COVID-19 የኪራይ ውል የሕግ ድጋፍ
የእኛ ሸሪክ ድርጅት ፣ ኮሚኒቲ ራይዝ እና ፕርክን ኮይ ኤል ኤል ፒ ለትናንሽ ንግዶች እና ለትርፍ ላልሆኑ ድርጅቶች COVID-19 የሊዝ ማሻሻያ መገልገያ መሳሪያ ፈጥረዋል ፣ ይህም ከንግድ ባለንብረቱ ጋር ስለ ኪራይ ሁኔታ ለመደራደር እንዲረዳቸው መረጃ እና ሰነዶችን ለማቅረብ ነው ፡፡ አነስተኛ የንግድ ሥራ እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች የሚከተሉትን ቀጣይ እርምጃዎች እንዲወስዱ ይመክራሉ፡
- ከአከራዮት ጋር ይወያዩ ፥ ቀደም ብሎ በጽሑፍ ከአከራዮት ጋር የሚደረግ ግንኙነት ተመራጭ ነው
- የኪራይዎን ውል ይገምግሙ
- በኪራዮና ውሎት ዙሪያ ድርድር ያድርጉ
- የመድን ዝርዝሮችን ይመርምሩ
- አብነቶችን ይጠቀሙ
እንዲሁም ከCOVID-19 ጋር የተያያዙ የኪራይ ጥያቄዎችን ለማገዝ ለአነስተኛ ንግዶች ወይም ከ 50 ሠራተኞች በታች ለሆኑ እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን የሕግ ባለሙያዎችን የ 60 ደቂቃ ነፃ ምክር ይሰጣሉ፡፡ ቀጠሮ ለመያዝ ይህንን የመመዝገቢያ ቅጽ ይሙሉ፡፡
የመመዝገቢያ ቅጹን ለመሙላት እርዳታ ከፈለጉ ወይም የቋንቋ እገዛ ከፈለጉ እባክዎን ለ oed@seattle.gov ኢሜል ይላኩ ወይም ለኢኮኖሚ ልማት ጽ / ቤት በ (206) 684-8090 ይደውሉ እና የሚከተሉትን መረጃዎች የያዘ የድምጽ መልዕክት (voice mail) ይተዉ፡
- ስምዎን
- ስልክ ቁጥር
- በእንግሊዝኛ የሚፈልጉትን ቋንቋ
- ከኪራይ ጋር የተያያዘ ጥያቄዎች እንዳሎት ይንገሩን
የአማርኛ ተናጋሪ ሠራተኛ ጥሪዎን በተቻለ ፍጥነት ይመልሳሉ።
በዋሽንግተን ስቴት እና በሲያትል ከተማ የንግዶች ማፈናቀል እገዳ ማጠቃለያ
የሲያትል ከተማ:
- ማርች 17, 2020 - ሴፕቴምበር 30, 2021 ድረስ በአነስተኛ ንግድ ፣ በመኖሪያ እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ማፈናቀል ላይ ጊዜያዊ እገዳ አለ
- አነስተኛ የንግድ ሥራዎችን እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን ኪራይ ባለመክፈላቸው ምክንያት የቤት አከራዮች ማስወጣት አይችሉም
- አከራዮች ወደ የክፍያ ዕቅድ ውስጥ ለመግባት ወይም ከትናንሽ ንግዶች እና ለትርፍ ላልሆኑ ድርጅቶች ጋር ወደ ስምምነት ለመግባት ግዴታ አለባቸው
- የCOVID-19 ድንገተኝነት እስከሚያበቃ ድረስ አከራዮች ለአነስተኛ ንግድ ወይም ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅቶች ላይ ኪራይ ሊጨምሩ አይችሉም
- ተከራዮች በአንድ ዓመት ውስጥ ኪራዩን መልሰው መክፈል አለባቸው
- ባለንብረቶች የዘግይተው ክፍያ ቅጣት ፣ ወለድ ወይም ሌሎች ክፍያዎችን ማስከፈል አይችሉም
ኪንግ ካውንቲ:
- ከመጋቢት 18, ጀምሮ እንስካልተወሰነ ጊዜ የኪንግ ካውንቲ የሸሪፍ ቢሮ መኖሪያ ቤት ኪራይ ፣ ንግድ ቤት ወይም የቤት ወርሃዊ ብድር ክፍያ ባለመከፈሉ አይስወጣም።
ኃላፊነትን የማውረድ
ይህ መረጃ እና ለኪራይ ማሻሻያ መሣሪያ ሰነድ የተፈጠሩ የሰነድ አብነቶች ለህጋዊ ወይም ለንግድ ምክር ሳይሆን ለትምህርታዊ ዓላማዎች የታሰቡ ናቸው። በእናንተ ሁኔታ ላይ ህጉ እንዴት መተርጎም እንዳለበት ምክር ለማግኘት ሁልግዜ ጠበቃ ማማከር ጥሩ ሃሳብ ነው ፡፡ እንዲሁም በገንዘብ ወይም ንግድ ጥያቄዎች ላይ የሂሳብ ባለሙያ ማማከሩ ጥሩ ሀሳብ ነው።