በግሪንዉድ ጐዳና ላይ የእግረኛ ማሻሻያዎች

ጥር 11 ቀን 2022

አሁን ምን እየሆነ ነው?

የፕሮጀክታችን ቡድን፣ የተሰጠውን የመንገድ መብት መስረጽን የመሰለ፣ ስምምነቶችን ለማጠናቀቅ እና የፕሮጀክቱን ንድፍ ለማጠናቀቅ ልዩ ተፅእኖ ካላቸው የንብረት ባለቤቶች ጋር ሲሰራ ቆይቷል። በዚህ ፕሮጀክት የመጨረሻ የንድፍ ደረጃ ላይ እንገኛለን እና ግንባታው ልክ በቅርቡ በመጋቢት 2022 ይጀመራል እና ከ6-8 ወራት ሊቆይ መርሀግብር ተይዟል። በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ የማህበረሰቡ አባላት ግንባታ እንደሚጀመር የሚጠቁሙ የቅድመ-ግንባታ ማስታወቂያዎችን በፖስታዎች እና በምልክት መልክ መጠበቅ አለባቸው። ለዚህ ሥራ ስንዘጋጅ ለትዕግስትዎ እናመሰግናለን።

የቅድመ-ግንባታ ፕሮጀክት የጊዜ ቅደም-ተከተል ስዕላዊ ንድፍ

የፕሮጀክት አጠቃላይ እይታ

በሁለቱም በግሪንዉድ ጐዳና ሰሜን 117ኛ መንገድ እና ሰሜን 130ኛ መንገድ በኩል አዳዲስ የእግረኛ መንገዶችን ለመትከል አቅደናል። ግንባታ በቅርብ በመጋቢት 2022 ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ግሪንዉድ ጐዳና በመኖሪያ ቤቶች፣ በአፓርታማዎች፣ በኮንዶሚኒየም ቤቶች እና በንግዶች የታጀበ ሲሆን በተጨማሪም በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የአውቶቡስ መስመር ነው። በብሮድቪው ውስጥ የሰሜን 117ኛ መንገድ እና ሰሜን 130ኛ መንገድ የግሪንዉድ ክፍል ለአዲስ የእግረኛ መንገድ ግንባታ የረዥም ጊዜ ቅድሚያ ተሰጥቶታል።

እነዚህ አዳዲስ የእግረኛ መንገዶች ወሳኝ ክፍተቶችን በመሙላት ነዋሪዎችን ከተደጋጋሚ የመጓጓዣ አገልግሎቶች፣ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች የአጎራባች መዳረሻዎች ጋር ለማገናኘት ይረዳሉ። እነዚህ ማሻሻያዎች በ2030 ሁሉንም የትራፊክ ሞት እና ከባድ ጉዳቶችን ለማስወገድ የሲያትል ራዕይ ዜሮ (Seattle's Vision Zero) ግብን ለማሳካት ይረዳሉ።

በተለይ በግሪንዉድ ጐዳና ሰሜን፣ የብሮድቪው ማህበረሰብ የጎርፍ ችግር እንዲሁም ለእግረኛ መሠረተ ልማት ከበቂ መዋዕለ ንዋይ በታች መደረጉ አጋጥሞታል። በዚህ ፕሮጀክት የውሃ ጥራትን እና የውሃ ፍሳሽን በዚህ አካባቢ የሚያሻሻል፣ የቦታ የተፈጥሮ ፍሳሽ ማስወገጃ/ ማጥሪያ ዘዴዎችን ለመስራት አቅደናል።

የፕሮጀክት ዳራ

ከ 2016 ጀምሮ በሰሜን ግሪንዉድ ጐዳና በሰሜን 92ኛ መንገድ እና ሰሜን 145ኛ መንገድ መካከል የእግረኛ መንገዶችን ለመትከል እየሰራን ነበር። ከአዲስ የእግረኛ መንገድ በተጨማሪም፣ ኩርባዎችን፣ የመትከያ ንጥፍ ቁራሾችን፣ የእግረኛ ምልክቶችን ማሻሻያዎችን፣ አዲስ የትራፊክ ምልክቶችን እና ለአካል ጉዳተኛ አሜሪካዊያን የወጣ ህግን የሚያሟላ የኩርባ መወጣጫዎችን ጨምረናል።

በግሪንዉድ ጐዳና ሰሜን ላይ የአሁን የእግረኛ ሁኔታዎች

በግሪንዉድ ጐዳና ሰሜን ላይ የአሁን የእግረኛ ሁኔታዎች።

በግሪንዉድ ጐዳና ላይ የእግረኛ ማሻሻያዎች ካርታ

የፕሮጀክት አካባቢ

የፕሮጀክት አካባቢ በግሪንዉድ ላይ ከ113ኛ እስከ 117ኛ ነው

መርሀ-ግብር

ግንባታው የሚጀምረው በሰሜን 117ኛ መንገድ እና ሰሜን 130ኛ መንገድ መካከል - መጋቢት 2022 ነው

ስምምነት የተጠናቀቀ በሲያትል የማመላለሻ መምሪያ እና በንብረት ባለቤቶች መካከል - ህዳር 2021

ለማህበረሰብ ቡድኖች ምናባዊ አቀራረብ - ጥር 2020

የፖስታ ካርድ በአቅራቢያ ላሉ ንግዶች እና ነዋሪዎች የተላከ - ሰኔ 2020

ቁሶች

ለነዋሪዎች ደብዳቤዎች (ሰኔ 2020)

የገንዘብ ድጋፍ

ይህ ፕሮጀክት በ ሙቭ ሲያትል ለቪ (Move Seattle Levy) የተደገፈ ነው፣ እሱም በመራጮች የጸደቀው በ2015።

ሙቭ ሲያትል ለቪ (Move Seattle Levy)

Transportation

Greg Spotts, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.