ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማስጀመር (Safe Start) ፈቃዶች ብቻ

ምን አዲስ ነገር አለ

ለማካፈል ያጓጓንን አንዳንድ ጠቃሚ ዝመናያዎችን አድርገናል!

 • ጊዜያዊ ፈቃዳችን ለጠርዝ የመከለያ ቦታ እና የእግረኛ መንገዶች እስከ ጥር 31 ቀን 2023 ድረስ የሚሰራ ይሆናል። እባክዎን ለአጭር ጊዜ ወይም ለረጅም ጊዜም ቢሆን የተፈቀደ አጠቃቀምን ለማስወገድ የሚያስፈልግ የግንባታ ወይም የፍጆታዎች ግጭቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ። ማሳሰቢያ ከ30 ቀናት በፊት መስጠት እና ተጽእኖዎችን ለመቀነስ ለማስተባበር እንሞክራለን።
 • በተጨማሪም፣ ፈቃድ ወሳጆች ከቤት ውጭ ካፌዎቻቸውን ወይም ጊዜያዊ ማሳያዎቻቸውን ከእግረኛ መንገድ ላይ እንዲያነሱ ወይም ያሉ የጠርዝ ክፍት ቦታዎችን ከስራ ሰአታት ውጪ እንዲያስወግዱ የሚጠበቅባቸውን የፈቃድ መስፈርቶቻችንን አስተካክለናል። (ከስራ ሰአታትዎ ውጭ በሚሰራ የጭነት ዞን ተፈቅዶልዎ ክሆነ ወይም በገበሬዎች ገበያ አሻራ ውስጥ ከተፈቀደልዎ ይህ አይተገበርም - እርግጠኛ ካልሆኑ ያነጋግሩን!)
 • እንዲሁም እዚህ ያጸደቅንባቸውን መዋቅሮች እየለጠፍን ነው። ሌሎች ንግዶች የተፈቀደውን እንዲረዱ እና ምናልባትም ለተመሳሳይ የጣቢያ ሁኔታዎች እንዲጠቀሙባቸው እነዚህን እንዲገኙ እናደርጋለን።
 • ይህንን አዲስ መመሪያ ለማንፀባረቅ በአሁኑ ጊዜ የአመልካች ማመሳከሪያ ዝርዝሮችን እያዘመንን ነው። በማረጋገጫው ዝርዝሩ እና በዚህ ማሻሻያ መካከል አለመግባባት በሚፈጠርበት ጊዜ፣ እባክዎ ይህን አዲስ መመሪያ ይከተሉ።

አጠቃላይ እይታ

አሁን እስከ ጥር 31 ቀን 2023 ድረስ የሚሰሩ የተስተካከሉ፣ ነጻ ጊዜያዊ ፈቃዶችን ለከቤት ውጭ ካፌዎች፣ የችርቻሮ ዕቃ ማሳያዎች፣ የምግብ መኪናዎች፣ የሽያጭ ጋሪዎች እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች እያቀረብን ነው! እንዲሁም የምግብ ቤቶችን (ሬስቶራንት)፣ ችርቻሮ፣ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስራዎችን ለመደገፍ ጊዜያዊ የመንገድ መዝጋት ፈቃድን እያቀረብን ነው።

>ከመጀመርዎ በፊት

እባክዎ የደህና ጅማሮ (Safe Start) ፈቃዶቻችን ጥር 31 ቀን 2023 የሚያልቁጊዜያዊ ፈቃዶች መሆናቸውን ልብ ይበሉ። የእኛን መደበኛ ፈቃዶች የሚፈልጉ ከሆኑ፣ እባክዎን ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች የተገናኙትን የፍቃድ ገጾችን ይጎብኙ:

ጊዜያዊ ከቤት ውጭ ካፌ፣ የሸቀጣ ሸቀጥ ማሳያ፣ ሽያጭ፣ የመንገድ መዝጋት እና ከቤት ውጭ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፈቃዶች

ከቤት ውጭ ባሉ ቦታዎች ላይ ባሉት የፈቃድ አማራጮች ስኩፕዎትን (ድርሻዎትን) ያግኙ!

የድርጅት ባለቤቶች ስራዎቻቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማስፋፋት ያሉዋቸውን አማራጮች መለየት እንዲችሉ ለመርዳት፣ ለአስፈላጊ የፈቃድ ግብዣዎች መመሪያ አቀናጅተናል!

እባክዎ ከታች ያለው መረጃ ለጊዜያዊ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማስጀመር (Safe Start) ፈቃዶች ብቻ መሆኑን ያስታውሱ። እባክዎ በመደበኛ ፈቃዶቻችን ፍላጎት ካለዎት፣ ለተጨማሪ መረጃ ከታች የተያያዘውን የፈቃድ ገጾች ይጎብኙ፡

 • ከቤት ውጭ ካፌ
 • የሸቀጣ ሸቀጥ ማሳያ
 • ሽያጭ
 • የጎዳና እና እግረኛ መንገድ ተግባራት
 • በእግረኛ መንገድ ላይ የሚደረጉ ጠረጴዛ እና ወንበሮች

አጠቃላይ እይታ

አሁን ለከቤት ውጭ ካፌዎች፣ ለችርቻሮ ሸቀጣ ሸቀጥ ማሳያዎች፣ ለምግብ ተሽከርካሪዎች፣ ለሽያጭ ጋሪዎች፣ እና ለአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች እስከ ኦክቶበር 31, 2021 ድረስ ጽንቶ የሚቆይ የተሻሻለ፣ ነጻ ጊዜያዊ ፈቃዶችን እያቀረብን ነው! እንዲሁም የምግብ ቤቶችን (ሬስቶራንት)፣ ችርቻሮ፣ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስራዎችን ለመደገፍ ጊዜያዊ የመንገድ መዝጋት ፈቃድን እያቀረብን ነው።

የመንገድ ጠርዝ ቦታዎችን መጠቀምን በተመለከተ

የኩርባ ቦታዎችን ለመጠቀም የሚያመለክቱ ቢዝነሶች (የተከፈለ ወይም ያልተከፈለ) በተጨማሪ በጊዜያዊነት መኪና እንዳይቆም የሚከለክል ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት እና ከባሪኬድ ኩባንያ ማቆም ክልክል ነው የሚል ባሪኬድ መከራየት ወይም መግዛት (T-39 ምልክት) ያስፈልጋቸዋል። አንድ ጊዜ መኪና ማቆምን የሚከለክል ፈቃድ ለማግኘት ካመለከቱ ሊታተም የሚችል ከነቀኑ ማቆም የተከለከለ ነው የሚል ምልክት ይቀርብልዎታል። በቀላሉ ያትሙ እና በባሪኬድዎ ላይ ይለጥፉ። ለማስተካከል ካቀዱበት 72 ሰዓታት በፊት ባሪኬዶቹን እንዲያኖሩ እንመክራለን፣ ነገር ግን ተፈጻሚ እንዲሆን ቢያንስ 24 ሰዓታት ቀድሞ ሊቀመጡ ይገባል። መኪና ማቆም የተከለከለበት ዞን (ቦታ) ላይ መኪና ከቆመ፣ መኪና የመጎተት አገልግሎት የሚሰጡ ኩባንያዎች ጋር መደወል የቢዝነሱ ኃላፊነት ነው።.

በ ... ደህንነቱ የተጠበቀ መጀመር ፈቃድ ለማግኘት ፍላጎት አለኝ

መንገዱን አይዝጉት - የአካባቢ መመሪያዎች ወሳኝ ነገሮች ናቸው!

ለ COVID-19 ቀውስ ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ የእግረኛ መንገድ ላይ ካፌዎች እና የሸቀጣሸቀጥ ማሳያዎች በከተማ ዙሪያ እየበዙ ከመምጣቸው ጋር፣ በቅርቡ ለእግረኛ መንገድ ካፌ ምደባ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ከአካል ጉዳተኞች እንቅስቃሴ ኢኒሽዬቲቭ ጋር በዋሽንግተን ከአካል ጉዳተኞች መብቶች ውስጥ ትብብር ፈጥረናል።

ጊዜያዊ ከቤት ውጭ የካፌ ፈቃድ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማስጀመር (Safe Start)

ይህ ፈቃድ የሬስቶራንት አገልግሎት እና ከቤት ውጭ በእግረኛ መንገድ ወይም በኩርባ (ጠርዝ) ላይ ባለ የመኪና ማቆሚያ ላይ መቀመጥን እስከ ጥቅምት 31, 2021 ድረስ ይፈቅዳል። የአልኮል አገልግሎት በ"ከቤት ውጭ የመጠጥ አገልግሎት አቅርቦት" በኩል በዋሺንግተን ስቴት የመጠጥ ቁጥጥር ቦርድ (WSLCB) ሊፈቀድ ይችላል። ሂደቱን ለመጀመር የለውጥ ጥያቄ ቅጹን ያውርዱ። የአልኮል አገልግሎትን በተመለከተ ማንኛውንም ጥያቄ ካለዎት እባክዎን WSLCBን ያነጋግሩ።

ማመልከት የሚችለው ማን ነው?

ማወቅ ያለብዎት ነገር፥

 • ከቤት ውጭ መመገቢያ ከሬስቶራንቱ አጠቀብ ባለ የእግረኛ መንገድ ወይም በ ኩርባ ላይ ባለ የመኪና ማቆሚያ ላይ መሆን አለበት።
 • ሬስቶራንቶች የአጥር መስፈርትን ለማሟላት የእራሳቸውን አጥር እና/ወይም ማስቀየሻዎች ሊኖራቸው ይገባል። ለምሳሌ እንዲሆን እባክዎ ለጊዜያዊ ከቤት ውጭ መሳሪያዎች ፈቃድ ላይ በራሪ ወረቀታችንን ይመልከቱ።
 • ያለ ተጨማሪ SDOT ግምገማ ሊጠቀሙባቸው በሚችሉ መጠለያዎች እና የቤት ዕቃዎች ላይ ዝርዝር መረጃዎችን የያዘ የአየር ሁኔታ ጥበቃ መመሪያን አሳትመናል።
 • እባክዎን የሲያትል የእሳት አደጋ መከላከያ መምሪያ (Seattle Fire Department)፣ የሲያትል የግንባታ እና ቁጥጥር መምሪያ (Seattle Department of Construction and Inspections)፣ እና የሲያትል የአከባቢ ታሪካዊ/የመሬት አቀማማጥ (Seattle Department of Neighborhood Historic/Landmark) ማረጋገጫዎች አሁንም አስፈላጊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይወቁ፣ እንዲሁም እነዚያ ኤጀንሲዎች እርስዎ ያቀረቡት ሀሳብ ላይ ተጽኖ ማምጣት የሚችሉ ተጨማሪ ሕጎች ሊኖራቸው ይችላል።
 • በሕዝብ ላይ አደጋ ሊያስከትሉ በሚችሉ አውሎ ነፋሶች ወይም ከፍተኛ ነፋሶች ወቅት ማውረድን ጨምሮ ለሁሉም መሳሪያዎች እርስዎ ኃላፊነት አለብዎት
 • ከተማው ለመሳሪያው መጎዳት፣ መሰረቅ፣ ወይም አላግባብ ጥቅም ላይ መዋል ኃላፊነት የለበትም
 • ጊዜያዊ ከቤት ውጭ ካፌዎች በዓይነታቸው በነባር የመጫኛ ዞኖች ውስጥ አይጸድቅም፣ ሆኖም በተለየ ሁኔታ ልናይ እንችላለን።
 • ጊዜያዊ ከቤት ውጭ ካፌዎች በመጓጓዣ መስመሮች (የብስክሌት እና አውቶቢስ መስመሮችን ጨምሮ) ላይ ላይደረጉ ይችላሉ
 • ጊዜያዊ የተፈቀዱ ካፌዎች መዋቅሮች ከሥራ ሰዓታት ውጭ በሕዝብ ቦታ ላይ ሊቆዩ ይችላሉ። (ፈቃድ የተሰጠዎት ከሥራ ሰዓቶችዎ ውጭ በሚሠራው የጭነት ቀጠና ውስጥ ወይም በአርሶ አደሮች የገቢያ ቦታt ውስጥ ከሆነ፣ ይህ ተግባራዊ አይሆንም - እርግጠኛ ካልሆኑ እኛን ያግኙን!)
 • ሬስቶራንትዎ በተወሰነ ታሪካዊ ዲስትሪክት ውስጥ የሚገኝ ከሆነ፣ ፈቃዱ ከመሰጠቱ በፊት ከታሪካዊው ዲስትሪክት ማረጋገጫ ማግኘት አለብዎት፣ ሆኖም ሠነዶችዎን ወደነሱ ስለምንልክ በተናጠል (ለብቻው) ማመልከት አያስፈልግዎትም።
 • ከእኛ ዘንድ ነባር የእግረኛ መንገድ ላይ ካፌ ፈቃድ ካለዎት እና ማስፋፋት ከፈለጉ፣ በጊዜያዊነት ለመጠቀም አዲስ ማመልከቻ ማስገባት ያስፈልግዎታል
 • liእንዲሁም በጊዜያዊነት ጎዳናዎን ለተሽከርካሪ ትራፊክ ለመዝጋት ፈቃዶችን እናቀርባለን። እርስዎ እና በእርስዎ ብሎክ (መስመር) ያሉ ሌሎች የንግድ ስራዎች ለዚህ ፈቃድ ፍላጎት ካላችሁ፣ እባክዎን የእኛን ጊዜያዊ የመንገድ መዝጋት አስተማማኝ ጅምር ገጻ ይመልከቱ።

ለህብረተሰብ የማሳወቅ መስፈርቶች

ፈቃዳችንን በፍጥነት ለማውጣት ለአዳዲስ ጊዜያዊ የቤት ውጪ ማሳያያዎች የተለመደው ሁለት-ሳምንት የይፋዊ አስተያየት ጊዜ አንጠይቅም። ይልቁንም፣ አመልካቾች ስራ ከመጀመራቸው ቢያንስ 2 ቀናት በፊት የታቀደውን ጊዜያዊ ካፌ በአቅራቢያው ለሚገኙ ነዋሪዎች እና ንግድ ቤቶች ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል።

መሙላት፣ ማተም፣ እና ማሰራጨት የሚችሉት የህብረተሰብ ማሳወቂያ በራሪ ወረቀትን ያውርዱ!

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

206-684-7623 ላይ ያነጋግሩን። የትርጉም አገልግሎቶች በነጻ ይገኛሉ!

ለማመልከቻዎ፣ ሳይት ፕላን እንፈልጋለን፣ እንዲሁም የድርጅቱ ወይም ንብረቱ ባለቤት ካልሆኑ የፈቃድ (ማረጋገጫ) ደብዳቤ ሊያስፈልገን ይችላል።

የፈቃድ ወይም የማረጋገጫ ደብዳቤ: የድርጅቱ ወይም ንብረቱ ባለቤት ካልሆኑ የተፈረመ የፈቃድ ደብዳቤ ይጫኑ 

የሳይት ፕላን ዓይነቶች:

የቦታ ፕላን ሳይኖር ማመልከቻዎን ልናይ አንችልም።ሳይት ፕላን መጠቀም የፈለጉትን የቦታ ልኬት እና ትክክለኛ መገኛውን ያሳያል። ከመጫንዎ በፊት ፕላንዎን ለማዘጋጀት ከሚከተሉት መንገዶች አንዱን መምረጥ ይችላሉ።

አማራጭ 1፡ ፎቶግራፍ ላይ የተመሠረተ ፕላን (የሚመከር!)
 • ከዚህ በታች ያሉትን ልዩ መመሪያዎችን የሚከተሉ 3 ፎቶግራፎችን በመጠቀም በፎቶግራፍ ላይ የተመሠረተ ፕላን ያዘጋጁ
 • ሁሉም 3 ፎቶግራፎች ሳይት ፕላንዎን እንዲሸፍኑ ይጠበቃል። ከፎቶግራፍዎችዎ ውስጥ አንዱ በሳይት ፕላን ዝርዝር ውስጥ በይበልጥ ከታች የተገለጹትን አስፈላጊ ልኬቶች ማሳየት አለበት።
 • በፎቶግራፍ የቦታውን ማሳያ በዲጅታል ለማሳየት የሚክብድዎት ሆኖ ካገኙ፣ እባክዎ የታቀደውን የማሳያ ጠርዞች ወይም ሙሉ ንድፍ በቀጥታ በእግረኛ መንገዱ ወይም በጎዳናው ላይ ክር ወይም ቾክ በመጠቀም “ይሳሉ”። ፎቶዎችን ከማንሳትዎ በፊት ይህንን ያድርጉ!
  • ፎቶ #1: ከታቀደው ካፌ 10 ጫማ ያህል በመራቅ የታቀደውን የካፌ ቦታ ፎቶ ያንሱ። ጠርዞቹን አስቀድመው ምልክት አድርገውበት ከሆነ፣ በፎቶው ውስጥ ያስገቡ፣ እንዲሁም መገኛውን ለመለየት እንዲረዳ የተወሰኑ ከጀርባ ያሉትንም ያስገቡ!
  • ፎቶ #2: የታቀደውን የካፌ ቦታ በሌላኛው አቅጣጫ ተመሣሣይ ፎቶ ያንሱ።
  • ፎቶ #3: የሬስቶራንትዎን/ህንጻዎን ፊት ለፊት በሙሉ እና የካፌውን ጠርዞች ጨምሮ የሚያሳይ ፎቶ ያንሱ።

ከፎቶዎቹ አንዱን ይምረጡ እና ሁሉንም ተፈላጊ ልኬት ለማጠቃለል ምልክት ያድርጉበት። ይህንን በዲጅታል መስራት ይችላሉ፣ ወይም ፎቶውን በማተም (በማጠብ) በእጅ ምልክት ያድርጉበት።

ፎቶ #2: የታቀደውን የካፌ ቦታ በሌላኛው አቅጣጫ ተመሣሣይ ፎቶ ያንሱ።
መደበኛውን ሳይት ፕላን ያስገቡ (የዕቅድ ቴምፕሌት እዚህ ሊያገኙ ይችላሉ)። መደበኛ ሳይት ፕላን እንዴት እንደሚዘጋጅ ስልጠና ለማግኘት እባክዎ በስልክ ቁጥር 206-684-7623 ይደውሉልን።
 • የሳይት ፕላን ዝርዝሮች:ሳይት ፕላዎን በሚያዘጋጁበት ጊዜ፣ ከታች የተዘረዘሩትን ሁሉንም መረጃ ማጠቃለል አለበት። ከዚህ መረጃ ውጪ፣ ማመልከቻዎን ለማየት እና ለማጽደቅ ረጅም ጊዜ ልወስድብን ይችላል። ለዚህም የርዝመት መለኪያ ሜትር ማግኘት እና በፕላንዎ ላይ በግልጽ ማሳየት ያስፈልግዎታል፡
 • የማሳያ ቦታ ልኬቶች፡የታቀደውን ከቤት ውጭ ካፌ አካባቢ ርዝመት እና ስፋት ያሳዩ።  በእግረኛ መንገድ ባለው “ፈርኒቸር ዞን” ውስጥ ባለ ቦታ ላይ ካቀዱ፣ ከእግረኛ መንገድ (ጠርዝ) ጀምሮ የታቀደው ማሳያ ቦታ ያለውን ልኬት ማሳየት አለብዎት። በመንገዱ ጠርዝ እና ጊዘያዊ የውጭ መቀመጫ ቦታዎት ከሚጀምርበት ቦታ መካከል ቢያንስ 4’ እንዶኖር ያስፈልግዎታል።
 • የእግረኛ ነጻ ዞን፥እግረኞች በእግረኛ መንገዱ ላይ እንዴት መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ለማሳየት ከየውጭ መቀመጫ ቀጥሎ ያለውን የእግረኛ መንገድ ስፋት ያሳዩ። በአብዛኛው ሰፈር ውስጥ የሚያስፈልገው ዝቅተኛው የእግረኛ ነጻ ዞን 6 ጫማ ነው (በአንዳንድ የከተማ አካባቢዎች የሚፈለገው ዝቅተኛ ስፋት 8 ጫማ ነው)። 
  • ማስታወሻ፥ዝቅተኛውን ነጻ ዞን ለማስጠበቅ በቂ ቦታ ከሌለ፣ ለዚህ ፈቃድ ብቁ ላይሆኑ ይችላሉ።
 • ከሌሎች ቋሚ ነገሮች የሚኖር እርቀት፥የእግረኛ መንገዱ እንደ የመብራት ምሶሶ፣ ዛፎች፣ የመኪና ማቆሚያ ሜትሮች፣ የውሃ መሳቢያ ቧንቧዎች፣ እና የብስክሌት ማቆሚያዎች ያሉ ሌሎች ቁሶችን ሊጨምር ይችላል። እባክዎ ከእነዚህ ቁሶች እስከ የቦታዎ ማሳያ ጠርዝ ድረስ ያለውን ርቀት ይስፈሩና እነኚህን ልኬቶች በፕላንዎ ውስጥ ያካትቱ።
 • የጠርዝ ቦታ መለያ ቁጥሮች፥በሚከፈልበት የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ላይ ለካፌ መጠቀም ካቀዱ፣ እባክዎ የጠርዝ ቦታውን መለያ ቁጥር(ሮች) ያቅርቡ (ቁጥሮቹን ለማግኘት ይህን ካርታ ይጠቀሙ)።
  • መግለጫ፥ ከሚያስፈልጉ ልኬቶች ጋር የሳይት ፕላን ምሳሌ ፎቶግራፍ 
 • የአጥር እና ማስቀየሻዎች ዝርዝሮችአጥር ለሁሉም የጠርዝ ቦታ ካፌዎች እና በፈርኒቸር ዞን ውስጥ ላሉ ካፌዎች (ከኩርባ አጠገብ በእግረኛ መንገድ ላይ) ያስፈልጋል፣ እንዲሁም ከህንጻው ቀጥሎ ላሉ ካፌዎችም ሊጠቅም ይችላል። ከህንጻው አጠገብ አጥር የለሽ ካፌ ምርጫዎ ከሆነ፣ ማስቀየሻዎች ለ ADA ዓላማዎች ያስፈልጋሉ። ያቀዱት አጥር ያለውን ወይም አጥር የሌለውን ካፌ መሆን አለመሆኑ ላይ በመመስረት፣ የሚከተሉትን ዝርዝሮች እንፈልጋለን፡ 
  • ልኬቶችን እና ስዕሎችን ወይም ፎቶን ጨምሮ ለአጥር የለሽ ካፌዎች የማስቀየሻ መግለጫ እንፈልጋለን። ማስቀየሻዎች ከፍታቸው ከ 30” እስከ 42” መሆን አለባቸው ። 
  • ልኬቶች፣ ስዕል ወይም ፎቶን ጨምሮ አጥር ላላቸው ካፌዎች የአጥር መግለጫ፣ ወይም የአጥር መሳሪያዎች መግለጫ። አልኮል የሚቀርብ ከሆነ የአጥሩ ከፍታ 42” መሆን አለበት፣ እንዲሁም አልኮል የማይቀርብ ከሆነ የአጥሩ ከፍታ በ 30” እና 42” መካከል መሆን አለበት።
  • በእግረኛ መንገድ ላይ የሚሰራ የትኛውም አጥር በከዘራ የሚነኩ መሆን አለባቸው፤ ይህ በኩርባ (ጠርዝ) ቦታ ላይ ባለ ካፌ አጥር ከእግረኛው መንገድ ጎን ለጎን የተሰራውንም ክፍል ይጨምራል። 
 • በታሪካዊ ዲስትሪክቶች ውስጥ የሚገኙ ከሆኑ፣ ከሳይት ፕላንዎ ጋር ለመጠቀም ያቀዱትን የሁሉም ፈርኒቸር፣ ድንበር መለያዎች፣ አትክልት የሚተከልባቸውን፣ የአጥር፣ ወይም ሌሎች ዓይነቶችን ቀለም እና አጨራረስ የሚያሳይ ሰነድ(ዶች)ይጫኑ።
 • ካታሎግ የተቆረጡ ወረቀቶች በከለር (በቀለም) እስከሆነ ድረስ ተቀባይነት አላቸው። ይህንን መረጃ ለታሪካዊ ዲስትሪክት ሰራተኛ እንዲያዩት እንልካለን፤ ለማጽደቂያ የምስክር ወረቀት እርስዎ በተናጥል ለእነርሱ ማስገባት አይጠበቅብዎትም።
 • ማስታወሻ፥ የተፈቀደውን ቦታ ለመግለፅ ከሚጠቀሙባቸው የአጥር እና የትራፊክ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች በስተቀር፣ ብዙ ደማቅ ያልሆኑ ቀለሞች፣ እንደ ግራጫ/ጥቁር አረንጓዴ ወይም ተመሳሳይ ለማንኛውም የቤት ዕቃዎች፣ አጥር፣ ወይም ለሚለጠፉ ነገሮች ይመከራሉ። 
ቀጣዩ ነገር ምንድን ነው? አንድ ጊዜ ለአስተማማኝ ጊዜያዊ የሽያጭ ማስጀመሪያ ፈቃድ ማመልከቻዎትን ካስገቡ፣ ስራውን ለመጀመር ለመዘጋጀት መውሰድ ያለብዎ የተወሰኑ ተጨማሪ እርምጃዎች እዚህ አሉ!  
 • በጠርዝ ላይ ያለን ቦታ ለመጠቀም ካቀዱ፣ ከቡድናችን ከሚሰጠው ፈቃድ በተጨማሪ፣ በጊዜያዊነት መኪና ማቆምን የሚከለክል ፈቃዶችን ለማግኘት ማመልከት ያስፈልግዎታል።  ለዚህ ፈቃድ ለማመልከት እንድናግዝዎ
 • አዲሱን ስራ ከመጀመርዎ ቢያንስ ከሁለት ቀን በፊት በህዝብ ቦታው ላይ ለመስራት ስላሰቡት ነገር ለጎረቤቶች ያሳውቁ።  ይህንን የህብረተሰብ ማሳወቂያ በራሪ ጽሁፍ ቴምፕሌት ይጠቀሙ።
 • የከተማዋን መስፈርቶች ያሟላ ኢንሹራንስ መያዝዎን ያረጋግጡ። ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ በ (206) 684-7623 ላይ ይደውሉልን።
ጠቃሚ ሆኖ ሊያገኙት የሚችሉትን የከቤት ውጭ መሳሪያ አማራጮች መመሪያ ከታች ባለው ሊንክ ይከተሉ።

ጊዜያዊ ከቤት ውጭ የሸቀጣ ሸቀጥ ማሳያች ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማስጀመር (Safe Start)

በዚህ ፈቃድ፣ የችርቻሮ ንገዶች በጊዜያዊነት ስራቸውን ወደ ውጭ ወደ እግረኛ መንገድ ወይም በመኪና ማቆሚያ ውስጥ ባለ ጠርዝ እስከ ጥቅምት 31, 2021 ድረስ ማስፋፋት ይችላሉ።

ማመልከት የሚችለው ማን ነው?

 • የችርቻሮ ንግዶች

ማወቅ ያለብዎት ነገር፥

 • ጊዜያዊ የሸቀጣ ሸቀጥ ማሳያ ከንግዱ አጠገብ ባለው የመኪና ማቆሚያ የእግረኛ መንገድ ወይም ኩርባ ቦታ ላይ መደረግ አለባቸው
 • የችርቻሮ ንግዶች የጊዜያዊውን የአጥር መስፈርት ለማሟላት የእራሳቸውን አጥር ማቅረብ አለባቸው (ለኩርባ አካባቢዎች)።
 • ለምሳሌ እንዲሆን፣ እባክዎ ለጊዜያዊ ከቤት ውጭ መሳሪያዎች ፈቃድ ላይ በራሪ ወረቀታችንን ይመልከቱ። 
 • ያለ ተጨማሪ SDOT ግምገማ ሊጠቀሙባቸው በሚችሉ የሚፈቀዱ መጠለያዎች እና የቤት ዕቃዎች ላይ ዝርዝር መረጃዎችን የያዘ የአየር ሁኔታ ጥበቃ መመሪያን አሳትመናል።
 • እባክዎን የሲያትል የእሳት አደጋ መከላከያ መምሪያ (Seattle Fire Department)፣ የሲያትል የግንባታ እና ቁጥጥር መምሪያ (Seattle Department of Construction and Inspections)፣ እና የሲያትል የአከባቢ ታሪካዊ/የመሬት አቀማማጥ (Seattle Department of Neighborhood Historic/Landmark)ማረጋገጫዎች አሁንም አስፈላጊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይወቁ፣ እንዲሁም እነዚያ ኤጀንሲዎች እርስዎ ያቀረቡት ሀሳብ ላይ ተጽኖ ማምጣት የሚችሉ ተጨማሪ ሕጎች ሊኖራቸው ይችላል።
 • በሕዝብ ላይ አደጋ ሊያስከትሉ በሚችሉ አውሎ ነፋሶች ወይም ከፍተኛ ነፋሶች ወቅት ማውረድን ጨምሮ ለሁሉም መሳሪያዎች እርስዎ ኃላፊነት አለብዎት
 • ከተማው ለመሳሪያው መጎዳት፣ መሰረቅ፣ ወይም አላግባብ ጥቅም ላይ መዋል ኃላፊነት የለበትም
 • ጊዜያዊ የሸቀጣ ሸቀጥ ማሳያዎች በዓይነታቸው በነባር የመጫኛ ዞኖች ውስጥ አይጸድቅም፣ ሆኖም በተለየ ሁኔታ ልናይ እንችላለን።
 • ጊዜያዊ የሸቀጣ ሸቀጥ ማሳያዎች በመጓጓዣ መስመሮች (የብስክሌት እና አውቶቢስ መስመሮችን ጨምሮ) ላይ ላይደረጉ ይችላሉ
 • ጊዜያዊ የተፈቀዱ የማሳያ መዋቅሮች ከሥራ ሰዓታት ውጭ በሕዝብ ቦታ ላይ ሊቆዩ ይችላሉ። (ፈቃድ የተሰጠዎት ከሥራ ሰዓቶችዎ ውጭ በሚሠራው የጭነት ዞን ውስጥ ወይም በአርሶ አደሮች የገቢያ ቦታ ውስጥ ከሆነ፣ ይህ ተግባራዊ አይሆንም - እርግጠኛ ካልሆኑ እኛን ያግኙን!)  
 • ድርጅትዎ በተወሰነ ታሪካዊ ዲስትሪክት ውስጥ የሚገኝ ከሆነ፣ ፈቃዱ ከመሰጠቱ በፊት ከታሪካዊው ዲስትሪክት ማረጋገጫ ማግኘት አለብዎት፣ ሆኖም ሠነዶችዎን ወደነሱ ስለምንልክ በተናጠል (ለብቻው) ማመልከት አያስፈልግዎትም።
 • ይህ ፈቃድ ውጭ ላይ በተፈቀደልዎት አካባቢ ውስጥ ሽያጭ እንዲከናወን የሚፈቅድ ነው
 • እንዲሁም በጊዜያዊነት ጎዳናዎን ለተሽከርካሪ ትራፊክ ለመዝጋት ፈቃዶችን እናቀርባለን። እርስዎ እና በእርስዎ ብሎክ (መስመር) ያሉ ሌሎች የንግድ ስራዎች ለዚህ ፈቃድ ፍላጎት ካላችሁ፣ እባክዎን የእኛን ጊዜያዊ የመንገድ መዝጋት አስተማማኝ ጅምር ገጻ ይመልከቱ።

ለህብረተሰብ የማሳወቅ መስፈርቶች

ፈቃዳችንን በፍጥነት ለማውጣት ለአዳዲስ ጊዜያዊ የቤት ውጪ ማሳያያዎች የተለመደው ሁለት-ሳምንት የይፋዊ አስተያየት ጊዜ አንጠይቅም። ይልቁንም፣ አመልካቾች ስራ ከመጀመራቸው ቢያንስ 2 ቀናት በፊት የታቀደውን ጊዜያዊ ማሳያ በአቅራቢያው ለሚገኙ ነዋሪዎች እና ንግድ ቤቶች ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል። ይህንን የህብረተሰብ ማሳወቂያ በራሪ ጽሁፍ ቴምፕሌት ይጠቀሙ።

መሙላት፣ ማተም፣ እና ማሰራጨት የሚችሉት የህብረተሰብ ማሳወቂያ በራሪ ወረቀትን ያውርዱ!

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

206-684-7623 ላይ ያነጋግሩን። የትርጉም አገልግሎቶች በነጻ ይገኛሉ!

ማመልከቻዎ ሁሉንም የሚፈለጉ ሠነዶችን ያጠቃለለ መሆኑን ያረጋግጡ፡
 • የፈቃድ ወይም የማረጋገጫ ደብዳቤ:የድርጅቱ ወይም ንብረቱ ባለቤት ካልሆኑ የተፈረመ የፈቃድ ደብዳቤ ይጫኑ
የሳይት ፕላን ዓይነቶች:
የቦታ ፕላን ሳይኖር ማመልከቻዎን ልናይ አንችልም። ይህ መጠቀም የፈለጉትን የቦታ ልኬት እና ትክክለኛ መገኛውን ያሳያል። ከመጫንዎ በፊት ፕላንዎን ለማዘጋጀት ከሚከተሉት መንገዶች አንዱን መምረጥ ይችላሉ።
አማራጭ 1፡ ፎቶግራፍ ላይ የተመሠረተ ፕላን (የሚመከር!)
 • ከዚህ በታች ያሉትን ልዩ መመሪያዎችን የሚከተሉ 3 ፎቶግራፎችን በመጠቀም በፎቶግራፍ ላይ የተመሠረተ ፕላን ያዘጋጁ
 • ሁሉም 3 ፎቶግራፎች ሳይት ፕላንዎን እንዲሸፍኑ ይጠበቃል። ከፎቶግራፍዎችዎ ውስጥ አንዱ በሳይት ፕላን ዝርዝር ውስጥ በይበልጥ ከታች የተገለጹትን አስፈላጊ ልኬቶች ማሳየት አለበት።
 • በፎቶግራፍ የቦታውን ማሳያ በድጅታል ለማሳየት የሚክበድዎት መሆኑን ካገኙ፣ እባክዎ የታቀደውን የማሳያ ጠርዞች ወይም ሙሉ ንድፍ በቀጥታ በእግረኛ መንገዱ ወይም በጎዳናው ላይ ክር ወይም ቾክ በመጠቀም “ይሳሉ”። ፎቶዎችን ከማንሳትዎ በፊት ይህንን ያድርጉ!
  • ፎቶ #1: ከታቀደው የሽያጭ ወይም የማሳያ ቦታ 10 ጫማ ያህል በመራቅ የታቀደውን የቦታ ማሳያ ፎቶ ያንሱ። ጠርዞቹን አስቀድመው ምልክት አድርገውበት ከሆነ፣ በፎቶው ውስጥ ያስገቡ፣ እንዲሁም መገኛውን ለመለየት እንዲረዳ የተወሰኑ ከጀርባ ያሉትንም ያስገቡ!
  • ፎቶ #2: የታቀደውን የማሳያ ቦታ በሌላኛው አቅጣጫ ተመሣሣይ ፎቶ ያንሱ።
  • ፎቶ #3: የቢዝነስዎን ሙሉ ህንጻ ፊት ለፊት እና የቦታውን ጠርዞች ጨምሮ የሚያሳይ ፎቶ ያንሱ።
 • ከፎቶዎቹ አንዱን ይምረጡ እና ሁሉንም ተፈላጊ ልኬት ለማጠቃለል ምልክት ያድርጉበት። ይህንን በዲጅታል መስራት ይችላሉ፣ ወይም ፎቶውን በማተም (በማጠብ) በእጅ ምልክት ያድርጉበት።
መደበኛውን ሳይት ፕላን ያስገቡ (የዕቅድ ቴምፕሌት እዚህ ሊያገኙ ይችላሉ)። መደበኛ ሳይት ፕላን እንዴት እንደሚዘጋጅ ስልጠና ለማግኘት እባክዎ በስልክ ቁጥር 206-684-7623 ይደውሉልን።
 • የሳይት ፕላን ዝርዝሮች:ሳይት ፕላዎን በሚያዘጋጁበት ጊዜ፣ ከታች የተዘረዘሩትን ሁሉንም መረጃ ማጠቃለል አለበት። ከዚህ መረጃ ውጪ፣ ማመልከቻዎን ለማየት እና ለማጽደቅ ረጅም ጊዜ ልወስድብን ይችላል። ለዚህም የርዝመት መለኪያ ሜትር ማግኘት እና በፕላንዎ ላይ በግልጽ ማሳየት ያስፈልግዎታል፡
 • የማሳያ ቦታ ልኬቶች፡የታቀደውን ከቤት ውጭ ማሳያ አካባቢ ርዝመት እና ስፋት ያሳዩ። በእግረኛ መንገድ ባለው “ፈርኒቸር ዞን” ውስጥ ባለ ቦታ ላይ ካቀዱ፣ ከእግረኛ መንገድ (ጠርዝ) ጀምሮ የታቀደው ማሳያ ቦታ ያለውን ልኬት ማሳየት አለብዎት። በመንገዱ ጠርዝ እና ጊዘያዊ የማሳያ ቦታዎት ከሚጀምርበት ቦታ መካከል ቢያንስ 4’ እንዶኖር ያስፈልግዎታል። 
 • የእግረኛ ነጻ ዞን፥ እግረኞች በእግረኛ መንገዱ ላይ እንዴት መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ለማሳየት ከማሳያ ቦታው ቀጥሎ ያለውን የእግረኛ መንገድ ስፋት ያሳዩ። በአብዛኛው ሰፈር ውስጥ የሚያስፈልገው ዝቅተኛው yeእግረኛ ነጻ ዞን 6 ጫማ ነው (በአንዳንድ የከተማ አካባቢዎች የሚፈለገው ዝቅተኛ ስፋት 8 ጫማ ነው።
  • ማስታወሻ፥ዝቅተኛውን ነጻ ዞን ለማስጠበቅ በቂ ቦታ ከሌለ፣ ለዚህ ፈቃድ ብቁ ላይሆኑ ይችላሉ። 
 • ከሌሎች ቋሚ ነገሮች የሚኖር እርቀት፥ የእግረኛ መንገዱ እንደ የመብራት ምሶሶ፣ ዛፎች፣ የመኪና ማቆሚያ ሜትሮች፣ የውሃ መሳቢያ ቧንቧዎች፣ እና የብስክሌት ማቆሚያዎች ያሉ ሌሎች ቁሶችን ሊጨምር ይችላል። እባክዎ ከእነዚህ ቁሶች እስከ የቦታዎ ማሳያ ጠርዝ ድረስ ያለውን ርቀት ይስፈሩና እነኚህን ልኬቶች በፕላንዎ ውስጥ ያካትቱ።
የጠርዝ ቦታ መለያ ቁጥሮች፥ በሚከፈልበት የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ላይ የሽያጭ ለመስራት/ማሳያ መጠቀም ካቀዱ፣ እባክዎ የጠርዝ ቦታውን መለያ ቁጥር(ሮች) ያቅርቡ (ቁጥሮቹን ለማግኘት ይህን ካርታ ይጠቀሙ)።
  1. የቦታው ማሳያ ልኬቶች
  2. የእግረኛ ነጻ ዞን ልኬቶች
  3. ከሌሎች ቋሚ ነገሮች የሚኖር እርቀት
  1. ጊዜያዊ የመጠቀሚያ ቦታ 4 ጫማ ስፋት በ 14 ጫማ ርዝመት
  2. ጊዜያዊ የመጠቀሚያ ቦታ 7 ጫማ ስፋት በ 28 ጫማ ርዝመት
  1. የእግረኛ ዞን 10 ጫማ ስፋት
  2. የእግረኛ ነጻ ዞን 6 ጫማ ስፋት
  1. የኃይል ምሶሶ ከኩርባ /ጠርዝ/ አካባቢ 8 ጫማ
  2. የመብራት ምሶሶ፣ አትክልቶች፣ እና ዛፎች ከኩርባ በግምት 18’’ እርቀት ላይ መሆን አለባቸው

መግለጫ፥ ከሚያስፈልጉ ልኬቶች ጋር የሳይት ፕላን ምሳሌ ፎቶግራፍ 

መዋቅራዊ ዝርዝሮች: ለሁሉም የጠርዝ ቦታ ላይ ማሳያዎች ቦታዎች አጥር ያስፈልጋል
 • በዚህ ላይ እንዲሁም ለማሳያው የሚጠቀሙትን ማናቸውም መሳሪያዎች ወይም አቅርቦቶች ላይ ዝርዝሮች እንፈልጋለን
  • ልኬቶችን፣ ስዕል ወይም ፎቶ፣ ወይም የአጥር መስሪያ ዕቃዎች መግለጫን ጨምሮ በጠርዝ አካባቢዎች የማሳያዎች የአጥር መግለጫ።
  • የማሳያ መሳሪያዎች ዝርዝር ከመግለጫቸው ጋር (ለምሳሌ፣ 4'x 6' ጠረጴዛ ከጠረጴዛ ልብስ ጋር እና ሸቀጣ ሸቀጥ ለሽያጭ፤ 3’ ርዝመት x 2’ ስፋት x 5’ ከፈታ ያለው የብረት የልብስ መደርደሪያ፤ 2 የእንጨት ወንበር ለሽያጭ ሰራተኞች፤ 3’ ርዝመት x 18” ስፋት x 5’ ከፍታ ያለው የእንጨት ማሳያ መደርደሪያ)።
 • በታሪካዊ ዲስትሪክቶች ውስጥ የሚገኙ ከሆኑ፣ ከሳይት ፕላንዎ ጋር ለመጠቀም ያቀዱትን የሁሉም ፈርኒቸር፣ የዋና አቅራቢዎች፣ አትክልት የሚተከልባቸውን፣ የአጥር፣ ወይም ሌሎች ዓይነቶችን ቀለም እና አጨራረስ የሚያሳይ ሰነድ(ዶች)ይጫኑ።
 • ፎቶዎች፣ ከድረ-ገጾች የተገኙ ምስሎች፣ ወይም ካታሎግ የተቆረጡ ወረቀቶች በከለር (በቀለም) እስከሆነ ድረስ ተቀባይነት አላቸው። ይህንን መረጃ ለታሪካዊ ዲስትሪክት ሰራተኛ እንዲያዩት እንልካለን፤ ለማጽደቂያ የምስክር ወረቀት እርስዎ በተናጥል ለእነርሱ ማስገባት አይጠበቅብዎትም።
  • ማስታወሻ፥ የተፈቀደውን ቦታ ለመግለፅ ከሚጠቀሙባቸው የአጥር እና የትራፊክ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች በስተቀር፣ ብዙ ደማቅ ያልሆኑ ቀለሞች፣ እንደ ግራጫ/ጥቁር አረንጓዴ ወይም ተመሳሳይ ለማንኛውም የቤት ዕቃዎች፣ አጥር፣ ወይም ለሚለጠፉ ነገሮች ይመከራሉ።
ቀጣዩ ነገር ምንድን ነው? አንድ ጊዜ ለአስተማማኝ ጊዜያዊ የሽያጭ ማስጀመሪያ ፈቃድ ማመልከቻዎትን ካስገቡ፣ ስራውን ለመጀመር ለመዘጋጀት መውሰድ ያለብዎ የተወሰኑ ተጨማሪ እርምጃዎች እዚህ አሉ!
 • በጠርዝ ላይ ያለን ቦታ ለመጠቀም ካቀዱ፣ ከቡድናችን ከሚሰጠው ፈቃድ በተጨማሪ፣ በጊዜያዊነት መኪና ማቆምን የሚከለክል ፈቃዶችን ለማግኘት ማመልከት ያስፈልግዎታል። ለዚህ ፈቃድ ለማመልከት እንድናግዝዎ እባክዎ በስልክ ቁጥር (206) 684-7623 ይደውሉልን።
 • አዲሱን ስራ ከመጀመርዎ ቢያንስ ከሁለት ቀን በፊት በህዝብ ቦታው ላይ ለመስራት ስላሰቡት ነገር ለጎረቤቶች ያሳውቁ። ይህንን የህብረተሰብ ማሳወቂያ በራሪ ጽሁፍ ቴምፕሌት ይጠቀሙ።
 • የከተማዋን መስፈርቶች ያሟላ ኢንሹራንስ መያዝዎን ያረጋግጡ።
ጠቃሚ ሆኖ ሊያገኙት የሚችሉትን የከቤት ውጭ መሳሪያ አማራጮች መመሪያ ከታች ባለው ሊንክ ይከተሉ።

ደህንነቱ የተጠበቀ ጊዜያዊ የሽያጭ ማስጀመሪያ ፈቃዶች 

አዳዲስ ሳይቶችን ለመሞከር ለሻጮች የበለጠ ተለዋዋጭነትን ለመስጠት ፣ ጊዜያዊ የሽያጭ ፈቃድ እስከ ኦክቶበር 31, 2021 ድረስ እናቀርባለን። ይህ አማራጭ በሽያጭ ተሽከርካሪ ላይ ወይም በጋሪ በመንገድ ጠርዝ፣ በእግረኛ መሄጃ፣ ወይም ፕላዛ አካባቢዎች ላይ ምግብ፣ አበባዎችን፣ ወይም ህትመቶችን ለመሸጥ የቀረበ ነው። 

ማመልከት የሚችለው ማን ነው?

 • ማንኛውም ብቁ የሆነ የምግብ፣ አበባ፣ ወይም ህትመት ሻጭ 

ማወቅ ያለብዎት ነገር፥ 

 • ጊዜያዊ የምግብ ሽያጭ የምግብ አገልግሎት ንግድ ካለበት በ 50 ጫማ ርቀት ውስጥ እና ጊዜያዊ የአበባ ሽያጭ የአበባ አግልግሎት ንግድ ካለበት በ 50 ጫማ ርቀት ውስጥ መደረግ አይችልም (የንግድ ቤቶቹ ድጋፍ ካለ በስተቀር) 
 • ጊዜያዊ መሸጫ ቀጥሎ ያለው ንግድ ቤት ለመጠቀም ያቀደበት ጠርዝ ቦታ ላይ ሊደረግ አይችልም (ለጠርዝ ቦታ አካባቢዎች) 
 • ጊዜያዊ መሸጫ በነባር መጫኛ ዞኖች ውስጥ ሊኖር አይችልም (ለጠርዝ ቦታ አካባቢዎች) 
 • በዚህ የፍቃድ ዓይነት ከሁለት በላይ ሻጮችን በአንድ ብሎክ እንፈቅዳለን 

ለህብረተሰብ የማሳወቅ መስፈርቶች 

የእኛን ፈቃድ በፍጥነት ለመስጠት፣ መደበኛውን የሁለት-ሳምንት የህብረተሰብ አስተያየት ጊዜን ለአዲስ ጊዜያዊ የሽያጭ ቦታዎች እንደ መስፈርት አናስቀምጥም። ይልቁንም፣ አመልካቾች ስራ ከመጀመራቸው ቢያንስ 2 ቀናት በፊት የታቀደውን የሽያጭ ቦታ በአቅራቢያው ለሚገኙ ነዋሪዎች እና ንግድ ቤቶች ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል።

መሙላት፣ ማተም፣ እና ማሰራጨት የሚችሉት የህብረተሰብ ማሳወቂያ በራሪ ወረቀትን ያውርዱ! 

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

206-684-7623 ላይ ያነጋግሩን። የትርጉም አገልግሎቶች በነጻ ይገኛሉ!
ማመልከቻዎ ሁሉንም የሚፈለጉ ሠነዶችን ያጠቃለለ መሆኑን ያረጋግጡ፡
 • የ King County የህብረተሰብ ጤና መምሪያ ተንቀሳቃሽ የምግብ ክፍል ፈቃድ ወይም ነጻ የተደረጉ ከሆነ ይግለጹ (ከ 2020 መጀመሪያ ጀምሮ ጊዜያቸው ያበቃ ፈቃዶች ተቀባይነት አላቸው)  
 • ክፍት ነበልባል ወይም ፈሳሽ ነዳጅ (የፔትሮሊዬም ጋዝ) (LPG) የሚጠቀሙ ከሆነ ወይም ፈቃዱ በህደት ላይ ያለ ከሆነ፣ የሲያትል (Seattle) የእሳት ማርሻል ፈቃድ  
 • የሲያትል የንግድ ፈቃድ 
 • ከተሽከርካሪ ላይ የሚሸጡ ከሆነ፣ የተሽከርካሪዎ ሠሌዳ ቁጥር ፈቃድ

የሳይት ፕላን እና ተያያዥ ዝርዝሮች (ከታች ይመልከቱ)

የሳይት ፕላን ዓይነቶች:የቦታ ፕላን ሳይኖር ማመልከቻዎን ልናይ አንችልም።

ይህ መጠቀም የፈለጉትን የቦታ ልኬት እና ትክክለኛ መገኛውን ያሳያል። ከመጫንዎ በፊት ፕላንዎን ለማዘጋጀት ከሚከተሉት መንገዶች አንዱን መምረጥ ይችላሉ።

አማራጭ 1፡ ፎቶግራፍ ላይ የተመሠረተ ፕላን (የሚመከር!)

 • ከዚህ በታች ያሉትን ልዩ መመሪያዎችን በመከተል 3 ፎቶግራፎችን በመጠቀም በፎቶግራፍ ላይ የተመሠረተ ፕላን ያዘጋጁ 
 • ሁሉም 3 ፎቶግራፎች ሳይት ፕላንዎን እንዲሸፍኑ ይጠበቃል። ከፎቶግራፍዎችዎ ውስጥ አንዱ በሳይት ፕላን ዝርዝር ውስጥ በይበልጥ ከታች የተገለጹትን አስፈላጊ ልኬቶች ማሳየት አለበት።
 • በፎቶግራፍ የቦታውን ማሳያ በድጅታል ለማሳየት የሚክበድዎት መሆኑን ካገኙ፣ እባክዎ የታቀደውን የማሳያ አከባቢ ጠርዞች ወይም ሙሉ ንድፍ በቀጥታ በእግረኛ መንገዱ ወይም በጎዳናው ላይ ክር ወይም ቾክ በመጠቀም “ይሳሉ”። ፎቶዎችን ከማንሳትዎ በፊት ይህንን ያድርጉ! 
 • ፎቶ #1: ከታቀደው የሽያጭ ቦታ 10 ጫማ ያህል በመራቅ የታቀደውን የቦታ ማሳያ ፎቶ ያንሱ።
 • ጠርዞቹን አስቀድመው ምልክት አድርገውበት ከሆነ፣ በፎቶው ውስጥ ያስገቡ፣ እንዲሁም መገኛውን ለመለየት እንዲረዳ የተወሰኑ ከጀርባ ያሉትንም ያስገቡ! 
 • ፎቶ #2: የታቀደውን የሽያጭ ቦታ በሌላኛው አቅጣጫ ተመሣሣይ ፎቶ ያንሱ። 
 • ፎቶ #3: ቀጥሎ ያለውን የህንጻ ፊት ለፊት እና የቦታውን ጠርዞች ጨምሮ የሚያሳይ ከመንገድ አቅጣጫ ያለውን የሽያጭ ቦታዎን ከፊት ለፊት ፎቶ ያንሱ። 
 • ከፎቶዎቹ አንዱን ይምረጡ እና ሁሉንም ተፈላጊ ልኬት ለማጠቃለል ምልክት ያድርጉበት። ይህንን በዲጅታል መስራት ይችላሉ፣ ወይም ፎቶውን በማተም (በማጠብ) በእጅ ምልክት ያድርጉበት።  

አማራጭ 2፡ መደበኛ ሳይት ፕላን

 • መደበኛውን ሳይት ፕላን ያዘጋጁ (የዕቅድ ንድፍ መመሪያ  እዚህ ይገኛል)። መደበኛ ሳይት ፕላን እንዴት እንደሚዘጋጅ ስልጠና ለማግኘት እባክዎ በስልክ ቁጥር 206-684-7623 ይደውሉልን።
 • የሳይት ፕላን ዝርዝሮች:ሳይት ፕላዎን በሚያዘጋጁበት ጊዜ፣ ከታች የተዘረዘሩትን ሁሉንም መረጃ ማጠቃለል አለበት።
 • ከዚህ መረጃ ውጪ፣ ማመልከቻዎን ለማየት እና ለማጽደቅ ረጅም ጊዜ ልወስድብን ይችላል። ለዚህም የርዝመት መለኪያ ሜትር ማግኘት እና በፕላንዎ ላይ በግልጽ ማሳየት ያስፈልግዎታል፡ 
 • የማሳያ ቦታ ልኬቶች፡ የታቀደውን የሽያጭ ቦታ ርዝመት እና ስፋት ያሳዩ (ወይም ለተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ ልኬቶች)።
 • በእግረኛ መንገድ ውስጥ ባለው "ፈርኒቸር ዞን" ውስጥ የሽያጭ ጋሪ ለመጠቀም ካቀዱ፣ ከእግረኛ መንገድ (ጠርዝ) ጀምሮ የታቀደው የሽያጭ አካባቢ ዳር ያለውን ልኬት ማሳየት አለብዎት።
 • በመንገዱ ጠርዝ እና ጊዘያዊ የሽያጭ ቦታዎት ከሚጀምርበት ቦታ መካከል ቢያንስ 4’ እንዶኖር ያስፈልግዎታል። 
 • የእግረኛ ነጻ ዞን፥በእግረኛ መንገድ ላይ ለመሸጥ ካቀዱ፣ እግረኞች በእግረኛ መንገዱ ላይ እንዴት መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ለማሳየት ከቤት ውጭ የሽያጭ አካባቢ ማሳያ ቦታ ቀጥሎ ያለውን የእግረኛ መንገድ ስፋት ያሳዩ።
 • በአብዛኛው ሰፈር ውስጥ የሚያስፈልገው ዝቅተኛው የእግረኛ ነጻ ዞን 6 ጫማ ነው (በአንዳንድ የከተማ አካባቢዎች የሚፈለገው ዝቅተኛ ስፋት 8 ጫማ ነው)። 
 • ማስታወሻ፥ ዝቅተኛውን ነጻ ዞን ለማስጠበቅ በቂ ቦታ ከሌለ፣ ለዚህ ፈቃድ ብቁ ላይሆኑ ይችላሉ። 
 • ከሌሎች ቋሚ ነገሮች የሚኖር እርቀት፥የእግረኛ መንገዱ እንደ የመብራት ምሶሶ፣ ዛፎች፣ የመኪና ማቆሚያ ሜትሮች፣ የውሃ መሳቢያ ቧንቧዎች፣ እና የብስክሌት ማቆሚያዎች ያሉ ሌሎች ቁሶችን ሊጨምር ይችላል።
 • እባክዎ ከእነዚህ ቁሶች እስከ የቦታዎ ማሳያ ጠርዝ ድረስ ያለውን ርቀት ይስፈሩና እነኚህን ልኬቶች በፕላንዎ ውስጥ ያካትቱ። 
የጠርዝ ቦታ መለያ ቁጥሮች፥ 

ክፍያ በሚከፈልበት የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ውስጥ ሽያጭ ለመስራት ካቀዱ፣ እባክዎ የጠርዝ ቦታውን መለያ ቁጥር(ሮች) ያቅርቡ (ቁጥሮቹን ለማግኘት ይህን ካርታ ይጠቀሙ )።

 1. የቦታው ማሳያ ልኬቶች
 2. የእግረኛ ነጻ ዞን ልኬቶች
 3. ከሌሎች ቋሚ ቁሶች የሚኖር እርቀት

 1. ጊዜያዊ የመጠቀሚያ ቦታ 7 ጫማ ስፋት በ 28 ጫማ ርዝመት
 2. ጊዜያዊ የመጠቀሚያ ቦታ 4 ጫማ ስፋት በ 14 ጫማ ርዝመት
 3. የእግረኛ ነጻ ዞን 6 ጫማ ስፋት
 4. የእግረኛ ዞን 10 ጫማ ስፋት
 5. የኃይል ምሶሶ ከኩርባ /ጠርዝ/ አካባቢ 8 ጫማ
 6. የመብራት ምሶሶ፣ አትክልቶች፣ እና ዛፎች ከኩርባ በግምት 18’’ እርቀት ላይ መሆን አለባቸው

መግለጫ፥ ከሚያስፈልጉ ልኬቶች ጋር የሳይት ፕላን ምሳሌ ፎቶግራፍ 

የአጥር አስተጣጠር ዝርዝሮች: 

በኩርባ ቦታዎች ለሁሉም የጋሪ ሻጮች አጥር ያስፈልጋል። በአጥር አስተጣጠር ላይ የሚከተሉትን ዝርዝር ነገሮች እንፈልጋለን። 

የአጥር አስተጣጠር መግለጫ፣ ልኬቶችን ጨምሮ፣ ስዕል ወይም ፎቶ፣ ወይም የአጥር መስሪያ ዕቃዎች መግለጫ።  አጥሩ ከ 30” እስከ 42” የሆነ ከፍታ የለው መሆን አለበት።

ቀጣዩ ነገር ምንድን ነው? አንድ ጊዜ ለአስተማማኝ ጊዜያዊ የሽያጭ ማስጀመሪያ ፈቃድ ማመልከቻዎትን ካስገቡ፣ ስራውን ለመጀመር ለመዘጋጀት መውሰድ ያለብዎ የተወሰኑ ተጨማሪ እርምጃዎች እዚህ አሉ!  
 • በጠርዝ ላይ ያለን ቦታ ለመጠቀም ካቀዱ፣ ከቡድናችን ከሚሰጠው ፈቃድ በተጨማሪ፣ በጊዜያዊነት መኪና ማቆምን የሚከለክል ፈቃዶችን ለማግኘት ማመልከት ያስፈልግዎታል። ለዚህ ፈቃድ ለማመልከት እንድናግዝዎ እባክዎ በስልክ ቁጥር (206) 684-7623 ይደውሉልን።
 • በሚያመለክቱበት ጊዜ፣ የጠቅላላ መረጃ ክፍል አለ እናም ለማመልከቻዎ “ምክንያት” ሊመርጡ ይችላሉ። ጥያቄዎ መፍጠን ያለበት መሆኑን እንድናውቅ “ሌላ” የሚለውን በመምረጥ “አስተማማኝ ጊዜያዊ የሽያጭ መጀመር ፈቃድ” ብለው ይጻፉ። 
 • የተዘጋጀው ይፋዊ ማስታወቂያ ከባሪኬድ ኩባንያ መግዛት ወይም መከራየት በሚችሉት መኪና ማቆም አይቻልም የሚሉ ባሪኬዶች (T-39 ምልክቶች) ላይ መለጠፍ ያስፈልጋል።
 • ለማስተካከል ካቀዱበት 72 ሰዓታት በፊት ባሪኬዶቹን እንዲያኖሩ እንመክራለን፣ ነገር ግን ተፈጻሚ እንዲሆን ቢያንስ 24 ሰዓታት ቀድሞ ሊቀመጡ ይገባል።
 • አዲሱን ስራ ከመጀመርዎ ቢያንስ ከሁለት ቀን በፊት በህዝብ ቦታው ላይ ለመስራት ስላሰቡት ነገር ለጎረቤቶች ያሳውቁ። ይህንን የህብረተሰብ ማሳወቂያ በራሪ ጽሁፍ ቴምፕሌት ይጠቀሙ።
 • የከተማዋን መስፈርቶች ያሟላ ኢንሹራንስ መያዝዎን ያረጋግጡ። 

የጊዜያዊ የመንገድ መዝጋት በአስተማማኝ ሁኔታ ማስጀመር (Safe Start)

ነባር የንግዶች ድርጅቶች ወይም ድርጅቶች በጋራ በመጣመር ለንግድ ተግባራት እና ለእግረኞች እንቅስቃሴ ተጨማሪ ቦታ እንዲኖር ለማድረግ ለጊዜያዊ የጎዳና መዘጋት ፈቃድ ለማመልከት ይችላሉ። 

ከመጀመርዎ በፊት…

ከማመልከትዎ በፊት ለቅድመ-ማመልቻ ስልጠና ቀጠሮ እንዲታስይዙ እናበረታታዎታለን። ዕቅድዎን ለመረዳት እና የሚቻል ስለመሆኑ ለወመሰን እና፣ አስፈላጊ ከሆነ፣ አማራጮችን ለማቅረብ ከእርስዎ ጋር መስራት እንችላለን። ለመጀመር፣ በ publicspace@seattle.gov ኢሜይል ይላኩልን። 

ማወቅ ያለብዎት ነገር 

አንዳንድ ጎዳናዎች እንደገና ለማየት እና ለማጽደቅ ለእኛ ቀላል እና ፈጣን ይሆናሉ። ምሳሌዎች የሚያካትቱት፡ 

 • የውስጥ ለውስጥ መንገዶች 
 • አውቶቢስ የማይሄድባቸው ጎዳናዎች 
 • ነጠላ ብሎክ (የሚዘጋ መስቀለኛ መንገድ የሌለው) 
 • አንዳንድ ጎዳናዎችን ከሚሰጡት የትራንስፖርት አገልግሎት የተነሳ መዝጋት አይቻልም።
 • በመስመሩ/ብሎኩ ውስጥ ሰዎች መንቀሳቀስ እንዲችሉ የእግረኛ መንገዶች ክፍት ሆነው መቀጠል ይኖርባቸዋል፤ ጎዳናው ብቻ ይዘጋል። 
 • ባለ 20 ጫማ የእሳት አደጋ መስመር በማንኛውም ጊዜ ክፍት መሆን አለበት። ይህ የእሳት አደጋ መስመር በቀላሉ የሚንቀሳቀሱ ቁሳቁሶች (ቀላል ጠረጴዛዎች እና ወንበሮች) ሊኖሩበት ይችላል፣ ሆኖም እንደ ድንኳኖች ወይም ከባድ የፒክኒክ ጠረጴዛዎች ያሉ በቀላሉ የማይንቀሳቀሱ ማናቸውም ትላልቅ ነገሮች በባለ 20 ጫማ የእሳት አደጋ መኪና መንገድ/መስመር ውስጥ አይፈቀዱም። 
 • የጎዳና መዘጋት ለነባር የብሎኬት (ጡብ) እና የሃርማታ (ከአሸዋ ጋር የተቦካ ሲሚንቶ) ንግዶች እና በተዘጋው ጎዳና አከባቢ ውስጥ ለተፈቀደላቸው ነጋዴዎች የታሰበ ነው።
 • መዝጋት በአካባቢው ለሚዘዋወሩ ሰዎች ተጨማሪ ቦታ እንዲኖር ለማድረግ እና ተጨማሪ የንግድ እንቅስቃሴ ቦታን ለመጨመር ነው። እነዚህ ለዝጅግቶች ወይም ለህዝብ መሰብሰብ የታሰቡ አይደሉም. 
 • መዝጊያዎች በተለያዩ ሁኔታዎች፣ ሙሉ መዘጋት (ሙሉ የመንገድ ክፍል መዝጋት)፣ በግማሽ መዘጋት (የመኪና ማቆሚያ/የጉዞ መንገዶች በአንድ አቅጣጫ መዝጋት፣ በሌላኛው አቅጣጫ ያለው ለትራፊክ ሲፈቀድ)፣ ወዘተ ጨምሮ ሊታቀዱ ይችላሉ።
 • ድንኳኖች፣ ጣራዎች፣ እና ማሞቂያዎች ከሲያትል የእሳት አደጋ መከላከያ መምሪያ የተለየ ማረጋገጫ ሊፈልጉ ይችላሉ። 

ለንግድ ስራዎች ጎዳናዎትን ለመዝጋት ይፈልጋሉ? 

 1. ከጎረቤቶችዎ ጋር ይቀናጁ እና ድጋፍ ይሰብስቡ 
 2. በህዝብ መንገድ የመጠቀም መብት ውስጥ መጠቀም የፈለጉት ቦታ ምን እንደሆነ እና እንዴት ሊጠቀሙበት እንደፈለጉ በጋራ ይወስኑ፤ በማመልከቻዎ ውስጥ ይህንን ለእኛ መግለጽ ያስፈልግዎታል 
 3. ለቅድመ-ማመልከቻ ስልጠና እኛን ያግኙን፡ በ publicspace@seattle.gov ኢሜይል ይላኩ እና የስልክ ቁጥርዎን ይስጡን 
 4. ከማንኛውም ተጽዕኖ የተፈጠረበት ከዋናው መንገድ ወደ ግለሰብ ቤት የሚስደው መንገድ ባለቤት ኢሜይል ወይም የድጋፍ ደብዳቤ ያግኙ 
 5. የታቀደውን ማመልከቻ የሚዘጋው መንገድ አካባቢ ላሉት ሁሉም የድርጅት ባለቤቶች እና የንብረት ባለቤቶች/ሥራ አስኪያጆች ያሳውቁ። በዚህ ላይ እርስዎን ለመርዳት ይፋዊ የማሳወቂያ ቴምፕሌት አዘጋጅተናል!
 6. ማስታወቂያው በ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ጎረቤቶችዎ እርስዎን ወይም SDOT ን ስላላቸው አስተያየት እንዲያነጋግሩ ያሳውቃል። አብዛኛዎቹ ጎረቤቶች ዕቅድዎትን እንደሚደግፉ የሚያሳይ ማስረጃ እንፈልጋለን፣ ይህም ያቀዱትን እንዲያገኙ ይረዳዎታል። የጎረቤት ድጋፍን ይህንን ቅጽ በመጠቀም በሠነድ ማቅረብ ይችላሉ.
 7. በኦንላይን ያመልክቱ! 

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

206-684-7623 ላይ ያነጋግሩን። የትርጉም አገልግሎቶች በነጻ ይገኛሉ!
ማመልከቻዎ ሁሉንም አስፈላጊ ሠነዶች ማካተቱን ያረጋግጡ፤ እነዚህ ወደ ማመልከቻዎ መጫን አለባቸው፡
 • የሁሉም ተሳታፊ ቢዝነሶች እና ድርጅቶች ዝርዝር 
 • ከጎረቤቶችዎ የሰሙት ማጠቃለያ፤ ቅጻችንን መጠቀም ይችላሉ 
 • እንደ የማመልከቻዎ አካል የጎረቤቶችዎን የድጋፍ ኢሜል/ደብዳቤ፣ አመልካቹ እራሱ ካልሆነ በስተቀር፣ ተጽዕኖ የተፈጠረበት ከዋናው መንገድ ወደ ግለሰብ ቤት የሚስደው መንገድ ባለቤት(ቶች) እና የንግድ ማሻሻይ ህብረት (BIA) ጨምሮ
 • የድንኳኖች/ጣሪያዎች/አጥሮች/ማሞቂያዎች ዝርዝር። ፎቶዎች፣ ከድረ-ገጾች የተገኙ ምስሎች፣ ወይም ካታሎግ የተቆረጡ ወረቀቶች በከለር (በቀለም) እስከሆነ ድረስ ተቀባይነት አላቸው።
 • በፕላንዎ ላይ ማየት የምንፈልጋቸውን አንዳንድ ይዘቶች ለመለየት የሚያግዝ የሳይት ፕላን ምሳሌ አለን ።
 • በታሪካዊ ዲስትሪክቶች ውስጥ፣ እባክዎን በሚዘጋው መንገድ አካባቢ የታቀዱ የአጥር፣ የቤት ዕቃ፣ አትክልት የሚተከልባቸውን፣ ወይም ሌሎች ዓይነቶችን ቀለም እና አጨራረስ የሚያሳይ ሰነድ(ዶች)ይጫኑ። ፎቶዎች፣ ከድረ-ገጾች የተገኙ ምስሎች፣ ወይም ካታሎግ የተቆረጡ ወረቀቶች በከለር (በቀለም) እስከሆነ ድረስ ተቀባይነት አላቸው።
 • ተፈቀደውን ቦታ ለመግለፅ ከሚጠቀሙባቸው የአጥር እና የትራፊክ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች በስተቀር፣ ብዙ ደማቅ ያልሆኑ ቀለሞች፣ እንደ ግራጫ/ጥቁር አረንጓዴ ወይም ተመሳሳይ ለማንኛውም የቤት ዕቃዎች፣ አጥር፣ ወይም ለሚለጠፉ ነገሮች ይመከራሉ። 
 • ድርጅትዎ በተወሰነ ታሪካዊ ዲስትሪክት ውስጥ የሚገኝ ከሆነ፣ ፈቃዱ ከመሰጠቱ በፊት ከታሪካዊው ዲስትሪክት ማረጋገጫ ማግኘት አለብዎት፣ ሆኖም ሠነዶችዎን ወደነሱ ስለምንልክ በተናጠል (ለብቻው) ማመልከት አያስፈልግዎትም።  

ጊዜያዊ ከቤት ውጭ የአካል ብቃት ፈቃድ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማስጀመር (Safe Start)

ነባር የስፖርት መስሪያ ጂም እና የአካል ብቃት ስቱዲዮዎች ውጭ ላይ ለማስተማር እና ለአካላዊ ርቀት የበለጠ ቦታን ለመፍጠር የእግረኛን መንገድ ወይም የኩርባ ቦታን ለመጠቀም ነጻ ፈቃድ ለማግኘት ማመልት ይችላሉ። 

ከመጀመርዎ በፊት…

 • ከማመልከትዎ በፊት ለቅድመ-ማመልከቻ ስልጠና ቀጠሮ እንዲታስይዙ እንመክርዎታለን። ዕቅድዎን ለመረዳት እና የሚቻል ስለመሆኑ ለመወሰን እና፣ የሚቻል ከሆነ፣ አማራጮችን ለማቅረብ ከእርስዎ ጋር መስራት እንችላለን።
 • ለመጀመር፣ በ publicspace@seattle.gov ኢሜይል ይላኩልን.

ማወቅ ያለብዎት ነገር

 • የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ከጂም ቤቱ አጠገብ ባለው የመኪና ማቆሚያ የእግረኛ መንገድ ወይም ኩርባ ቦታ ላይ መደረግ አለባቸው
 • ጂሞች የጊዜያዊውን የአጥር መስፈርት ለማሟላት የእራሳቸውን አጥር ማቅረብ አለባቸው (ለኩርባ አካባቢዎች)። ለምሳሌ እንዲሆን እባክዎ ለጊዜያዊ ከቤት ውጭ መሳሪያዎች ፈቃድ ላይ በራሪ
 • ያለ ተጨማሪ SDOT ግምገማ ሊጠቀሙባቸው በሚችሉ መጠለያዎች እና የቤት ዕቃዎች ላይ ዝርዝር መረጃዎችን የያዘ የአየር ሁኔታ ጥበቃ መመሪያንአሳትመናል።
 • እባክዎን የሲያትል የእሳት አደጋ መከላከያ መምሪያ (Seattle Fire Department), የሲያትል የግንባታ እና ቁጥጥር መምሪያ (Seattle Department of Construction and Inspections)፣, እና የሲያትል የአከባቢ ታሪካዊ/የመሬት አቀማማጥ(Seattle Department of Neighborhood Historic/Landmark) ማረጋገጫዎች አሁንም አስፈላጊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይወቁ፣ እንዲሁም እነዚያ ኤጀንሲዎች እርስዎ ያቀረቡት ሀሳብ ላይ ተጽኖ ማምጣት የሚችሉ ተጨማሪ ሕጎች ሊኖራቸው ይችላል።  
 • በሕዝብ ላይ አደጋ ሊያስከትሉ በሚችሉ አውሎ ነፋሶች ወይም ከፍተኛ ነፋሶች ወቅት ማውረድን ጨምሮ ለሁሉም መሳሪያዎች እርስዎ ኃላፊነት አለብዎት
 • ከተማው ለመሳሪያው መጎዳት፣ መሰረቅ፣ ወይም አላግባብ ጥቅም ላይ መዋል ኃላፊነት የለበትም
 • የአካል ብቃት አካባቢዮች በዓይነት በነባር የመጫኛ ዞኖች ውስጥ አይጸድቅም፣ ሆኖም በተለየ ሁኔታ ልናይ እንችላለን።
 • የአካል ብቃት አካባቢዎች በመጓጓዣ መስመሮች (የብስክሌት እና አውቶቢስ መስመሮችን ጨምሮ) ላይ ላይደረጉ ይችላሉ
 • ጊዜያዊ ከቤት ውጭ የአካል ብቃት ፈቃድ አስተማማኝ ጅምር ጋር የተገናኙ መዋቅሮች ከሥራ ሰዓታት ውጭ በሕዝብ ቦታ ላይ ሊሰሩ ይችላሉ። (ፈቃድ የተሰጠዎት ከሥራ ሰዓቶችዎ ውጭ በሚሠራው የጭነት ቀጠና ውስጥ ወይም በአርሶ አደሮች የገቢያ ቦታ ውስጥ ከሆነ፣ ይህ ተግባራዊ አይሆንም - እርግጠኛ ካልሆኑ እኛን ያግኙን!) 
 • የስፖርት ማዘወተሪያ ጅምዎ በተወሰነ ታሪካዊ ዲስትሪክት ውስጥ የሚገኝ ከሆነ፣ ፈቃዱ ከመሰጠቱ በፊት ከታሪካዊው ዲስትሪክት ማረጋገጫ ማግኘት አለብዎት፣ ሆኖም ሠነዶችዎን ወደነሱ ስለምንልክ ለብቻው ማመልከት አያስፈልግዎትም።
 • እንዲሁም በጊዜያዊነት ጎዳናዎን ለተሽከርካሪ ትራፊክ ለመዝጋት ፈቃዶችን እናቀርባለን። እርስዎ እና በእርስዎ ብሎክ (መስመር) ያሉ ሌሎች የንግድ ስራዎች ለዚህ ፈቃድ ፍላጎት ካላችሁ፣ እባክዎን የእኛን ጊዜያዊ የመንገድ መዝጋት አስተማማኝ ጅምር ገጻ ይመልከቱ።

ፈቃድ ለማግኘት ፈልገዋል?

 • በህዝብ መንገድ የመጠቀም መብት ውስጥ መጠቀም የፈለጉት ቦታ ምን እንደሆነ እና እንዴት ሊጠቀሙበት እንደፈለጉ ይወስኑ፤ በማመልከቻዎ ውስጥ ይህንን ለእኛ መግለጽ ያስፈልግዎታል።
 • ለቅድመ-ማመልከቻ ስልጠና እኛን ያግኙን፡ በ publicspace@seattle.gov ኢሜይል ይላኩ እና የስልክ ቁጥርዎን ይስጡን
 • ለማመልከት ዝግጁ ሲሆኑ፣ በ (206) 684-7623 ያግኙን። የትርጉም አገልግሎቶች በነጻ ይገኛሉ!

ለህብረተሰብ የማሳወቅ መስፈርቶች

ይልቁንም፣ አመልካቾች ስራ ከመጀመራቸው ቢያንስ 2 ቀናት በፊት የታቀደውን አካል ብቃት እንቅስቃሴ ቦታ በአቅራቢያው ለሚገኙ ነዋሪዎች እና ንግድ ቤቶች ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል።

መሙላት፣ ማተም፣ እና ማሰራጨት የሚችሉት የህብረተሰብ ማሳወቂያ በራሪ ወረቀትን ያውርዱ!

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

206-684-7623 ላይ ያነጋግሩን። የትርጉም አገልግሎቶች በነጻ ይገኛሉ!

ለማመልከቻዎ፣ ሳይት ፕላን እንፈልጋለን፣ እንዲሁም የድርጅቱ ወይም ንብረቱ ባለቤት ካልሆኑ የፈቃድ (ማረጋገጫ) ደብዳቤ ሊያስፈልገን ይችላል።

ማመልከቻዎ ሁሉንም የሚፈለጉ ሠነዶችን ያጠቃለለ መሆኑን ያረጋግጡ፡

 • የፈቃድ ወይም የማረጋገጫ ደብዳቤ:የድርጅቱ ወይም ንብረቱ ባለቤት ካልሆኑ የተፈረመ የፈቃድ ደብዳቤ ይጫኑ

የሳይት ፕላን ዓይነቶች

የቦታ ፕላን ሳይኖር ማመልከቻዎን ልናይ አንችልም። ከመጫንዎ በፊት ፕላንዎን ለማዘጋጀት ከሚከተሉት መንገዶች አንዱን መምረጥ ይችላሉ።

አማራጭ 1፡ ፎቶግራፍ ላይ የተመሠረተ ፕላን (የሚመከር!)

 • ከዚህ በታች ያሉትን ልዩ መመሪያዎችን የሚከተሉ 3 ፎቶግራፎችን በመጠቀም በፎቶግራፍ ላይ የተመሠረተ ፕላን ያዘጋጁ
 • ሁሉም 3 ፎቶግራፎች ሳይት ፕላንዎን እንዲሸፍኑ ይጠበቃል። ከፎቶግራፍዎችዎ ውስጥ አንዱ በሳይት ፕላን ዝርዝር ውስጥ በይበልጥ ከታች የተገለጹትን አስፈላጊ ልኬቶች ማሳየት አለበት።
 • በፎቶግራፍ የቦታውን ማሳያ በድጅታል ለማሳየት የሚክበድዎት መሆኑን ካገኙ፣ እባክዎ የታቀደውን የማሳያ ጠርዞች ወይም ሙሉ ንድፍ በቀጥታ በእግረኛ መንገዱ ወይም በጎዳናው ላይ ክር ወይም ቾክ በመጠቀም “ይሳሉ”። ፎቶዎችን ከማንሳትዎ በፊት ይህንን ያድርጉ!
  • ፎቶ #1: ከታቀደው የሽያጭ ወይም የማሳያ ቦታ 10 ጫማ ያህል በመራቅ የታቀደውን የቦታ ማሳያ ፎቶ ያንሱ። ጠርዞቹን አስቀድመው ምልክት አድርገውበት ከሆነ፣ በፎቶው ውስጥ ያስገቡ፣ እንዲሁም መገኛውን ለመለየት እንዲረዳ የተወሰኑ ከጀርባ ያሉትንም ያስገቡ!
  • ፎቶ #2: የታቀደውን የማሳያ ቦታ በሌላኛው አቅጣጫ ተመሣሣይ ፎቶ ያንሱ።
  • ፎቶ #3: የቢዝነስዎን ሙሉ ህንጻ ፊት ለፊት እና የቦታውን ጠርዞች ጨምሮ የሚያሳይ ፎቶ ያንሱ።
 • ከፎቶዎቹ አንዱን ይምረጡ እና ሁሉንም ተፈላጊ ልኬት ለማጠቃለል ምልክት ያድርጉበት። ይህንን በዲጂታል መስራት ይችላሉ፣ ወይም ፎቶውን በማተም (በማጠብ) በእጅ ምልክት ያድርጉበት።

አማራጭ 2፡ መደበኛ ሳይት ፕላን

መደበኛውን ሳይት ፕላን ያስገቡ (የዕቅድ ቴምፕሌት እዚህ ሊያገኙ ይችላሉ)። መደበኛ ሳይት ፕላን እንዴት እንደሚዘጋጅ ስልጠና ለማግኘት እባክዎ በስልክ ቁጥር 206-684-7623 ይደውሉልን።

 • የሳይት ፕላን ዝርዝሮች:ሳይት ፕላዎን በሚያዘጋጁበት ጊዜ፣ ከታች የተዘረዘሩትን ሁሉንም መረጃ ማጠቃለል አለበት። ከዚህ መረጃ ውጪ፣ ማመልከቻዎን ለማየት እና ለማጽደቅ ረጅም ጊዜ ልወስድብን ይችላል። ለዚህም የርዝመት መለኪያ ሜትር ማግኘት እና በፕላንዎ ላይ በግልጽ ማሳየት ያስፈልግዎታል፡
 • የማሳያ ቦታ ልኬቶች፡ የታቀደውን ከቤት ውጭ ማሳያ አካባቢ ርዝመት እና ስፋት ያሳዩ። በእግረኛ መንገድ ባለው “ፈርኒቸር ዞን” ውስጥ ባለ ቦታ ላይ ካቀዱ፣ ከእግረኛ መንገድ (ጠርዝ) ጀምሮ የታቀደው ማሳያ ቦታ ያለውን ልኬት ማሳየት አለብዎት። በመንገዱ ጠርዝ እና የአካል ብቃት ቦታዎት ከሚጀምርበት ቦታ መካከል ቢያንስ 4’ እንዶኖር ያስፈልግዎታል። 
 • የእግረኛ ነጻ ዞን፥እግረኞች በእግረኛ መንገዱ ላይ እንዴት መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ለማሳየት ከአካል ብቃት አካባቢ ቀጥሎ ያለውን የእግረኛ መንገድ ስፋት ያሳዩ።
 • በአብዛኛው ሰፈር ውስጥ የሚያስፈልገው ዝቅተኛው yeእግረኛ ነጻ ዞን 6 ጫማ ነው (በአንዳንድ የከተማ አካባቢዎች የሚፈለገው ዝቅተኛ ስፋት 8 ጫማ ነው)። ለሰፈርዎ የሚያስፈልገው የእግረኛ ነጻ ዞን በተመለከተ ጥያቄዎች ካለዎት፣ እባክዎ በ 206-684-7623 ይደውሉልን።.
  • ማስታወሻ፥ ዝቅተኛውን ነጻ ዞን ለማስጠበቅ በቂ ቦታ ከሌለ፣ ለዚህ ፈቃድ ብቁ ላይሆኑ ይችላሉ። 
 • ከሌሎች ቋሚ ነገሮች የሚኖር እርቀት፥የእግረኛ መንገዱ እንደ የመብራት ምሶሶ፣ ዛፎች፣ የመኪና ማቆሚያ ሜትሮች፣ የውሃ መሳቢያ ቧንቧዎች፣ እና የብስክሌት ማቆሚያዎች ያሉ ሌሎች ቁሶችን ሊጨምር ይችላል። እባክዎ ከእነዚህ ቁሶች እስከ የቦታዎ ማሳያ ጠርዝ ድረስ ያለውን ርቀት ይስፈሩና እነኚህን ልኬቶች በፕላንዎ ውስጥ ያካትቱ።
 • የጠርዝ ቦታ መለያ ቁጥሮች፥ በሚከፈልበት የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ላይ የአካል እንቅስቃሴ ጂም ቦታ መጠቀም ካቀዱ፣ እባክዎ የጠርዝ ቦታውን መለያ ቁጥር(ሮች) ያቅርቡ (ቁጥሮቹን ለማግኘት ይህን ካርታ ይጠቀሙ)።
   1. የቦታው ማሳያ ልኬቶች
   2. የእግረኛ ነጻ ዞን ልኬቶች
   3. ከሌሎች ቋሚ ቁሶች የሚኖር እርቀት
   1. ጊዜያዊ የመጠቀሚያ ቦታ 4 ጫማ ስፋት በ 14 ጫማ ርዝመት
   2. ጊዜያዊ የመጠቀሚያ ቦታ 7 ጫማ ስፋት በ 28 ጫማ ርዝመት
   1. የእግረኛ ዞን 10 ጫማ ስፋት
   2. የእግረኛ ነጻ ዞን 6 ጫማ ስፋት
   1. የኃይል ምሶሶ ከኩርባ /ጠርዝ/ አካባቢ 8 ጫማ
   2. የመብራት ምሶሶ፣ አትክልቶች፣ እና ዛፎች ከኩርባ በግምት 18’’ እርቀት ላይ መሆን አለባቸው
 • መግለጫ፥ ከሚያስፈልጉ ልኬቶች ጋር የሳይት ፕላን ምሳሌ ፎቶግራፍ 
 • መዋቅራዊ ዝርዝሮች:ለሁሉም የጠርዝ ቦታ ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካባቢዎች አጥር ያስፈልጋል። በዚህ ላይ እንዲሁም ለማሳያው የሚጠቀሙትን ማናቸውም መሳሪያዎች ወይም አቅርቦቶች ላይ ዝርዝሮች እንፈልጋለን
  • ልኬቶችን፣ ስዕል ወይም ፎቶ፣ ወይም የአጥር መስሪያ ዕቃዎች መግለጫን ጨምሮ በጠርዝ አካባቢዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካባቢ የአጥር መግለጫ።
  • የመሳሪያዎች ዝርዝር ከመግለጫቸው ጋር (ለምሳሌ፣ አስር 2' x 3' የዮጋ ማት (የዮጋ መስሪያ ምንጣፎች)፤ አምስት የመለማመጃ ብስክሌቶች፤ አራት 10lb ኬትል ቤልስ)።
 • በታሪካዊ ዲስትሪክቶች ውስጥ የሚገኙ ከሆኑ፣ ከሳይት ፕላንዎ ጋር ለመጠቀም ያቀዱትን የሁሉም ፈርኒቸር፣ የዋና አቅራቢዎች፣ አትክልት የሚተከልባቸውን፣ የአጥር፣ ወይም ሌሎች ዓይነቶችን ቀለም እና አጨራረስ የሚያሳይ ሰነድ(ዶች)ይጫኑ።
 • ፎቶዎች፣ ከድረ-ገጾች የተገኙ ምስሎች፣ ወይም ካታሎግ የተቆረጡ ወረቀቶች በከለር (በቀለም) እስከሆነ ድረስ ተቀባይነት አላቸው። ይህንን መረጃ ለታሪካዊ ዲስትሪክት ሰራተኛ እንዲያዩት እንልካለን፤ ለማጽደቂያ የምስክር ወረቀት እርስዎ በተናጥል ለእነርሱ ማስገባት አይጠበቅብዎትም።

<ቀጣዩ ነገር ምንድን ነው? አንድ ጊዜ ለአስተማማኝ ጊዜያዊ የሽያጭ ማስጀመሪያ ፈቃድ ማመልከቻዎትን ካስገቡ፣ ስራውን ለመጀመር ለመዘጋጀት መውሰድ ያለብዎ የተወሰኑ ተጨማሪ እርምጃዎች እዚህ አሉ!

 • በጠርዝ ላይ ያለን ቦታ ለመጠቀም ካቀዱ፣ ከቡድናችን ከሚሰጠው ፈቃድ በተጨማሪ፣ በጊዜያዊነት መኪና ማቆምን የሚከለክል ፈቃዶችን ለማግኘት ማመልከት ያስፈልግዎታል።  ለማመልከት ዝግጁ ሲሆኑ፣ ለእርዳታ እባክዎ (206) 684-7623 ላይ ይደውሉልን።
 • አዲሱን ስራ ከመጀመርዎ ቢያንስ ከሁለት ቀን በፊት በህዝብ ቦታው ላይ ለመስራት ስላሰቡት ነገር ለጎረቤቶች ያሳውቁ።  ይህንን የህብረተሰብ ማሳወቂያ በራሪ ጽሁፍ ቴምፕሌት ይጠቀሙ።
 • የከተማዋን መስፈርቶች ያሟላ ኢንሹራንስ መያዝዎን ያረጋግጡ። ስለኢንሹራንስ መስፈርቶች ለተጨማሪ መረጃ፣ እባክዎ በ (206) 684-7623 ላይ ይደውሉልን!

ጠቃሚ ሆኖ ሊያገኙት የሚችሉትን የከቤት ውጭ መሳሪያ አማራጮች መመሪያ ከታች ባለው ሊንክ ይከተሉ።

Transportation

Greg Spotts, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.