በ 8/6/2025 ተዘምኗል
የሱቅ ፊት ለፊት ጥገና የገንዘብ ድጋፍ እስከ ሶስት (3) ለሚደርሱ የተለያዩ አደጋዎች የንብረት ውድመት ለመጠገን የንግድ ባለቤቶች የሚያወጡትን ወጪ ይመልሳል። የሚመለሰው ገንዘብ ለአንድ ክስተት እስከ 3,000 ዶላር የሚደርስ ወጪን ይሸፍናል። ማመልከቻዎች እስከ ታህሳስ 2025 ድረስ ክፍት ናቸው ፣ ወይም ገንዘብ እስከሚያልቅ ድረስ ።
በአንድ ማመልከቻ ውስጥ ከአንድ በላይ የገንዘብ ስጦታ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ ነገር ግን እያንዳንዱ የገንዘብ ስጦታ በተለየ ቀን ለተከሰተ የተለየ ክስተት መሆን አለበት። ቀደም ሲል የገንዘብ ስጦታ የተቀበሉ የንግድ ባለቤት ከሆኑ፣ ነገር ግን ሌላ ብቁ የሆነ ክስተት ከተፈጠረ፣ እንደገና እንዲያመለክቱ እናበረታታዎታለን።
ብቁ የሆነ የሱቅ ፊት ለፊት ንብረት ላይ የሚደርሰው ጉዳት የሚከተሉትን ያጠቃልላል ነገር ግን በእነዚህ ብቻ አይወሰንም፦
- በሮች
- መቆለፊያዎች
- አጥሮች
- የግቢ በሮች
- ምልክቶች
- የተሰበሩ ወይም የተጫሩ መስኮቶች
ለእርዳታ ብቁ ለመሆን ጉዳቱ በሀምሌ 1፣ 2024 ላይ ወይም ከዛ በኋላ የደረሰ መሆን አለበት። የገንዘብ ድጎማዎች የተሰረቁ ዕቃዎችን ወይም የግድግዳ ላይ ሕገወጥ ጽሑፎችን ወይም ስዕሎችን አይሸፍኑም።
ማመልከቻዎች እስከ ታህሳስ 2025 ድረስ ክፍት ናቸው ፣ ወይም ገንዘብ እስከሚያልቅ ድረስ ።
እባክዎ ከማመልከትዎ በፊት ሙሉውን የብቃት መስፈርት፣ አስፈላጊ ሰነዶችን እና ሌሎች መረጃዎችን ይመልከቱ። ከማመልከትዎ በፊት ይህንን ሰነድ ከማመልከቻው ጋር አብረው ማየት ይችላሉ፦ ወደ ንግድ መመለስ ፈንድ ማመልከቻ የጥያቄዎች መመሪያ።
ጽ/ቤታችን ሁሉም ማህበረሰቦች የኢኮኖሚ ዕድሎችን እንዲያገኙ በማረጋገጥ በሲያትል ውስጥ ለሁሉም ሰው ተስማሚ የሆነ ተደራሽ እና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው።
የሲያትል ከተማ፣ እያንዳንዱን ሰው በፕሮግራሞቹ እና በእንቅስቃሴዎቹ እንዲሳተፍ ያበረታታል። እርዳታ፣ ትርጉም፣ ለአካል ጉዳተኞች የሚደረጉ ማስተካከያዎች ወይም በተለየ ቅርጸት የተዘጋጁ ሰነዶች ከፈለጉ፣ ቢሯችንን በ206-684-8090 ወይም በOED@seattle.gov ያነጋግሩ።
ወደ አንድ ክፍል ይዝለሉ
የብቁነት መስፈርቶች
ለሱቅ ፊት ለፊት ጥገና ፈንድ ብቁ ለመሆን፣ ብቁ ንግዶች የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው፡-
- በሀምሌ 1፣ 2024 ላይ ወይም በኋላ በሱቃቸው ፊት ላይ አካላዊ ጉዳት የደርሰባቸው።
- መሳሪያ የገዙ እና/ወይም ለጥገናዎች የከፈሉ።
- የሱቅ ፊት ለፊት ጥገና ፈንድ የሚሠራው መልሶ በመክፈል ሞዴል ነው፣ ይህ ማለት እርስዎ አስቀድመው ገዝተዋል እና/ወይም ለጥገና ከፍለዋል ማለት ነው።
- ለግዢዎች እና/ወይም ለተጠናቀቁ ጥገናዎች ደረሰኞች ማቅረብ።
- ግምቶች እና/ወይም የዋጋ ጥቅሶች ተቀባይነት አይኖራቸውም ።
- አሁን ላይ የሚሰራ/ቀኑ ያላለፈበት የሲያትል የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው መሆን።
- ሁሉንም የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ ህጎች እና ደንቦችን ማክበር።
- በሲያትል ከተማ ወሰኖች ውስጥ መገኘት።
- በገለልተኛ ባለቤት የተያዘና የሰንሰለት ንግድ ያልሆነ።
- በገለልተኛ ባለቤትነት የተያዙ ፍራንቻይዝ ንግዶችም ለማመልከት ብቁ ናቸው።
- ለትርፍ የተቋቋመ ንግድ ወይም ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም፣ 501(c)(3)፣ 501(c)(6)፣ ወይም 501(c)(9) መሆን።
- ከሶስት (3) የማይበልጡ ቦታዎች ይኑርዎት።
- በአሁኑ ጊዜ ለንግድ ክፍት እና በመንቀሳቀስ ላይ ያለ።
ተጨማሪ መመዘኛዎች፦
- ለአንድ ንግድ፣ የንግድ ባለቤት፣ EIN፣ SSN፣ UBI ቁጥር፣ ንግድ ፈቃድ ቁጥር፣ ለቤት እና/ወይም ለንግድ አድራሻ ከሶስት (3) በላይ ክስተቶች መቅረብ አይችሉም። በአንድ ማመልከቻ ውስጥ ከአንድ በላይ የገንዘብ ፈንድ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ ነገር ግን እያንዳንዱ የገንዘብ ፈንድ በተለየ ቀን ለተከሰተ የተለየ ክስተት መሆን አለበት።
- ንግዱ ማመልከቻው ከገባበት ቀን በፊት ቢያንስ ለ12 ወራት ሲሠራ የቆየ መሆን አለበት።
- ንግዱ በአንድ ህዝቡን የሚያገለግል አካላዊ መገኛ ቦታ እና/ወይም በተንቀሳቃሽ የጭነት መኪናዎች ላይ ሆኖ የሚሰራ መሆን አለበት።
- የይገባኛል ጥያቄው ውድቅ ካልተደረገ እና ካልተዘጋ በስተቀር የገንዘብ ፈንዶች እንደ የይገባኛል ጥያቄ አካል ወደ ኢንሹራንስ የሚገቡትን ማንኛውንም ጉዳቶች አይሸፍኑም።
- ከተሰጣቸው፣ ንግዶች W-9 መሙላት አለባቸው።
የንግድ መጠንን የሚመለከቱ መስፈርቶች፦
- ንግዱ ከ50 የማይበልጡ የሙሉ ጊዜ አቻ ሰራተኞች ሊኖሩት ይገባል።
- ለሲያትል ከተማ የፋይናንስ እና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች መምሪያ በ2024በንግድ እና ሥራ (Business and Occupation) ግብሮች ላይ ሪፖርት በተደረገው መሠረት የንግዱ ዓመታዊ የተጣራ ገቢ ከ$1,000 ዶላር በላይ የሚሠራ እና ከ$7,000,000 ዶላር የማይበልጥ መሆን አለበት።
ለሱቅ የፊት ለፊት ጥገና የድጋፍ ገንዘብ (Storefront Repair Fund) ለማመልከት ብቁ ያልሆኑ ንግዶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
- ከኪንግ ካውንቲ ጋር ባልተካለለ አካባቢ ውስጥ የሚገኝ የንግድ ተቋም።
- በሲያትል ማዘጋጃ ቤት ኮድ 6.270 ሥር "የአዋቂ መዝናኛ" ተብለው የሚተዳደሩ ንግዶች።
- ንግዱ የአጭር ወይም የረጅም ጊዜ የኪራይ ወይም የኢንቨስትመንት ንብረት ነው (የግል ሪል እስቴት እና ገለልተኛ ሪልተሮችን (independent realtors)፣ የአጭር ጊዜ ኪራዮች ኤርቢኤንቢን (Airbnb)፣ ቨርቦን (Vrbo)፣ ወዘተ ያካትታሉ)።
- ንግዱ የታክሲ ስራ፣ በጋራ መሣፈር (ራይድሼር)፣ ወይም የምግብ ማድረስ አገልግሎት (ለምሳሌ እንደ ኡበር፣ ሊፍት፣ የሎ ካቢ፣ ዶር ዳሽ፣ ኡበር ኢትስ፣ ወዘተ) የሆነ።
ለማመልከቻ አስፈላጊ ሰነዶች
የሱቅ ፊት ለፊት ጥገና ፈንድ ማመልከቻዎች በኢንተርኔት ላይ እንደገቡ ተቀባይነት ያገኛሉ፣ ይታያሉ እና ይስተናገዳሉ።
ከማመልከትዎ በፊት ይህንን ሰነድ ከማመልከቻው ጋር አብረው ማየት ይችላሉ፦ ወደ ንግድ መመለስ ፈንድ ማመልከቻ የጥያቄዎች መመሪያ።
ብቁ አመልካቾች ማመልከቻቸውን ለማስገባት የሚከተለው መረጃ ያስፈልጓቸዋል፦
- የተዋሃደ የንግድ መታወቂያ (Unified Business Identifier) ቁጥር (ዘጠኝ አሃዞች)።
- ለዋሽንግተን ስቴት የንግድ ፍቃድ ሲያመለክቱ የተዋሃደ የንግድ መለያ ቁጥር ያገኛሉ። አመልካቾች የUBI ቁጥራቸውን በኢንተርኔት ላይ በዋሽንግተን ስቴት የገቢዎች መምሪያ (Washington State Department of Revenue) በኩል መፈለግ ይችላሉ።
- የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር (ከአራት እስከ ስድስት አሃዞች)።
- በሲያትል ውስጥ የንግድ ሥራ እየሰሩ ከሆነ፣ የሲያትል ንግድ ፈቃድ የግብር ምስክር ወረቀት ሊኖርዎት ይገባል፣ ይህ የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር (City Business License Number) በመባልም ይታወቃል። ይህንን የምስክር ወረቀት በየዓመቱ ከታህሳስ31 በፊት ማደስ አለብዎት።
- ይህ የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር ከዋሽንግተን ስቴት የንግድ ፍቃድ የተለየ ነው። ቁጥርዎን በከተማ ንግድ ፍቃድ የንግድ ፍለጋ መሳሪያ ላይ ማግኘት ካልቻሉ የዋሽንግተን ስቴት ፍቃድ ብቻ ሊኖርዎት ይችላል።
- ለከተማ ንግድ ፈቃድ ማመልከት እና በኢንተርኔት ላይ በ filelocal-wa.gov ወይም በፖስታ ማደስ ይችላሉ።
- ለመሳሪያ ግዢ እና/ወይም ጥገና ክፍያ ማረጋገጫ።
- ለመሳሪያ ግዢ ወይም ለተጠናቀቁ ጥገናዎች የደረሰኞች ቅጂዎች ያቅርቡ።
- ግምቶች እና/ወይም የዋጋ ጥቅሶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- የሱቅ ፊት ለፊት ጥገና ፈንድ የሚሠራው መልሶ በመክፈል ሞዴል ነው፣ ይህ ማለት አመልካቾች አስቀድመው ገዝተዋል እና/ወይም ለጥገና ከፍለዋል ማለት ነው።
- የሲያትል ፖሊስ መምሪያ ክስተት ቁጥር። በሲያትል ፖሊስ መምሪያ ድረገጽ ላይ የፖሊስ ሪፖርት በማቅረብ የክስተት ቁጥር ማግኘት ይችላሉ።
- አማራጭ፦ የንብረት ውድመት ማረጋገጫ።
- አመልካቾች ከፈለጉ የንብረት ውድመት ፎቶግራፎችን መጫን ይችላሉ።
- የንብረት ውድመት ማረጋገጫ በአማራጭ የሚቀርብ ነው።
የማመልከቻ እገዛ
የሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ ማመልከቻ በኢንተርኔት ላይ በእንግሊዝኛ መቅረብ አለበት።
የጽሑፍ ትርጉም ወይም የቃል ትርጉም ድጋፍ
ጥያቄዎችን ለመመለስ እና ማመልከቻዎን እንዲያጠናቅቁ ለመርዳት ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሰራተኞች አሉን።
የጽሑፍ ትርጉም ወይም የቃል አስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለመጠየቅ፣ እባክዎን በ(206) 684-8090 ይደውሉ። እባክዎ የእርስዎን ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ ተመራጭ ቋንቋ እና የተፈለገውን የድጋፍ ዓይነት የያዘ የድምጽ መልዕክት ይተዉ።
በማመልከቻው ላይ ተጨማሪ እገዛ
ጽ/ቤታችን ሁሉም ማህበረሰቦች የኢኮኖሚ ዕድሎችን እንዲያገኙ በማረጋገጥ በሲያትል ውስጥ ለሁሉም ሰው ተስማሚ የሆነ ተደራሽ እና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው። እርዳታ፣ ትርጉም፣ ለአካል ጉዳተኞች የሚደረጉ ማስተካከያዎች ወይም በተለየ ቅርጸት የተዘጋጁ ሰነዶች ከፈለጉ፣ ቢሯችንን በ206-684-8090 ወይም በOED@seattle.gov ያነጋግሩ።
በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች
1. በሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ እና ሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
የሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ በብልሽት ወይም በሌላ ንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በማካካስ ይረዳል።
የሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ የመከላከያ የደህንነት እርምጃዎችን ለማስመለስ ይረዳል። ስለ የሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ የበለጠ ይወቁ።
2. የሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ ድጎማዎች የሱቅ የፊት ለፊት ገፅታዎችን ለመጠገን ብቻ የተገደቡ ናቸው፣ ለምሳሌ መስኮቶችን እና በሮች ብቻ መተካት?
የገንዘብ ድጋፍ በሱቅ ፊት ለፊት ለሚደርስ ጉዳት ጥገና እና ለእነዚያ ጥገናዎች ክፍያ ብቻ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ብቁ የሆኑ ጉዳቶች የተሰበሩ መስኮቶችን ወይም በመስኮቶች ላይ መጫርን፣ የተሰበሩ በሮችን፣ የተሰበሩ መቆለፊያዎችን፣ የተሰበሩ ምልክቶችን፣ የተሰበሩ አጥሮችን እና የተሰበሩ የግቢ በሮችን ያጠቃልላል። ገንዘቡ የመከላከያ እርምጃዎችን፣ ሕገወጥ የግድግዳ ጽሑፎችን ማስወገድን፣ ቀለም መቀባትን፣ የደህንነት ካሜራዎችን ግዢ ወይም የተሰረቁ እቃዎች መጥፋትን አይሸፍንም።
አስቀድሞ መከላከያ የደህንነት እርምጃዎች ለሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ለማመልከት ከፈለጉ፣ የሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድን ይመልከቱ።
ሕገወጥ የግድግዳ ጽሑ በሕዝብ ቦታ ላይ ወይም በግል ንበረት ላይ ካዩ በሚከተለው ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ፦
- አግኝ/አስተካክል (Find It/Fix It) መተግበሪያን፣ የኢንተርኔት ላይ የሪፖርት ቅጹን በመጠቀም ወይም ወደ ከተማው የግራፊቲ ሪፖርት መስመር ጋር በ(206) 684-7587 በመደወል።
- በግል ንብረት ላይ ለሚጻፉ ሕገወጥ ጽሑፎች፣ የንብረቱ ባለቤቶች ጽሑፎችን የማስወገድ ኃላፊነት አለባቸው። ነገር ግን፣ ባለቤቱ ሕገወጥ ጽሁፉን ለማስወገድ ከከተማው እርዳታ ከፈለገ፣ ሕገወጥ ጽሁፎችን በነጻ ለማስወገድ የፈቃድ እና የመልቀቂያ ቅጹን መሙላት ይችላሉ።
ስለ ሕገወጥ ጽሑፍ መወገድ እና መቀነስ ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን የሕገወጥ ጽሑፍ መከላከያ እና ማስወገድ መጽሔቱን ይመልከቱ።
3. የሱቅ ፊት ለፊት ጥገና የገንዘብ ድጎማዎች ለጥገና እስከ 3,000 ዶላር ይከፍላሉ ። በልዩ ሁኔታዎች ለምሳሌ ከመጠን በላይ ጉዳት በሚደርስበት ጊዜ የገንዘብ ድጎማው ከዚህ ገደብ በላይ የመሆን ዕድል ይኖረዋል?
አንዳንድ ንግዶች ከ3,000 ዶላር በላይ የሚደርስ ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል እንገነዘባለን። ሆኖም ከተማዋ በተቻለ መጠን ብዙ ንግዶችን መርዳት እንድትችል እርዳታዎች በ3,000 ዶላር ብቻ የተገደቡ ይሆናሉ። ገንዘብ ካለ ንግዶች ብዙ የሱቅ ፊት ለፊት ውድመት ካጋጠማቸው እስከ ሶስት የገንዘብ ድጎማዎችን ማመልከት ይችላሉ። ለሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ድጎማ ብቁ ለመሆን ክስተቶቹ በተለያዩ ቀናት የተከሰቱ መሆን አለባቸው።
4. ምን ዓይነት ንግዶች ናቸው ለዚህ የገንዘብ ድጋፍ ብቁ የሆኑት?
አትራፊ ንግዶች ወይም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተቋሞች 501(c)(3)፣ 501(c)(6)፣ ወይም 501(c)(19)፣ በአካል መሬት ላይ ያሉ ሕዝብን የሚያገለግሉ ሱቆች እና የምግብ መኪናዎች ለሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ ብቁ ናቸው። ሁሉም አመልካቾች ወቅታዊ የሲያትል ንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል።
5. የገንዘብ ተቀባዮች እንዴት ነው የሚመረጡት?
ማመልከቻዎችን እንዳመጣጣቸው እየገመገምን እናስተናግዳለን። ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ያጋጠማቸው አነስተኛ ንግዶችን ለመርዳት ለሚከተሉት ቡድኖች ቅድሚያ እንሰጣለን፦
- በጥቁር፣ በአገሬው ተወላጆች እና በባለ ቀለም ሰዎች ባለቤትነት የተያዙ አነስተኛ ንግዶች።
- በሴት ባለቤትነት የተያዙ አነስተኛ ንግዶች።
- በጣም በሕዝብ ቆጠራ የተጨናነቀ፣ ቢያንስ 30% ድህነት ወይም ከ60% መካከለኛ ገቢ ያልበለጠ ቦታ ውስጥ የሚገኙ አነስተኛ ንግዶች። ማሳሰቢያ፡- እነዚህ አካባቢዎች የአነስተኛ ንግድ አስተዳደርን የ" ዝቅተኛ ገቢ ማህበረሰቦችን" ፍች ያሟላሉ።
ማሳሰቢያ፦ ሰራተኞቻችን አመልካቾችን በ206 ኤሪያ ኮድ ስልክ ወይም በ@seattle.gov በሚያልቅ ኢሜል ያነጋግራሉ። ንግዶች የሰራተኞቹን ማንነት በ (206) 684-8090 ወደ ቢሯችን በመደወል ማጣራት ይችላሉ።
6. የፖሊስ ሪፖርት እንዴት ማቅረብ እችላለሁ?
የፖሊስ ሪፖርት በ9-1-1 በመደወል ወይም በኢንተርኔት ላይ የወንጀል ሪፖርት ማድረጊያ ድረገጽ በኩል ማቅረብ ይችላሉ። ማመልከቻው በሚገባበት ወቅት የፖሊስ ሪፖርት ክስተት ቁጥርዎን ከሚያስፈልጉት ሰነዶች ውስጥ እንደ አንዱ ማቅረብ አለብዎት።
7. ተሸላሚዎች ገንዘቡን መልሰው መክፈል አለባቸው?
አይ፣ ይህ ስጦታ ነው። የንግድ ድርጅቶች ገንዘቡን መመለስ አይጠበቅባቸውም።
8. ድጎማዎቹ እንደ ታክስ ገቢ ይቆጠራሉ?
አይ፣ ድጎማዎቹ ታክስ የሚከፈልባቸው ገቢዎች አይደሉም።
9. የትርፍ ሰዓት ሰራተኞች እንደ ተቀጣሪዎች ይቆጠራሉ?
አዎ፣ በደመወዝ ላይ ያለ ማንኛውም ሰው እንደ ሰራተኛ ይቆጠራል።
10. ወደ ንግድ ሥራ መመለስ ፕሮግራም የገንዘብ ምንጭ ምንድን ነው?
የሱቅ ፊት ጥገና ፈንድ የሚሸፈነው በደመወዝ ወጭ ታክስ (Payroll Expense Tax) ነው።
11. አመልካቾች አንድ ነገር ከመግዛታቸው በፊት ገንዘቡን ማግኘት ይችላሉ?
አይ። ወደ ንግድ ሥራ መመለስ ፕሮግራም የሚሠራው በማካካሻ ሞዴል ነው፣ ይህም ማለት አመልካቾች አስቀድመው መሣሪያዎችን ገዝተዋል ወይም ለጥገና ክፍያ ከፍለዋል ማለት ነው።
12. አመልካቾች ገንዘቡን እንዴት ነው የሚያገኙት?
ብቁ አመልካቾች ቼክ በፖስታ ይላክላቸዋል። አስፈላጊ ከሆነ ቼኮችን በአካል የመቀበል አማራጭ ይኖርዎታል።