆንም፣ ዕድሎችን እና ሀብት ለማግኘት ያላቸው ተደራሽነት ውስን መሆኑን ጨምሮ የዚህ ዘረኝነት የረጅም ጊዜ አሉታዊ ውጤት በበለጠ ተጠቂዎች ናቸው። ይህንን አዲስ የመጓጓዣ እኩልነት ማዕቀፍ (TEF) በሥራ ክፍል ፖሊሲዎች እና የሥራ ክንዋኔዎች ውስጥ ማቀናጀት ለዚህ ችግር መፍትሔ የመስጠት ሂደቱን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ነው።
ልማት
የመጓጓዣ እኩልነት የሥራ ቡድን (TEW) ጥቁሮችን፣ ተወላጆችን፣ እና ባለ ቀለም ቆዳ ያላቸውን እና ተጋላጭ ማኅበረሰቦችን ከሚወክሉ ሰፊ እና የተለያዩ የማኅበረሰብ አባላት ግብዓት ለማግኘት ታስቦ በ 2019 መጀመሪያ ላይ የተቋቋመ ነው። እያንዳንዳቸው የ TEW አባላት በሲያትል-ኪንግ ካውንቲ ክልል ካሉ አካባቢያዊ ድርጅቶች ጋር ትስስር ያላቸው ሲሆን ያላቸውን ልምድ እና ሙያዉ ዕውቀት ከመጓጓዣ ጋር ተያያዥ ለሆኑ ተግዳሮቶች መፍትሔ ሊሆኑ የሚችሉ ተግባራትን ለመለየት ይጠቀሙበታል። የተገኙት ግብዓቶችም ለ TEF የእሴቶች እና ስልቶች ስብስብ ለመለየት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ይህ ስብስብም የሲያትል የመጓጓዣ ሥራ ክፍል (SDOT) ሠራተኞችን ተግባራት ለመጪዎቹ ዓመታት የሚመራ ይሆናል።
በመጓጓዣ እኩልነት መርሐ ግብር (TEP) የጋራ ግቦች መሠረት፦
- TEF በትብብር እኩልነት የሰፈነበትን የመጓጓዣ ሥርዓት ለመፍጠር የሚያስችል የውሳኔ ሰጭዎች፣ ሠራተኞች፣ ባለድርሻ አካላት፣ አጋሮች እና ለሰፊው ማኅበረሰብ የ የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (የሲማመ) ፍኖተ-ካርታ ነው።
- ከሲያትል ከተማ የዘር እና ማኅበራዊ ፍትህ ተነሳሽነት (RSJI)፣ በመነሳት ተቋማዊ በሆኑ ዘረኝነቶች ምክንያት በመጓጓዣ ሥርዓታችን ውስጥ ያሉትን አለመመጣጠኖች TEF ምላሽ ይሰጣቸዋል።
በ 2021 የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (የሲማመ) የትግበራ ዕቅዱን በጋራ ለመንደፍ ከ TEW አባላት ጋር በትብብር መሥራቱን ቀጥሏል። ከጥር እስከ ነሓሴ 2021 የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (የሲማመ) ሠራተኞች እና የ TEW አባላት የትግበራ ዕቅዱን በጋራ ለማዘጋጀት አባላቱ ጥልቅ የሆኑ ግንኙነቶችን እንዲመሠርቱ፣ በንቃት እንዲያዳምጡ፣ እና ፈጠራ በተሞላበት መልኩ ሐሳብ እንዲያመነጩ ያስቻሏቸው ተከታታይ የሆኑ ስብሰባዎች ላይ በትብብር ተሳትፈዋል።
የእኩልነት ማዕቀፍ መርጃ መሣሪያዎች
- የመጓጓዣ እኩልነት ማዕቀፍ፣ ክፍል 1፦ እሴቶች እና ስልቶች
- የመጓጓዣ እኩልነት ጽሑፍ (ታትሞ የሚጋራ)
- የመጓጓዣ የእኩልነት ማዕቀፍ ፎሊዮ
TEF የትግበራ ዕቅድ
የትግበራ ዕቅዱ በ TEF ክፍል አንድ ውስጥ ያሉትን እሴቶች እና ስልቶች የሚያሻሽሉ ዘዴዎችን ያካትታል፦
- እነዚህ ዘዴዎችም ከተሟጋችነት፣ ፖሊሲ፣ መርሐ ግብር፣ ፕሮጀክት ምድቦች እስከ በሥራ ክፍላችን ውስጥ ያሉ የውስጥ ሂደት እና ምርጥ ተሞክሮዎች የመሳሰሉ የአካሄድ ለውጦች ድረስ የተለያየ ምድብ ይይዛሉ።
- ዕቅዱ በመደበኛነት የሚስተካከል፣ ክትትል የሚደረግበት እና የሚሻሻል ተለዋዋጭ ሰነድ እንደሆነ በማሰብ ከ 2022 እስከ 2028 የሚቆይ ይሆናል።
ከታች የቀረበው መስተጋብራዊ የአተገባበር ዕቅድ ከ 200 በላይ የሆኑ በ TEF እሴቶች የተዘጋጁትን ዘዴዎች ያካትታል። የበለጠ ለማወቅ ያስሱ!
TEF ዳሽቦርድ
የተጠቀሱ ምንጮች፦