የተሻሻለው 6/10/26
የገንዘብ ድጋፉ አሁንም አለ።
የሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ጥፋትን እና የንብረት ውድመትን ለመከላከል የደህንነት ማሻሻያዎችን ለመክፈል ለማገዝ ለአንድ ንግድ እስከ 10,000 ዶላር የአንድ ጊዜ ተመላሽ ያደርጋል።
ብቁ ለመሆን፣ ንግዶች የወንጀል መከላከልን በአካባቢ ዲዛይን (CPTED) የደህንነት ግምገማን ከተረጋገጠ ባለሙያ፣ ለምሳሌ ከሲያትል ፖሊስ ዲፓርትመንት የወንጀል መከላከል አስተባባሪ ጋር ማጠናቀቅ አለባቸው። የCPTED የደህንነት ግምገማ ከተጠናቀቀ በኋላ ብቻ የተገዙ የደህንነት እርምጃዎች ገንዘቡን ለማስመለስ ብቁ ናቸው።
ማመልከቻዎች እስከ ዲሴምበር 2026 ወይም ገንዘቦች እስኪያልቁ ድረስ ክፍት ናቸው።
ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ወጪዎች እና ሌሎች በወንጀል መከላከል በአካባቢያዊ ዲዛይን የተረዱ ኢንቨስትመንቶች ገንዘብ ተመላሽ ሊያደርጉ ይችላሉ። በCPTED የደህንነት ግምገማ ወቅት ከወንጀል መከላከል አስተባባሪ በተሰጡት ጥቆማዎች መሰረት ኢንቨስትመንቶችን እንዲገዙ እናበረታታዎታለን። ስለ ብቁ ወጪዎች ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ ካልዎት እባክዎን ቢሯችንን ያነጋግሩ።
- መብራት
- የደህንነት መስኮት ማጠናከሪያ ፕላስቲክ
- የመስኮት መትከያዎች
- “ሲሰበር የማይበታተን” የታሸገ መስታወት ያለው መስኮት
- አዲስ የመደብር ታዛ ወይም ለነባሩ ጥገና
- የንግድ ቦታ እና መንገድ መሪ ምልክቶች (ክፍት ነው፣ ዝግ ነው፣ መግቢያ፣ መውጫ፣ የሥራ ሰዓቶች)።
- አድራሻ መሰየሚያ
- በመግቢያ ቦታዎች ላይ የመከላከያ የምድር ገጽታዎች (የሮዝ ቁጥቋጦዎች / ሆሊ ቡሽ)
- የተፈቀዱ የመንገድ መትከያዎች (የመንገድ ላይ የቤት ዕቃዎች መመሪያዎችን ይመልከቱ)
- መቀስ በር
- የመስኮት ታጣፊ የደህንነት መዝጊያ
- የበር መቆለፊያ
- የመስኮት መቆለፊያዎች
- የማንቂያ/ማስተንቀቂያ ሥርዓቶች (መሣሪያዎቹን ብቻ፣ መቆጣጠሪያ አገልግሎቶቹን እና የደኅንነት ካሜራዎቹን ሳያካትት)
ብቁ ያልሆኑ ወጪዎች፦
- ሕገ-ወጥ የግድግዳ ጽሑፍ ማስወገድ
- የደኅንነት ካሜራዎች ግዢ
- ለደኅንነት ጥበቃ ሠራተኞች የሚደረጉ ክፍያዎች
- የተሰረቁ ዕቃዎች/አገልግሎቶች
ለዚህ ፈንድ ለማመልከት እነዚህን አስፈላጊ እርምጃዎች ይከተሉ፦
እርምጃ 1፦ ነፃ የCPTED የደህንነት ግምገማዎን ለማድረግ ከአካባቢዎ የወንጀል መከላከያ አስተባባሪ ጋር ቀጠሮ ይያዙ።
- የCPTED የደህንነት ግምገማ ቀጠሮ ለመያዝ፣ የአካባቢዎን የወንጀል መከላከያ አስተባባሪ (CPC) በኢንተርኔት ላይ ያግኙ እና በኢሜል የሚከተሉትን አካተው ይላኩለት/ላት፦
- የንግድዎን ስም
- የንግድዎን አድራሻ
- ለንግድ መመለስ ፕሮግራም እንደሆነ የCPTED ደህንነት ግምገማ የሚጠይቁት ይጻፉ።
ደረጃ 2፦ የCPTED የደህንነት ግምገማዎን ያጠናቅቁ እና በCPCዎ የተሰጡዎን ምክሮች ያስቡባቸው።
- በCPTED የደህንነት ግምገማው ወቅት CPCዎ ከእርስዎ ጋር በመሆን የንግድ ቦታዎን ይጎበኛሉ። የውይይቱን ነጥቦች ማስታወሻ እንዲይዙ ይጠየቃሉ። የዚህ ሂደት አካል ሆኖ በጽሁፍ የሚደርስዎ መደበኛ ግምገማ አይኖርም።
ደረጃ 3፦ አጠቃላይ ከፍተኛው የካሳ ክፍያ $10,000 መሆኑን በአእምሮዎ በመያዝ ለግዢዎ እቅድ ያውጡ።
- ለደህንነት ማሻሻያዎችዎ አስፈላጊ የሆኑ ፈቃዶችን ያግኙ።
- አማራጭ፦ ሊያደርጓቸው ስለሚፈልጓቸው የደህንነት ማሻሻያዎች ለመወያየት እና ማንኛውንም ጥያቄ ለመጠየቅ በ (206) 684-8090 በመደወል ወይም ወደ OED@seattle.gov ኢሜል በማድረግ ቢሯችንን ያነጋግሩ።
- ንግድዎ በታሪካዊ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ከሆነ፣ ከCPTED ጋር የተያያዘ ኢንቨስትመንት ከመግዛትዎ በፊት የፈቃድ ሰርተፍኬት (Certificate of Approval) ማግኘት ሊኖርብዎ ይችላል። ንግድዎ ታሪካዊ ወረዳ ውስጥ መሆኑን እዚህ ያረጋግጡ፦ Historic Districts - Neighborhoods | seattle.gov (ታሪካዊ ወረዳዎች - ሰፈሮች | seattle.gov)።
ደረጃ 4፦ ግዢዎን(ዎችዎን) ይፈጽሙ እና የክፍያ ማስረጃዎችን (የዜሮ ቀሪ ሂሳብ ማሳያ ደረሰኞች እና/ወይም የሽያጭ ደረሰኞች) ይሰብስቡ።
- ተቀባይነት ያላቸው የወጪ ሰነዶች ምሳሌዎች ከዶላር መጠኑ ጋር የሚዛመድ የክፍያ ማስረጃ የተያያዘለት የእቃዎች ዝርዝር ደረሰኝን ያካትታሉ። ተቀባይነት ያላቸው የማስረጃ ዓይነቶች የሚከተሉትን የሚያካትቱ ሲሆኑ፣ በእነዚህ ብቻ ግን አይወሰኑም፦
- ቀሪ ሂሳቡ ሙሉ በሙሉ መከፈሉን በግልጽ የሚያሳይ የደረሰኝ ማስረጃ።
- በገንዘብ ከተለወጠ ቼክ ማስረጃ ጋር የተያያዘ የደረሰኝ፣ የዋጋ ዝርዝር ወይም ግምት ማስረጃ።
- ግዢው ምልክት ከተደረገበት የባንክ መግለጫ ወይም የክሬዲት ካርድ መግለጫ ጋር የተያያዘ የደረሰኝ፣ የዋጋ ዝርዝር ወይም ግምት ማስረጃ።
- ምን እንደተገዛ፣ የግዢውን ቀን እና ግዢው መጠናቀቁን ማየት ያስፈልገናል።
ደረጃ 5፦ ለካሳ ክፍያ ማመልከቻዎን በኢንተርኔት ላይ ያስገቡ።
እባክዎ ከማመልከትዎ በፊት ሙሉውን የብቃት መስፈርት፣ አስፈላጊ ሰነዶችን እና ሌሎች መረጃዎችን ይመልከቱ።
ጽ/ቤታችን ሁሉም ማህበረሰቦች የኢኮኖሚ ዕድሎችን እንዲያገኙ በማረጋገጥ በሲያትል ውስጥ ለሁሉም ሰው ተስማሚ የሆነ ተደራሽ እና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው።
የሲያትል ከተማ፣ እያንዳንዱን ሰው በፕሮግራሞቹ እና በእንቅስቃሴዎቹ እንዲሳተፍ ያበረታታል። እርዳታ፣ ትርጉም፣ ለአካል ጉዳተኞች የሚደረጉ ማስተካከያዎች ወይም በተለየ ቅርጸት የተዘጋጁ ሰነዶች ከፈለጉ፣ እባክዎ ቢሯችንን በ206-684-8090 ወይም በOED@seattle.gov ያነጋግሩ።
ወደ አንድ ክፍል ይዝለሉ
የብቁነት መስፈርቶች
ለሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ብቁ ለመሆን፣ ብቁ ንግዶች የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው፡-
- የ CPTED የደህንነት ግምገማ ማግኘት።
- የCPTED የደህንነት ግምገማ ከተደረገ በኋላ ብቁ የሆነ CPTED መረጃ ያለው የደህንነት ኢንቨስትመንት መግዛት።
- አሁን ላይ የሚሰራ/ቀኑ ያላለፈበት የሲያትል የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው መሆን።
- ሁሉንም የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ ህጎች እና ደንቦችን ማክበር።
- በሲያትል ከተማ ወሰኖች ውስጥ መገኘት።
- በገለልተኛ ባለቤት የተያዘና የሰንሰለት ንግድ ያልሆነ።
- በገለልተኛ ባለቤትነት የተያዙ ፍራንቻይዝ ንግዶችም ለማመልከት ብቁ ናቸው።
- ለትርፍ የተቋቋመ ንግድ ወይም ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም፣ 501(c)(3)፣ 501(c)(6)፣ ወይም 501(c)(19) መሆን።
- ከአምስት (5) የማይበልጡ ቦታዎች ያለው።
- በአሁኑ ጊዜ ለአገልግሎት ክፍት እና የሚንቀሳቀስ ወይም ደግሞ የተፈረመ የኪራይ ውል በማስረጃነት ማቅረብ የሚችል ለአገልግሎት ክፍት ለመሆን እያቀደ ያለ ንግድ ነው።
ተጨማሪ መመዘኛዎች፦
- እያንዳንዱ የንግድ ቦታ፣ ባለቤት ወይም መለያ (እንደ EIN፣ SSN፣ UBI ቁጥር፣ የንግድ ፈቃድ ቁጥር፣ ቤት እና/ወይም የንግድ አድራሻ) አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው ማስገባት የሚችለው።
- ንግዱ በአንድ ህዝቡን የሚያገለግል አካላዊ ቦታ እና/ወይም በተንቀሳቃሽ የጭነት መኪናዎች ላይ ሆኖ የሚሰራ መሆን አለበት።
- ከተሰጣቸው፣ ንግዶች W-9 መሙላት አለባቸው።
የንግድ መጠንን የሚመለከቱ መስፈርቶች፦
- ንግዱ ከ50 የማይበልጡ የሙሉ ጊዜ አቻ ሰራተኞች ሊኖሩት ይገባል።
- ለሲያትል ከተማ የፋይናንስ እና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች መምሪያ በንግድ እና ሥራ (Business and Occupation) ግብሮች ላይ ሪፖርት በተደረገው መሠረት የንግዱ ዓመታዊ የተጣራ ገቢ ከ$1,000 ዶላር በላይ የሚሠራ እና ከ$7,000,000 ዶላር የማይበልጥ መሆን አለበት።
ለሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ለማመልከት ብቁ ያልሆኑ ንግዶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
- ከኪንግ ካውንቲ ጋር ባልተካለለ አካባቢ ውስጥ የሚገኝ የንግድ ተቋም።
- ሰንሰለት ንግዶች።
- በሲያትል ማዘጋጃ ቤት ህግ አንቀጽ 6.270 ስር የሚተዳደሩ "የአዋቂዎች መዝናኛ" ንግዶች።
- ንግዱ የአጭር ወይም የረጅም ጊዜ የኪራይ ወይም የኢንቨስትመንት ንብረት ነው (የግል ሪል እስቴት እና ገለልተኛ ሪልተሮችን (independent realtors)፣ የአጭር ጊዜ ኪራዮች ኤርቢኤንቢን (Airbnb)፣ ቨርቦን (Vrbo)፣ ወዘተ ያካትታሉ)።
- ይህ መስፈርት ሱቃቸውን በሊዝ ወይም በኪራይ ይዘው ለሚገኙ የንግድ ባለቤቶች አይተገበርም። ሱቆቻቸውን በሊዝ ወይም በኪራይ የያዙ የንግድ ባለቤቶች ማመልከቻ ለማስገባት አሁንም ብቁ ናቸው።
- ንግዱ የታክሲ ስራ፣ በጋራ መሣፈር (ራይድሼር)፣ ወይም የምግብ ማድረስ አገልግሎት (ለምሳሌ እንደ ኡበር፣ ሊፍት፣ የሎ ካብ፣ ዶር ዳሽ፣ ኡበር ኢትስ፣ ወዘተ) የሆነ።
- የንብረት ባለቤቶች እና ቤት አከራዮች ለገንዘብ ድጋፉ ብቁ አይደሉም፣ ነገር ግን ለንግድ ሥራ ይዞታውን ያከራዩዋቸውን ተከራዮች እንዲያመለክቱ ማበረታታት ይችላሉ።
ለማመልከቻ አስፈላጊ ሰነዶች
የሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ማመልከቻዎች በኢንተርኔት ላይ እንደገቡ ተቀባይነት ያገኛሉ፣ ይታያሉ እና ይስተናገዳሉ።
ከማመልከትዎ በፊት ይህንን ሰነድ ከማመልከቻው ጋር አብረው ማየት ይችላሉ፦ ወደ ንግድ መመለስ ፈንድ ማመልከቻ የጥያቄዎች መመሪያ።
ብቁ አመልካቾች ማመልከቻቸውን ለማስገባት የሚከተለው መረጃ ያስፈልጋቸዋል፦
- የተዋሃደ የንግድ መታወቂያ (Unified Business Identifier) ቁጥር (ዘጠኝ አሃዞች)።
- ለዋሽንግተን ስቴት የንግድ ፍቃድ ሲያመለክቱ የተዋሃደ የንግድ መለያ ቁጥር ያገኛሉ። የተዋሃደ የንግድ መለያ ቁጥርዎን (Unified Business Identifier) በዋሽንግተን ስቴት የገቢዎች ክፍል (Washington State Department of Revenue) በኩል በኢንተርኔት ላይ መፈለግ ይችላሉ።
- የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር (ከአራት እስከ ስድስት አሃዞች)።
- በሲያትል ውስጥ የንግድ ሥራ እየሰሩ ከሆነ፣ የሲያትል ንግድ ፈቃድ የግብር ምስክር ወረቀት ሊኖርዎት ይገባል፣ ይህ የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር (City Business License Number) በመባልም ይታወቃል። ይህንን የምስክር ወረቀት በየዓመቱ ከዲሴምበር 31 በፊት ማደስ አለብዎት።
- ይህ የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር ከዋሽንግተን ስቴት የንግድ ፍቃድ የተለየ ነው። ቁጥርዎን በከተማ ንግድ ፍቃድ የንግድ ፍለጋ መሳሪያ ላይ ማግኘት ካልቻሉ የዋሽንግተን ስቴት ፍቃድ ብቻ ሊሆን ይችላል ያልዎት።
- ለከተማ ንግድ ፈቃድ ማመልከት እና በኢንተርኔት ላይ በfilelocal-wa.gov ወይም በፖስታ ማደስ ይችላሉ።
- ጥያቄ ካልዎት በቀጥታ ለከተማው ፋይናንስ ቡድን በtax@seattle.gov ኢሜል በማድረግ ወይም ወደ (206) 684-8484 በመደውል ማነጋገር ይችላሉ።
- የተሞላ CPTED የደህንነት ግምገማ ።
- የCPTED የደህንነት ግምገማ ቀጠሮ ለመያዝ፣ የአካባቢዎን የወንጀል መከላከያ አስተባባሪ በኢንተርኔት ላይ ያግኙ እና ኢሜል ይላኩለት/ላት። የንግድዎን ስም፣ የንግድ አድራሻዎን ያካትቱ እና ለወደ ንግድ መመለስ ፕሮግራም (Back to Business Program) የCPTED ደህንነት ግምገማ እየጠየቁ መሆኑን ልብ ይበሉ።
- ብቁ የሆኑ የኢንቨስትመንቶች ዝርዝር እዚህ ይገኛል።
- ብቁ ለሆኑ CPTED ኢንቨስትመንቶች የክፍያ ማስረጃ።
- ብቁ ለሆኑ CPTED በመረጃ የተደገፈ ኢንቨስትመንቶች ግዢ የደረሰኞች ቅጂዎችን ያቅርቡ። ብቁ የሆኑ የኢንቨስትመንቶች ዝርዝር እዚህ ይገኛል።
- ሙሉ ማመልከቻው ለገንዘብ ድጋፉ ከግምት እንዲገባ የዕቃ ዝርዝር የያዘ ደረሰኝ እና የክፍያ ማስረጃው ያስፈልጋሉ።
- የክፍያ ማስረጃ የማያሳዩ ግምቶች፣ ዋጋ ዝርዝሮች እና/ወይም ደረሰኞች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- የሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ የሚንቀሳቀሰው በካዳ ሞዴል ነው፣ ይህ ማለት አመልካቾች አስቀድመው ብቁ መሳሪያዎችን ገዝተዋል ወይም ለብቁ ተከላዎች ከፍለዋል።
- ስለ ብቁ ወጪዎች ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ ካልዎት እባክዎን ቢሯችንን ያነጋግሩ።
የማመልከቻ እገዛ
የሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ማመልከቻ በእንግሊዝኛ በኢንተርኔት ላይ መቅረብ አለበት።
የጽሑፍ ትርጉም ወይም የቃል ትርጉም ድጋፍ
ጥያቄዎችን ለመመለስ እና ማመልከቻዎን እንዲያጠናቅቁ ለመርዳት ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሰራተኞች አሉን።
የጽሑፍ ትርጉም ወይም የቃል አስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለመጠየቅ፣ እባክዎን በ(206) 684-8090 ይደውሉ። እባክዎ የእርስዎን ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ ተመራጭ ቋንቋ እና የተፈለገውን የድጋፍ ዓይነት የያዘ የድምጽ መልዕክት ይተዉ።
በማመልከቻው ላይ ተጨማሪ እገዛ
ጽ/ቤታችን ሁሉም ማህበረሰቦች የኢኮኖሚ ዕድሎችን እንዲያገኙ በማረጋገጥ በሲያትል ውስጥ ለሁሉም ሰው ተስማሚ የሆነ ተደራሽ እና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው። እርዳታ፣ ትርጉም፣ ለአካል ጉዳተኞች የሚደረጉ ማስተካከያዎች ወይም በተለየ ቅርጸት የተዘጋጁ ሰነዶች ከፈለጉ፣ እባክዎ ቢሯችንን በ206-684-8090 ወይም በOED@seattle.gov ያነጋግሩ።
በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች
1. ካመለከትኩ በኋላ ምን ይከሰታል?
ካመለከቱ በኋላ ከOED_BackToBusiness@seattle.gov የኢሜል ማረጋገጫ ይደርስዎታል። ማመልከቻዎን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገን በኢሜል ይነገርዎታል። ማመልከቻዎ ከተጠናቀቀ በኋላ ለኤሌክትሮኒክ ፊርማ የቀረቡ ሁለት ሰነዶች በAdobeSign በኩል ይደርሱዎታል። የኤሌክትሮኒክ ፊርማዎቹን አስቀምጠው ካጠናቀቁ በኋላ በW-9 ላይ በተጻፈው የደብዳቤ መቀበያ አድራሻ ቼክ እንልክልዎታለን። ለተሟሉ ማመልከቻዎች የማመልከቻ ግምገማ ጊዜው እስከ አራት ሳምንት ሊወስድ ይችላል። የተጓደለ መረጃ ያላቸው ወይም ተከታይ ጥያቄ የሚፈልጉ ማመልከቻዎችን ለመስተናገድ ረዘመ ያለ ጊዜ ይወስዳል።
ማስታወሻ፦ ሰራተኞቻችን አመልካቾችን በስልክ ወይም በ@seattle.gov በሚያበቃ ኢሜል አግኝተው ያነጋግራሉ። ንግዶች የሰራተኞቹን ማንነት በ(206) 684-8090 ወደ ቢሯችን በመደወል ማጣራት ይችላሉ።
2. በሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ እና ሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
የሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ በብልሽት ወይም በሌላ ንብረት ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት ለተደረጉ ጥገናዎች የወጣ ወጪን በማካካስ ይረዳል። ስለ የሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ስጦታ የበለጠ ይወቁ።
የሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ የመከላከያ የደህንነት እርምጃዎችን ለማስመለስ ይረዳል።
3. የሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ የሚውለው ለመከላከያ የደህንነት እርምጃዎች ግዢዎች ብቻ ነው?
የገንዘብ ድጋፍ ከመከላከያ የደህንነት እርምጃዎች ጋር ለተያያዙ ግዢዎች ብቻ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለው የCPTED የደህንነት ግምገማ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው። ሊገዙ የሚችሉ ግዢዎች ጊዜያዊ መስኮት ወይም የበር ማሸጊያ እንጨት፣ የመስኮት ጥገና ወይም መተካት፣ የበር ጥገና ወይም መተካት፣ የግቢ በር ጥገና ወይም መተካት፣ በሮች፣ መቆለፊያዎች፣ ምልክቶች፣ የደህንነት የደህንነት መስኮት ማጠናከሪያ ፕላስቲክ እና የማይሰበር መስታወትን ያካትታሉ። የሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት የገንዘብ ድጋፍ ሕገወጥ የግድግዳ ጽሑፎችን ማስወገድን፣ የደህንነት ካሜራዎችን መግዛትን፣ ለደህንነት ጥበቃ ሰራተኞች ክፍያን ወይም የተሰረቁ እቃዎች መጥፋትን አይሸፍንም።
የሱቅ ፊት ለፊትዎን ለመጠገን የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ማመልከት የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ በማመልከቻ ውስጥ ያሉትን ጥያቄዎች ይከተሉ። ስለ የሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል።
ሕገወጥ የግድግዳ ጽሑፍ በሕዝብ ቦታ ላይ ወይም በግል ንበረት ላይ ካዩ በሚከተለው ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ፦
- አግኝ/አስተካክል (Find It/Fix It) መተግበሪያን፣ የኢንተርኔት ላይ የሪፖርት ቅጹን በመጠቀም ወይም ወደ ከተማው የግራፊቲ ሪፖርት መስመር (City’s Graffiti Report Line) ጋር በ(206) 684-4243 በመደወል።
- ስለ ከተማዋ የግራፊቲ መከላከል እና ማስወገድ ፕሮግራም ተጨማሪ መረጃ በዚህ ገጽ ላይ ይገኛል።
4. የሱቅ የፊት ለፊት የደህንነት የገንዘብ ስጦታዎች 10,000 ዶላር ናቸው። በልዩ ሁኔታዎች ላይ ለምሳሌ ብዙ ኢንቨስትመንቶች መደረግ ሲኖርባቸው፣ ስጦታው ከገደቡ በላይ የመሄድ ዕድል ሊኖር ይችላል?
የደህንነት እርምጃዎች ዋጋ ከ10,000 ዶላር በላይ ሊሆን እንደሚችል እንገነዘባለን። ሆኖም ከተማዋ በተቻለ መጠን ብዙ ንግዶችን መርዳት እንድትችል እርዳታዎች በ10,000 ዶላር ብቻ የተገደቡ ይሆናሉ።
5. ምን ዓይነት ንግዶች ናቸው ለዚህ የገንዘብ ድጋፍ ብቁ የሆኑት?
አትራፊ ንግዶች ወይም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተቋሞች 501(c)(3)፣ 501(c)(6)፣ ወይም 501(c)(19)፣ በአካል መሬት ላይ ያሉ ሕዝብን የሚያገለግሉ ሱቆች እና የምግብ መኪናዎች ለሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ብቁ ናቸው። ሁሉም አመልካቾች ወቅታዊ የሲያትል ንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል። የንብረት አስተዳዳሪዎች እና ቤት አከራዮች ለገንዘብ ድጋፉ ብቁ አይደሉም፣ ነገር ግን ተከራዮቻቸውን እንዲያመለክቱ ሊያበረታቱ ይችላሉ።
6. በአካባቢ ዲዛይን ወንጀል መከላከል (Crime Prevention Through Environmental Design) ምንድነው?
በአካባቢ ዲዛይን ወንጀልን መከላከል ወንጀልን የመከላከል ቦታን መሰረት ያደረገ እና ዘርፈ-ብዙ ዲሲፕሊናዊ አካሄድ ሲሆን፣ የተገነባውን አካባቢ ዲዛይን እና አስተዳደር በመጠቀም ወንጀልን ለመከላከል ወንጀልን ሊያስከትሉ የሚችሉ የአደጋ ስሜቶችን በማሳደግ በሰዎች ባህሪ ላይ ተጽእኖ ማሳደር ነው። 'ሴፕ-ቴድ' እየተባለ የሚጠራው ሂደቱ ተጎጂዎችን ይቀንሳል፣ የደህንነትን ግንዛቤ ያሳድጋል እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታዎችን በመፍጠር እና በመንከባከብ የማህበረሰብን ጠቃሚ ሚና እውቅና ይሰጣል።
CPTED የቦታዎችን አካላዊ እና ማህበራዊ አካባቢ ለመገምገም እና የእንቅስቃሴ ቅጦችን እና እርስ በርስ የሚጋጩ አጠቃቀሞችን ለመለየት እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ለመገምገም ማዕቀፍ ያቀርባል፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ ተፅእኖዎችን እና የጠባቂዎች ዓይነቶችን እና ደረጃዎችን ይለያል።
ለበለጠ መረጃ የሲያትል ፖሊስ ዲፓርትመንት ድረ-ገጽን በCPTED እና በዚህ በራሪ ወረቀት ላይ ይመልከቱ።
7. የካናቢስ ንግዶች ለማመልከት ብቁ ናቸው?
አዎ፣ የካናቢስ ሱቆች፣ አብቃይ እና ማከፋፈያዎች ሌሎች የብቁነት መስፈርቶችን እስካሟሉ ድረስ ማመልከት ይችላሉ።
8. የገንዘብ ተቀባዮች እንዴት ነው የሚመረጡት?
ማመልከቻዎችን እንዳመጣጣቸው እየገመገምን እናስተናግዳለን። አመልካቾች የብቁነት መስፈርቶችን ካሟሉ እና የገንዘብ ድጋፍ ካለ የካሳ ስጦታው ይሰጣቸዋል።
9. ተሸላሚዎች ገንዘቡን መልሰው መክፈል አለባቸው?
አይ፣ ይህ ስጦታ ነው። የንግድ ድርጅቶች ገንዘቡን መመለስ አይጠበቅባቸውም።
10. ድጎማዎቹ እንደ ታክስ ገቢ ይቆጠራሉ?
አይ፣ ድጎማዎቹ ታክስ የሚከፈልባቸው ገቢዎች አይደሉም።
11. የትርፍ ሰዓት ሰራተኞች እንደ ተቀጣሪዎች ይቆጠራሉ?
አዎ፣ በደመወዝ ላይ ያለ ማንኛውም ሰው እንደ ሰራተኛ ይቆጠራል።
12. የሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ የገንዘብ ምንጭ ምንድን ነው?
የሱቅ ፊት ደህንነት ፈንድ የሚሸፈነው በደመወዝ ወጭ ታክስ (Payroll Expense Tax) ነው።
13. አመልካቾች አንድ ነገር ከመግዛታቸው በፊት ገንዘቡን ማግኘት ይችላሉ?
አይ። ወደ ንግድ ሥራ መመለስ ፕሮግራም የሚሠራው በካሳ ሞዴል ነው፣ ይህም ማለት አመልካቾች አስቀድመው መሣሪያዎችን ገዝተዋል ወይም ለጥገና ክፍያ ከፍለዋል እና ወጪዎቹን በማስረጃ ማረጋገጥ ይችላሉ ማለት ነው።
14. አመልካቾች ገንዘቡን እንዴት ነው የሚቀበሉት?
ብቁ አመልካቾች በW-9 ቅጻቸው ላይ በተዘረዘረው የፖስታ አድራሻ ቼክ ይደርሳቸዋል። አስፈላጊ ከሆነ ቼኮችን በአካል የመቀበል አማራጭ ይኖርዎታል።
15. ቀደም ብዬ ለሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ፕሮግራም አመልክቼ፣ ጠቅላላ ወጪዬ ግን ከቀድሞው የደህንነት ፈንድ ስጦታ ገደብ 6,000 ዶላር በላይ ከሆነ ምን ይደረጋል?
ቀደም ሲል ለፕሮግራሙ ያመለከቱ እና ጠቅላላ ወጪያቸው ከቀድሞው የደህንነት ፈንድ ስጦታ ገደብ 6,000 ዶላር በላይ የሆኑ አመልካቾች እስከ ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 10 ቀን 2026 ድረስ ወደ ንግድ ሥራ መመለስ (Back to Business) ፕሮግም ቡድን አባል አግኝቶ ያነጋግራቸዋል።
ከ6,000 ዶላር በላይ የሆነ ጠቅላላ ድምር የወጪ ሰነድ ያቀረቡ አመልካቾች ብቻ ተጨማሪ የካሳ ስጦታ ለማግኘት ብቁ ይሆናሉ። ለምሳሌ ቀደም ብለው አመልክተው፣ ያስገቧቸው ግን እስከ 6,000 ዶላር ወይም ከዚያ በታች ብቻ የሆኑ ደረሰኞችን ከሆነ ተጨማሪ የካሳ ስጦታ ለማግኘት ብቁ አይሆኑም።
ስለ ሂደቱ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት እባክዎ ወደ ንግድ ሥራ መመለስ ፕሮግራም ቡድንን በOED_BackToBusiness@seattle.gov ያነጋግሩ።