የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ
የሲያትል ከተማ ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ማመልከቻዎችን ከአሁን በኋላ አይቀበልም።
በአነስተኛ ንግድ የማረጋጊያ ፈንድ በኩል የገንዘብ ስጦታዎችን በማድረግ በኮቪድ-19 (COVID-19) አሉታዊ ተፅእኖ የደረሰባቸውን ጥቃቅን እና አነስተኛ ንግዶችን ለማረጋጋት የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት ተጨማሪ $4 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት እያደረገ ነው። በአሜሪካ የነፍስ አድን ዕቅድ ሕግ (ARPA)፣ መሠረት በተቋቋመው የኮሮናቫይረስ አካባቢያዊ የገንዘብ ማገገሚያ ፈንድ (CLFR) የተደገፈው የማረጋጊያ ፈንድ እንደ ኪራይ፣ ደመወዝ፣ መሣሪያ እና ሌሎችም ባሉ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች ላይ ጥቅም ላይ እንዲውል $5,000 ዶላር፣ $10,000 ዶላር እና $20,000 ዶላር እርዳታዎችን ይሰጣል።
ለዚህ አዲስ ዙር የማረጋጊያ ፈንድ እስከ 50 የሙሉ ጊዜ አቻ ሠራተኞች ያላቸውን አነስተኛ ንግዶችን ይደግፋል እንዲሁም ባለፉት ዙሮች የማረጋጊያ ፈንድ ስጦታ አግኝተውም ክሆነ የነሱንም ማመልከቻዎች ይቀበላል። ሁሉም ብቁ አመልካቾች፣ ቀደምት ተሸላሚዎች እና ቀደም ሲል ያመለከቱ ንግዶችን ጨምሮ የኦንላይን ማመልከቻ ማስገባት አለባቸው።
እስከዛሬ ድረስ የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት በመላው ሲያትል በተከሰተው ወረርሽኝ የኢኮኖሚ ውድቀት ለተጎዱ እስከ 1,500 የሚጠጉ አነስተኛ ንግዶች በአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ በኩል ከ$10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ አበርክቷል።
ከጥቅምት 25 ጀምሮ፣ ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በኪንግ ካውንቲ ውስጥ የተወሰኑ የቤት ውስጥ እና የውጭ ዝግጅቶችን እና ተቋማትን ለመግባት ሙሉ የ COVID-19 ክትባት ማረጋገጫ ወይም አሉታዊ የሙከራ ውጤት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። ተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖዎችን ለማካካስ እንዲያግዝ ይህ ደንብ ለማስፈፀም ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ማመልከት በሚፈለጉ ንግዶች እና ድርጅቶች ይህንን ደንብ መተግበር፣ እና በሚከተሉት ዘርፎች ውስጥ ያሉ ትናንሽ ንግዶች እና ድርጅቶች እስከ $1,000 ዶላር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ብቁ ይሆናሉ። የንግድ ድርጅቶች የተለየ ማመልከቻ ማስገባት አይጠበቅባቸውም።
ለዚህ ተጨማሪ ገንዘብ ዘርፎች ምግብ ቤቶችን፣ የተውነት ጥበቦች እና የባህል ተቋማትን፣ የምሽት ህይወት ቦታዎችን እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ/የቤት ውስጥ እንቅስቃሴ መዝናኛ ቦታዎችን (እንደ የቦውሊንግ ማንከባለልያ፣ ጂም፣ የጨዋታ መገልገያዎች፣ ወዘተ) ያካትታሉ።
ብቁነት
ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ብቁ ለመሆን ብቁ የሆኑ ንግዶች መሆን ያለባቸው:
- በCOVID-19 ወረርሽኙ ምክንያት እንደ የንግድ መቋረጦች ወይም መዘጋቶች ያሉ እና ተዛማጅ የጤና እና ደህንነት ገደቦች የተጐዱ።
- አሁን የሚሠራ የሲያትል የንግድ ሥራ ፈቃድ ያልዎት።
- የከተማ የንግድ እና ሙያ (B&O) ግብሮችን አስገብተው እና ዕዳ ካለባቸው ግብራቸውን ሙሉ በሙሉ የከፈሉ።
- ሁሉንም የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ ህጎች እና ደንቦችን አክብረው የተገኙ።
- በአንድ ንግድ፣ አድራሻ፣ ቤተሰብ፣ የሰራተኛ መለያ ቁጥር (EIN)፣ ወጥ የሆነ የንግድ መታወቂያ ቁጥር (UBI) እና/ወይም የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር አንድ ማመልከቻ ብቻ ያስገቡ።
ቦታ:
- በሲያትል ከተማ ወሰኖች ውስጥ ያሉ።
- በቀረበው የንግድ እና ሙያ (B&O) የግብር ተመላሾች በኩል በሚረጋገጠው፣ አካላዊ አድራሻ እና በሲያትል ውስጥ የሚሠራ ያለው። የንግድዎ የግብር ተመላሾች የሲያትል አድራሻውን ካልጠቀሰው፣ ብቁ እንዳልሆኑ ይቆጠራሉ።
- የተለየ ሁኔታ: የፈጠራ ሠራተኞች፣ የጭነት የምግብ መኪኖች እና የአርሶ አደሮች ገበያ ሻጮች። እነዚህ ንግዶች በአሁኑ ጊዜ በሲያትል ከተማ ውስጥ የንግድ ሥራ መሥራት እና በጣም ተደጋጋሚ የሆነውን የሲያትል አድራሻቸውን ማቅረብ አለባቸው።
- ከሁለት ቦታዎች ያልበለጠ ያላቸው።
መጠን:
- እስከ 50 የሚደርሱ የሙሉ ጊዜ አቻ ሠራተኞች ያለው።
- እስከ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ($2,000,000 ዶላር)፣ ነገር ግን ቢያንስ አንድ ሺህ ዶላር ($1,000 ዶላር) በዓመት የተጣራ ገቢ ያለው፣ ብቸኛ ባለቤት፣ ሲ (C)-ኮርፖሬሽን፣ ኤስ (S)-ኮርፖሬሽን፣ የጋርዮሽ ንግድ፣ ወይም የውስን ተጠያቂነት የጋርዮሽ ኩባንያ የሆነ።
- የሲያትል ፋይናንስ እና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች መምሪያ ይህንን ኪሳራ በንግድ ሥራው የ2019 እና 2020 የንግድ እና ሙያ (B&O) ግብሮች ውስጥ የገቢ ዘገባ በኩል ይወስናል።
ክወናዎች:
- በአሁኑ ጊዜ ለንግድ ክፍት እና የሚሠራ ይሁኑ።
- ከጥቅምት 19 ቀን 2019 በፊት መሥራት የጀመረ።
- በግል ባለቤትነት የተያዘ፣ ልዩ የመሸጥ ፈቃድ ያልሆነ (non-franchise) እና ሰንሰለት-አልባ የሆነ ንግድ።
የገቢ ኪሳራ:
- በከተማ የንግድ እና ሥራ (B&O) መረጃ መሠረት የተተገበረውን ዓመታዊ የተጣራ ኪሳራ ወይም ጠቅላላ የእርዳታ ስጦታውን መጠን የሚበልጥ ያለው።
ለትርፍ ያልተቋቋመ አካላት ተጨማሪ መመዘኛዎች:
- የተውነት ጥበባት፣ የባህላዊ ተቋም ወይም የንግድ ቴክኒካዊ ድጋፍ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሆነ።
- ከዋሽንግተን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር የሚሠራ ለትርፍ ያልተቋቋመ የአቋም ሁኔታ ያለው።
ብቁ ያልሆኑ አመልካቾች
ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ለማመልከት ብቁ ያልሆኑ ንግዶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
- ባልተቋቋመ የኪንግ ካውንቲ ውስጥ የሚገኙ ንግዶች።
- ንግዶቹ በፌዴራል፣ በክልል ወይም በአከባቢ ሕግ ሥር/ መሠረት በማንኛውም ሕገ-ወጥ በሆነ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሰማራ።
- በሲያትል ማዘጋጃ ቤት ኮድ270 መሠረት “የአዋቂዎች መዝናኛ” ንግዶች።
- የሀሺሽ ዕጽ (Cannabis) ሱቆች፣ አብቃዎች እና ማከፋፈያዎች።
- የሚከተሉት የ1099 ገለልተኛ ተቋራጮች:
- የአጭር ወይም የረጅም ጊዜ የኪራይ ባለቤቶች ወይም የኢንቨስትመንት ንብረት (Airbnb፣ Vrbo፣ ወዘተ ጨምሮ)።
- የግል ሰፊ የቤት ሕንፃ (ገለልተኛ አከራዮች)።
- የተሳፋሪ አክሲዮኖችን፣ ታክሲዎችን፣ የምግብ ማቅረቢያ አገልግሎትን እና (እንደ ኡበር፣ ሊፍት፣ ቢጫ ካቢ፣ የበር ዳሽ (Door Dash)፣ የኡበር ምግቦች፣ ወዘተ ያሉ) የመኪና አገልግሎቶችን
- ከሥነ ጥበብ፣ የባህል ተቋማት እና የንግድ ቴክኒካዊ ድጋፍ ሰጪ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች በስተቀር ለትርፍ ያልተቋቋሙ የ501 (c)(3)፣ 501 (c)(6) ወይም 501 (c)(19) አካላት።
አስፈላጊ ሰነድ
ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ለማመልከት ፍላጎት ያላቸው አነስተኛ ንግዶች ለድጎማው ብቁ ለመሆን የከተማ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ እና ሙያ (B&O) የግብር መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው። ብቁ አመልካቾች ማመልከቻቸውን ለማቅረብ የሚከተሉት ሰነዶች ያስፈልጓቸዋል።
- ወጥ የሆነ የንግድ መለያ መታወቂያ (UBI) ቁጥር (ዘጠኝ አሃዞች)።
- ለዋሽንግተን ስቴት የንግድ ፈቃድ ሲያመለክቱ ንግዶች አንድ ወጥ የሆነ የንግድ መለያ መታወቂያ (UBI) ቁጥር ያገኛሉ። ይህ በገቢ መምሪያ በኩል በኦንላይን ወይም በፖስታ መላላኪያ በኩል ሊከናወን ይችላል። አመልካቾች በdor.wa.gov/businessesላይ ወጥ የሆነ የንግድ መለያ መታወቂያ ቁጥራቸውን በመስመር ላይ መፈለግ ይችላሉ።
- የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር (ስድስት አሃዞች)።
- በሲያትል ውስጥ የንግድ ሥራ የሚሠራ ማንኛውም ሰው የሲያትል የንግድ ፈቃድ ግብር፣ እንዲሁም የከተማ የንግድ ፈቃድ ቁጥር፣ የከተማ ደንበኛ ቁጥር ወይም አጠቃላይ የንግድ ፈቃድ በመባል የሚታወቅ የምስክር ወረቀት ሊኖረው ይገባል። የንግድ ባለቤቶች ይህንን የምስክር ወረቀት በየዓመቱ እስከ ታህሳስ 31 ድረስ ማደስ አለባቸው።
- ይህ የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር ከዋሽንግተን ስቴት የንግድ ፈቃድ የተለየ ነው። ንግዶች ቁጥራቸውን በከተማ ንግድ ፈቃድ ላይ ማግኘት ካልቻሉ የንግድ ፍለጋ መሣሪያን ያግኙ፣ የዋሽንግተን ስቴት ፈቃድ ብቻ ኖሮዋቸው ይቻል ይሆናል። ለማጣቀሻ እያንዳንዱ ፈቃድ ምን እንደሚመስል ከዚህ በታች ይመልከቱ።
- ንግዶች ለከተማ ንግድ ፈቃድ በ filelocal-wa.gov በኦንላይን ወይም በፖስታ ማመልከት እና ማደስ ይችላሉ።
- የንግድ እና ሙያ (B&O) ግብሮች።
- ምንም ዓይነት የሥራ እንቅስቃሴ ባይኖር ወይም ምንም ዓይነት የግብር ዕዳ ባይኖርበትም እያንዳንዱ ንግድ ለከተማው ፋይል እና ሪፖርት ማድረግ አለበት። የሲያትል የንግድ ግብር ከዋሽንግተን ስቴት የንግድ ግብር ጋር ተመሳሳይ አይደለም፤ የንግድ ድርጅቶች የሲያትል ታክስን ከስቴቱ ግብሮች ለይተው ለየብቻ ፋይል ማድረግ አለባቸው።
- ዓመታዊ ግብር የሚከፈልበት ጠቅላላ ገቢ ከ $100,000 ዶላር በታች ከሆነ ንግዶች አጠቃላይ የንግድ እና ሙያ (B&O) ግብር አይኖራቸውም፣ ነገር ግን ንግዶች አሁንም ፋይል ማድረግ አለባቸው።
- ንግዶች filelocal-wa.gov ላይ በመስመር ወይም በፖስታ ፋይል ማድረግ እና ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ስለእነዚህ ግብሮች ተጨማሪ ጥያቄዎች፣ ንግዶች ወደ ሲያትል ፋይናንስ በ Tax@seattle.gov መድረስ ይችላሉ።
ማመልከቻ ድጋፍ
የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ይህንን ብቁ አመልካቾችን ማመልከቻ በማጠናቀቅ ለመደገፍ የቴክኒክ ድጋፍ፣ የቋንቋ ተደራሽነት አገልግሎቶች፣ የአካል ጉዳተኞች የመስተናገጃ ቦታዎችን፣ በተለዋጭ ቅርፀቶች ቁሳቁሶችን እና ስለ ተደራሽነት መረጃ ይሰጣል። ንግዶች በ (206) 684-8090 በመደወል ወይም oed@seattle.gov ኢሜይል በማድረግ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።
ማመልከቻው በስምንት ቋንቋዎች ይገኛል። የሁለት ቋንቋ ድጋፍ በአማርኛ፣ በቻይንኛ፣ በኮሪያኛ፣ በሶማሌኛ፣ በስፓኒሽ፣ በታይ እና በቬትናምኛ ይገኛል። የጽሑፍ ትርጉም ወይም የቃል ትርጓም አገልግሎቶችን ለመጠየቅ፣ ንግዶች በ (206) 684-8090 በመደወል የሚከተለውን መረጃ በድምጽ መልዕክቶቻቸው ውስጥ: ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ ተመራጭ ቋንቋ እና የሚያስፈልገውን የድጋፍ ዓይነት ማስታወሻ መተው ይችላሉ። አንድ ሰራተኛ በተቻለ ፍጥነት ጥሪዎን ይመልሳል።
ማመልከቻዎች ሁሉ በማመልከቻው ቀነ-ገደብ በኦንላይን ማመልከቻ መግቢያ በኩል መቅረብ አለባቸው። በኢሜይል ወይም በፖስታ የሚላኩ ማመልከቻዎች አይታሰቡም። የኮምፒተር ወይም አስተማማኝ በይነመረብ መዳረሻ ከሌለዎት፣ እባክዎን የሠራተኛ አባል እንዲያግዝዎ ማመልከቻዎች ከመዘጋታቸው ከሦስት የሥራ ቀናት በፊት የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤቱን ያግኙ። እንዲሁም ለኮምፒዩተር እና ለበይነመረብ መዳረሻ ማንኛውንም የሲያትል የህዝብ ቤተመጽሐፍት ቅርንጫፍ ሥፍራ መጎብኘት ይችላሉ።
የመረጃ ክፍለ-ጊዜዎች
የአነስተኛ ንግድ ልማት ቡድን እንዴት ለመረጋጋት ፈንድ ማመልከት እንደሚቻል ላይ ጥቅምት 21 ቀን ከምሽቱ 2 ሰዓት ምናባዊ የመረጃ ክፍለ ጊዜን ያካሄዳል።
የማረጋጊያ ፈንድ ስድስተኛ ዙር የመረጃ ክፍለ ጊዜ አምልጦዎታልን? በመስመር ላይ የመረጃ ክፍለ ጊዜ ቀረፃውን ማየት እና የማይንቀሳቀስ የፊልም ማቅረቢያ ጥራዝ ዝግጅት አቀራረብን ማየት ይችላሉ (በአማርኛ፣ በቻይንኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በኮሪያ፣ በሶማሌኛ፣ በስፓኒሽ፣ በታይ እና በቬትናምኛ ይገኛል)።
ለመስተንግዶዎች፣ ለተደራሽነት መረጃ ወይም ለትርጓሜ ጥያቄዎች፣ እባክዎን የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ቢሮውን በ (206) 684-8090 ያነጋግሩ ወይም oed@seattle.gov ኢሜይል ያድርጉ።
የማመልከቻ የጊዜ ገደብ
- ጥቅምት 19 ቀን 2021 የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ለአዲስ ማመልከቻዎች ክፍት ይሆናል።
- ማመልከቻዎች ህዳር 14 ቀን 2021: እስከ 11:59 ከሌሊቱ ድረስ መቅረብ አለባቸው። የዘገዩ ወይም ያልተሟሉ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ህዳር 15 ቀን 2021- ጥር 31 ቀን 2022: ማመልከቻዎች ይገመገማሉ እና የዕርዳታ ስጦታዎች ሂደት ይካሄዳል፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ አመልካቾችን ማግኘት ይቻል ይሆናል።
- ጥር 31 ቀን 2022: አመልካቾች ሁሉ በዚህ ዕለተ ቀን ስለ ያሉበት ሁኔታ ይነገራቸዋል።
የምርጫ ሂደት
የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ከተዘጋ በኋላ የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት ህዳር 15 ቀን 2021 ማመልከቻዎችን መገምገም እና የገንዘብ ድጋፍ ስጦታ ተቀባዮችን መምረጥ ይጀምራል። አመልካቾች ሁሉ እስከ ጥር 31 ቀን 2022 ድረስ ያሉበት ሁኔታ ይነገራቸዋል።
ያልተሟሉ ማመልከቻዎች እና በመጀመሪያው ግምገማ ላይ የመነሻ ዝቅተኛ የብቁነት መስፈርቶችን የማያሟሉ ማመልከቻዎች ብቁ እንዳልሆኑ ተደርገው እና ከተጨማሪ ግምት ይወገዳሉ። የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት አባል ሠራተኞች የከተማዎ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ እና ሥራ (B&O) ግብሮች ተግባራዊነትን ለማረጋገጥ እርስዎን ሊያገኝዎት ይችላሉ። በዚህን ጊዜ፣ ለዕርዳታ ስጦታ ገንዘብ ለመታሰብ ተግባራዊነትን ለማረጋገጥ 48 ሰዓታት ይኖርዎታል።
ማሳሰቢያ: የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ሠራተኞች በ 206 የአከባቢ ቁጥር በሚጀመሩ ስልክ ወይም በ @seattle.gov በሚያበቃ ኢሜይል በኩል አመልካቾችን ሊያገኟቸው ይችላሉ። ንግዶች በ (206) 684-8090 ቢሮአችን በመደወል ወይም በድህረገጻችን የቡድናችንን ማውጫ ገጽ በመጎብኘት የሰራተኞችን ማንነት ማረጋገጥ ይችላሉ።
ተጨማሪ መረጃ
ለተጨማሪ ድጋፍ ምንጮች፣ እባክዎ ይጎብኙ:
- በ COVID-19 ለተጎዱት የንግድ ድርጅቶች እና ሠራተኞች የድጋፍ ምንጮች እና መመሪያ
- የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት (OED) የአነስተኛ ንግድ ፕሮግራሞች
- የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት (OED) አነስተኛ ንግድ የመመሪያ መጽሐፍ
- የኮቪድ-19 የአነስተኛ ንግድ የገንዘብ ድጎማዎች
- የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት (OED) የኪራይ ውል ማሻሻያ መሣሪያ ስብስብ
- አረንጓዴ የእርስዎ ንግድ ፕሮግራም
- የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት (OED) የምሽት ህይወት ማቋቋሚያ መመሪያ መጽሐፍ
- የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት (OED) የምግብ ንግድ ፕሮግራሞች
ይህንን መረጃ ከአውታረ መረብዎ ጋር ለማጋራት ከፈለጉ እባክዎን ይህንን የሚዲያ መሣሪያ ስብስብ ለመጠቀም ነፃነት ይሰማዎ።
የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት ለሁሉም የሲያትል የተለያዩ ማኅበረሰቦች የኢኮኖሚ ዕድሎችን ተደራሽነት በማስተዋወቅ ከተማዋን በሙሉ የሚጠቅም ፍትሐዊና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚ ለመገንባት ቁርጠኛ ነው። የአነስተኛ ንግድ ሥራ ልማት ቡድን እንደ አነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ፣ የቴክኒክ ድጋፍ መርሃ ግብሮች፣ እና ከተጨማሪ ሀብቶች ጋር በማገናኘት የአነስተኛ የንግድ ሥራ ባለቤቶች በቀጥታ እንዲረጋጉ እና እንዲያድጉ ይረዳል።
ጥያቄዎች? ለተጨማሪ ጥያቄዎች፣ እባክዎን የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤትን በ (206) 684-8090 ወይም oed@seattle.gov ያግኙ።