አንድ የእድሳት ወይም የግንባታ ፕሮጀክት እንዴት ማጠናቀቅ እንደሚችሉ እና በሲያትል ውስጥ በአካል የሚገኝ ንግድ እንዴት እንደሚከፍቱ ይወቁ። ይህ መመሪያ አዲስ የንግድ ቦታ ለመክፈት ወይም እንድ የንግድ ሥራን ለማደስ የሚያስፈልጉትን ደረጃዎች በዝርዝር ያስቀምጣል።
ጊዜ እና ገንዘብ ለመቆጠብ ጠቃሚ ጥቆማዎች
1. በእርስዎ ቡድን ውስጥ ባለሙያዎችን ያግኙ።
ምንም እንኳን የግንባታ ልምድ ቢኖርዎትም፣ የንግድ ሥራ ለመክፈት የማያውቋቸው መስፈርቶች ሊኖሩ ይችላሉ። የራሳቸውን ፕሮጄክቶች የሚያካሄዱ ብዙ የንግድ ሥራ ባለቤቶች ባለሙያዎች እንዳያጋጥማቸው ሊረዷቸው ይችሉ በነበረ ችግሮች ውስጥ ይገባሉ። ሊያስፈልጉዎት የሚችሉ ባለሙያዎች የቤት/መሬት ሽያጭ ደላላ፣ ጠበቃ፣ አርኪቴክት እና አጠቃላይ ተቋራጭን ይካተታሉ።
2. ለነፃ የፍቃድ ስልጠና ይመዝገቡ እና የግንባታ ፍቃድዎን በፍጥነት ያግኙ።
ለአነስተኛ ንግድዎ ቦታ ለመምረጥ ዝግጁ ነዎት? ለነጻ የንግድ ፈቃድ ማሰልጠኛ ብቁ መሆንዎን ይወቁ። እኛ ልንረዳዎ እንችላለን…
- ፍላጐት ያሳደሩበትን ቦታ/አድራሻ የፍቃድ ታሪክን ይመርምሩ።
- ለእርስዎ ንግድ ስፍራውን ለመጠቀም ምን ጥገናዎች ወይም ዝመናዎች እንደሚያስፈልጉ ይወቁ።
- የግንባታ ፈቃድዎን ያፋጥኑ።
3. ለእርስዎ ንግድ እና በጀት ትክክለኛውን ሥፍራ ያግኙ።
እርስዎ ሊከፍቱት ያሉትን የንግድ አይነት አስቀድሞ የተሰራበት ቦታ ካገኙ ዋጋው ያነሰ እና ይበልጥ ቀላል ይሆናል። ለምሳሌ፣ አንድ የምግብ ቤት ንግድ ለመክፈት ከፈለጉ፣ ቀደም ሲል ምግብ ቤት ፍቃድ የነበረውን ቦታ መጠቀም ከአንድ አመት በላይ ስራ የሚወስደውን ጊዜ ሊያድን ይችላል።
አንድ ቦታን ማደስ ከፈለጉ፣ ከርስዎ ምን ማድረግ እንደሚጠበቅ ለመረዳት እንዲችሉ ምን ፈቃዶች እንደነበሩት ይወቁ። አንድ ቦታ/አድራሻ ምን ፈቃዶች እንደነበሩት ለማወቅ፣ በኢንተርኔት ላይ የፍቃድ ታሪኩን መመርመር ይችላሉ፦
ለፕሮጀክት ዕቅድ ማውጣት
የጊዜ መስመሮች እና ዋጋዎች በፕሮጀክትዎ ላይ የተመሠረተ ነው። ከታች የተዘረዘረው እንደ ሀሳብ የቀረበ የጊዜ መስመር ነው፣ ነገር ግን የእርስዎ ፕሮጀክት የበለጠ ወይም ያነሰ ጊዜ ሊወስድ ይችላል።
ከመክፈት ቢያንስ ከአንድ አመት በፊት፦ ትክክለኛውን ቦታ ያግኙ
ቦታዎችን ማጥናት
- ተፈላጊነት ያለው ቦታ ለማግኘት የሚረዳዎትን አንድ የቤት ደላላ ያግኙ።
- በሚፈለጉት ቦታ አካባቢ ያሉትን የጎረቤት የንግድ ቡድን ያነጋግሩ።
- ለፕሮጀክትዎ ገንዘብ ያግኙ።
- ቦታው አሁኑ ባለው ፈቃድ እና በአድራሻው መሠረት ምን ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ለማወቅ ከሲያትል ከተማ ሰራተኛ ነፃ የጥናት እገዛ ያግኙ።
ውልዎን ይደራደሩ
- ስለ የፍላጎት ደብዳቤ ከባለንብረቱ ጋር ይነጋገሩ።
- ውልዎን ለመደራደር የሚረዳ ጠበቃ ያግኙ።
- እድሳቶች ምን ያህል እንደሚያስወጡ ግምት ለማውጣት አርኪቴክት ይቅጠሩ።
- ፊርማ ከማድረግዎ በፊት አንድ ጠበቃ ውልዎን እንዲያይ ያድርጉ።
ከመከፈቱ ቢያንስ ዘጠኝ (9) ወራት በፊት፦ ፈቃዶችን ያግኙ
ንድፍ እና እቅድ
- ዕቅዶችን ከአርኪቴክትዎ ጋር ያጠናቅቁ።
- የቤት እቃዎች፣ የተገጣጠሙ እቃዎች፣ እና የመሳሪያ ዋጋዎችን ጨምሮ የዘመነ በጀት ያግኙ።
- ፈቃድ ካለው ተቋራጭ ጋር ይነጋገሩ እና የፕሮጀክት የጊዜ ሠሌዳ እና የወጪ ግምት ይፍጠሩ።
ለፍቃዶች ያመልክቱ
- ለእርስዎ ምን ፍቃዶች እንደሚያስፈልጉ ለማወቅ ለፈቃድ ማሰልጠኛ ይመዝገቡ።
- የእርስዎ ንግድ በአንድ ታሪካዊ ወረዳ ወይም በታሪካዊ ምልክትነት ተጠብቆ የሚቆይ ሕንፃ ውስጥ ከሆነ፣ የታሪክ ማቆያ ማጽደቂያ የምስክር ወረቀት ያስፈልግዎታል
- ማንኛውንም ግንባታ ወይም እድሳት የሚሰሩ ከሆነ፣ አርኪቴክትዎ ለግንባታ ፈቃድ እንዲያመልክት ያድርጉ።
- የምግብ ንግድ እየከፈቱ ከሆነ፣ የምግብ አገልግሎት እቅድዎ በሕዝብ ጤና - ሲያትል እና የኪንግ ካውንቲ (PHSKC) የምግብ እና መገልገያዎች ፕሮግራም ያስገምግሙ።
- እንዲሁም በ ኪንግ ካውንቲ የቧንቧ ሥራ እና ጋዝ ፕሮግራም ፈቃድ ሊያስፈልግዎት ይችላል።
- እንደ መጠጥ ፈቃድ ወይም የንግድ ምልክት ፈቃድ ያሉ ለእርስዎ ንግድ አስፈላጊ በሆኑ ላይ በመመስረት ለሌሎች ፈቃዶች ያመልክቱ።
ከመከፈቱ ከስድስት (6) ወራት በፊት፦ ግንባታ
- እርስዎ እና የሥራ ተቋራጭዎ ግንባታው ከመጀመሩ በፊት ሁሉንም ፈቃዶች እንዳለዎት ያረጋግጡ
- የግንባታውን የጊዜ ሠሌዳ ከሥራ ተቋራጭ ጋር ይመልከቱት
- እርስዎ ለየትኞቹ ምርመራዎች ቀጠሮ እንደሚያስይዙ እና የሥራ ተቋራጩ ለየትኞቹ ቀጠሮዎች እንደሚያስይዝ ይወቁ
ከመከፈቱ ከሶስት (3) ወራት በፊት፦ ምርመራዎች
ለምርመራዎች ቀጠሮ መያዝ
- ለግንባታ ስራዎች ከSeattle Department of Construction and Inspections (የሲያትል የግንባታ እና ምርመራዎች መምሪያ) እና ከሲያትል የእሳት አደጋ መከላከያ መምሪያ ምርመራዎችን ያግኙ።
- ሌሎች ማንኛቸውንም፣ ለምሳሌ እንደ ከ100+ ሰዎች ላሏቸው የምግብ ንግድ ቤቶች የመሰብሰቢያ ፈቃድ ያሉ ከሲያትል የእሳት አደጋ መምሪያ ሊፈልጉ የሚችሉትን ፈቃዶች ያግኙ
- አስፈላጊ ከሆነ፣ ከኪንግ ካውንቲ የህዝብ ጤና ለምግብ አገልግሎት እና የቧንቧ ሥራ እና የጋዝ ፍተሻዎችን ያግኙ።
- ከሁሉም ፍተሻዎች በኋላ፣ የእርስዎን የይዘት የምስክር ወረቀት ለመቀበል የመጨረሻ ፍተሻ/ ምርመራ ያግኙ።
ንግድዎን ያስተዋውቁ
- በአካባቢዎ ካሉ ሌሎች ተጐራባች የንግድ ባለቤቶች ጋር ይገናኙ።
- በተጐራባች ቡድኖች እና በማህበራዊ አውታረ መረቦች ውስጥ የእርስዎን ንግድ መከፈት ያሰራጩ።
- ነፃ ከማርኬቲንግ አማካሪዎች እርዳታ ያግኙ።
በአማካይ የጊዜ መስመሮች እና የፈቃድ ዋጋዎች
እነዚህ አማካዮች በቅርብ ጊዜ ሲያትል ውስጥ ከሚገኙ አነስተኛ የንግድ ፕሮጀክቶች የተገኙ ናቸው። የፈቃድ ክፍያዎች መጠን ከ 2026 ዓመት የክፍያ ተመኖች ተስተካክለዋል።
ምግብ ቤቶች
- ከፈቃድ ማመልከቻ እስከ የመጨረሻ ፍተሻ ድረስ አንድ (1) ዓመት።
- $5,600 ዶላር አማካይ የግንባታ ፈቃድ ክፍያዎች።
የውበት ሳሎኖች
- ከፈቃድ ማመልከቻ እስከ የመጨረሻ ፍተሻ አስራ አንድ (11) ወራት
- $1,800 ዶላር አማካይ የግንባታ ፈቃድ ክፍያዎች
የችርቻሮ መደብሮች
- ከፈቃድ ማመልከቻ እስከ የመጨረሻ ፍተሻ ድረስ ስምንት (8) ወራት
- $4,700 ዶላር አማካይ የግንባታ ፈቃድ ክፍያዎች
ምሳሌ የሚሆኑ ፕሮጀክቶች

ከዚህ በፊት
ይህ የመሀል ከተማ ሲያትል ውስጥ ያለ ቦታ የምግብ ቤት ንግድ የመሆን ፍቃድ ስለነበረው፣ አዲስ ምግብ ቤት ለመክፈት ብዙ ለውጦች አላስፈለጉትም።

በኋላ
ፓጁ (Paju)፣ የኮሪያ ምግብ ቤት፣ እንደገና ከታደሰ በኋላ ወደዚህ ቦታ ተዛወረ። የፎቶ ዕውቅና: Atelier Drome (አተሊዬ ድሮም)።

ከዚህ በፊት
ይህ ቦታ በአዲስ ሕንፃ ውስጥ ነበር፣ ስለዚህ ከመከፈቱ በፊት አንድ ንግድ አብዛኛውን ነገሮችን በራሳቸው መገንባት ነበረባቸው።

በኋላ
ኮሚንዮን ምግብ ቤት እና ባር የራሳቸውን ምግብ ቤት እና ኩሽናቸውን ለመስራት ፍቃድ አግኝተዋል። ሁሉንም ፈቃዶች ማግኘት ወራት ሊወስድ ስለሚችል፣ አስቀድመው ዕቅድ ያውጡ። የፎቶ ዕውቅና: Atelier Drome (አተሊዬ ድሮም)።
በጥልቀት ይቅዱ፦ ንግድዎን ለመክፈት እርምጃዎች
ትክክለኛውን ቦታ መምረጥ የእርስዎን ገንዘብ፤ ጊዜ እና ራስ ምታት ይቆጥባል። ክፍት ቦታዎችን እንዴት እንደሚያገኙ እና የንግድ ውል መደራደር እንደሚችሉ ያጥኑ።
የእርስዎን አካባቢ/ ቦታ ዲዛይን ያድርጉ እና ንግድዎን ለመገንባት ወይም ለማስፋት ፈቃዶችን ያግኙ።
ከመከፈቱ በፊት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የምርመራ ቀጠሮዎች ያስይዙ።
ለፈቃድ ሥልጠና ይመዝገቡ
አንድ የንግድ ቦታን ለማጥናት፣ ቦታውን ለመጠቀም ምን ጥገና ወይም እድሳት እንደሚያስፈልግ ለመረዳት እና የግንባታ ፈቃዶችዎ ላይ እገዛ ለማግኘት ለነጻ እርዳታ ለንግድ ቦታ ፈቃድ ማግኛ ማሰልጠኛ ብቁ መሆንዎን ይመልከቱ/ ይፈትሹ።