የወጣቶች ድረ-ገጽ ንድፍ

የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ከኣርባን ሊግ ኦፍ ሜትሮ ፖሊታን ሲያትል ጋር በመተባበር የወጣቶች ድረ-ገጽ ዲዛይን ፕሮግራምን ለማስፋት እየሰራ ነው። ትናንሽ ንግዶች እና ሥራ ፈጣሪዎች የንግድ ድረ-ገጽ ለመፍጠር እና መስመር ላይ መገኘታቸውን ለማሻሻል ለፕሮግራሙ ማመልከት ይችላሉ።

የማመልከቻ ሂደት

ማመልከቻዎን እስከ መስከረም 30 2022 በመስመር ላይ ማስገባት አለብዎት።

ማመልከቻው በእንግሊዝኛ መቅረብ አለበት። የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሰራተኞች ጥያቄዎችን ለመመለስ እና አመልካቾች ማመልከቻቸውን እንዲያጠናቅቁ ለመርዳት ዝግጁ ናቸው። የትርጉም ወይም የትርጓሜ አገልግሎቶችን ለመጠየቅ፣ እባክዎን (206) 684-8090 ይደውሉ።

እዚህ ያመልክቱ!

የብቃት መስፈርቶች

አነስተኛ ንግዶች እና ሥራ ፈጣሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፥

  • የንግድ እና ሥራ (B&O) ግብሮች ሙሉ በሙሉ መከፈል አለባቸው።
  • የሲያትል ከተማ የንግድ ፈቃድ ያለው።
  • ለትርፍ ያልተቋቋመ የ501(c)(3) ድርጅት መሆን አይችልም።
  • በሲያትል፣ ዋሽንግተን ያለ።
  • በአሁኑ ጊዜ የንግድ ድረ-ገጽ የሌለው ወይም ድረ-ገጹ በጣም ጊዜው ያለፈበት እና ንግዱ አስፈላጊ ዝመናዎችን ማከናወን የማይችል።

የፕሮግራም ዝርዝሮች

ፕሮግራሙ ነፃ ነው።

የንግዱ በመስመር ላይ ተገኝነት እና ስራዎችን ለማስፋት ተማሪዎች እና የንግድ ባለቤቶች ለስድስት ሳምንታት አብረው በመስራት ዘመናዊ ድረ-ገጽዎችን ይፈጥራሉ።

የተመረጡ የንግድ ባለቤቶች እና/ወይም የንግድ ተወካዮች ድህረ- ገጹን ከሚነድፉ ወጣቶች ጋር ለማስተባበር በግዴታ ስብሰባዎች ላይ መሳተፍ አለባቸው።

እርዳታ ይፈልጋሉ ወይም ጥያቄዎች አሉዎት?

እባክዎን ለእርዳታ (206) 684-8090 ይደውሉ እና የሚከተሉትን መረጃዎች በድምጽ መልእክትዎ ውስጥ ያስተውሉ: ስም፣ የስልክ ቁጥር፣ ተመራጭ ቋንቋ፣ እና የሚያስፈልግዎት የድጋፍ አይነት።

መጪ ፕሮግራሞች ወይም እርዳታ

ስለ ሌሎች ፕሮግራሞች ዝመናዎችን ከኢኮኖሚ ልማት ጽህፈት ቤት ለማግኘት፣ እባክዎ ለጋዜጣችን አባልነት ይመዝገቡ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይከተሉን: @SeattleEconomy በ Twitter፣ Instagram፣ እና Facebook። 

የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለሁሉም የሲያትል ልዩ ልዩ ማህበረሰቦች የኢኮኖሚ ዕድሎችን በማስፋፋት መላውን ከተማ የሚጠቅም ፍትሃዊ እና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት ቁርጠኛ ነው።

የሲያትል ከተማ ሁሉንም ሰው በፕሮግራሞቹ እና በእንቅስቃሴዎቹ እንዲሳተፍ ያበረታታል። ለተጨማሪ ጥያቄዎች፣ ለትርጉም ወይም ለቃል ትርጉም፣ ለቴክኒክ ድጋፍ፣ ለአካል ጉዳተኝነት ማስተናገጃዎች፣ ተለዋጭ ይዞታዎች ላላቸው ቁሳቁሶች ወይም የተደራሽነት መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤትን በ (206) 684-8090 ወይም oed@seattle.gov ያግኙ።

Economic Development

Markham McIntyre, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 5752, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 94708, Seattle, WA, 98124-4708
Phone: (206) 684-8090
Phone Alt: (206) 684-0379
Fax: (206) 684-0379
oed@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Economic Development

The mission of the Office of Economic Development (OED) is to help create healthy businesses, thriving neighborhoods, and community organizations to contribute to a robust economy that will benefit all Seattle residents and future generations.