ንድፍ እና እቅድ
ባለሙያ ለምን ይቀጥራሉ?
አርኪቴክት እና ተቋራጭ መቅጠር መጀመሪያ ላይ ብዙ ወጪ ሊጠይቅ ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን በመጨረሻ፣ ብዙ ጊዜ እና ገንዘብ ሊቆጥብ ይችላል። ሲያትል ውስጥ በአነስተኛ የንግድ ሥራ ፕሮጀክቶች ልምድ ያለውን አርኪቴክት ያግኙ። ስለ ከተማ እና ስለ ካውንቲ መስፈርቶች ያውቃሉ።
የፕሮጀክትዎ ቦታ ከ4,000 ካሬ ጫማ በላይ ከሆነ ወይም እንደ የእሳት ጊዜ መውጫዎች፣ ግድግዳዎች፣ ወይም ደረጃዎች ያሉ አስፈላጊ ነገሮችን የሚነካ ከሆነ አርኪቴክት መቅጠር አለብዎት።
ገንዘብ ለመቆጠብ ቦታዎን ይንደፉ
ቦታዎን የሚነድፉበት መንገድ ምን አይነት ፈቃዶች እንደሚያስፈልጉዎት ሊለውጥ ይችላል። ተጨማሪ ፈቃዶች ሊፈልጉ የሚችሉ አንዳንድ ነገሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
- መስኮቶችን መጨመር ማለት አዲስ የኃይል ኮድ ደንቦችን መከተል ያስፈልግዎታል ማለት ነው።
- ግድግዳዎችን ወይም ጣሪያዎችን መቀየር ማለት ወደ የእሳት ጊዜ ማንቂያዎች ወይም ውሃ መርጫዎች ላይ ለውጦች ማለት ሊሆን ይችላል።
- ሰዎች ከህንጻው እንዴት እንደሚወጡ መለወጥ ማለት ተጨማሪ መከተል ያለባቸው ህጎችን ሊያመለክት ይችላል ማለት ነው።
ኮንትራክተር ይቅጠሩ እና የጊዜ ሰሌዳ ይፍጠሩ
የሕንጻዎ ንድፍ ዝግጁ ከሆነ በኋላ፣ የግንባታ ስራውን ለመስራት ኮንትራክተር ይቅጠሩ። ሲያትል ውስጥ በአነስተኛ የንግድ ሥራ ፕሮጀክቶች ልምድ ያለው ባለሙያ ኮንትራክተር በእርስዎ ፕሮጀክት አፈጻጸም ሊረዳዎት ይችላል።
ኮንትራክተር ሲያገኙ፣ ስለ ግንባታው ሥራ የጊዜ ሠሌዳ ያነጋግሯቸው። ሁለታችሁም የትኞቹን ፈቃዶች እነርሱ እንደሚያመለክቱ እና የትኞቹን እርስዎ ማውጣት እንዳለብዎት ማወቃችሁን ያረጋግጡ።
ከዋሽንግተን ስቴት የሰራተኛ እና ኢንዱስትሪዎች ኮንትራክተር ስለ መቅጠር የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ፈቃዶችን ማግኘት
ለሚያስፈልጉዎት ፈቃዶች ሁሉ በተመሳሳይ ጊዜ እንዲያመለክቱ እንመክራለን። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ፈቃዶች ሁሉም ለእርስዎ ላያስፈልጉ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ እርስዎ ምግብ የማያቀርቡ ከሆነ፣ የምግብ አገልግሎት ክፍልን መዝለል ይችላሉ።
ለታሪካዊ ቦታዎች ፈቃድ ማግኘት
የእርስዎ ንግድ ሲያትል ውስጥ ባለ አንድ እንደ ታሪካዊ ሆኖ የሚቆይ ወይም በታሪካዊ ምልክትነት ተጠብቆ የሚቆይ ሕንፃ ውስጥ ከሆነ፣ ሌሎች ፈቃዶችን ከማግኘትዎ በፊት ከSeattle Department of Neighborhoods (ሲያትል የሠፈሮች መምሪያ) የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያስፈልግዎታል።

በባላርድ፣ በሳንድ ፖይንት፣ በፎርት ላውተን፣ በሰሜን ካፒቶል ሂል፣ በፓይክ ፕሌስ ማርኬት፣ በፓዮኒር አደባባይ፣ በቻይናታውን-ኢንተርናሽናል ዲስትሪክት፣ እና በኮሎምቢያ ሲቲ አካባቢዎች ታሪካዊ ወረዳዎች አሉ።
የእርስዎ ዕቅዶች ሕጐቹን ተከትለው እንደሆነ ለማረጋገጥ ከታሪካዊ ጥበቃ ፕሮግራም ሰራተኞች ጋር ይነጋገሩ።
- ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል፦ ለአንዳንድ ፕሮጀክቶች ከ4-6 ሳምንታት ወይም ከዚያም በላይ።
- የፍቃድ ወጪ፦ በ $25 ዶላር ይጀምራል እና በፕሮጀክት የዋጋ መጠን እየጨመረ ይሄዳል።
የግንባታ ፈቃዶች
ከሲያትል የግንባታ እና ምርመራዎች መምሪያ (SDCI) የግንባታ ፈቃድ ያስፈልግዎታል። የእርስዎ ኮንትራክተር በዚህ ሊረዳዎ ይችላል። በኢንተርኔት ፖርታል በኩል ያመልክቱ።
- ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል፦ በፕሮጀክቱ ላይ በመመስረት፣ ለግምገማ/ ክለሳ ከ6-12 ሳምንታት
- የፍቃድ ወጪ፦ በፕሮጀክት ወጪ/የዋጋ መጠን መሰረት ይለያያል፤ የቅርብ ጊዜ ጠቅላላ የግንባታ ፈቃድ እና የፍተሻ/ ምርመራ ወጪዎች አነስተኛ የንግድ ፕሮጀክቶች በአማካይ ወደ $7,000 ዶላር ነበር
የኤሌክትሪክ ፈቃድ
አብዛኛዎቹ ፕሮጀክቶች የኤሌክትሪክ ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል። የኤሌክትሪክ ፈቃድ የሚያስፈልገው ሽቦዎቹን ለመገመድ ወይም ሌላ ለሚያደርጉት የኤሌክትሪክ ለውጦች ነው።
- ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል፦ ለአብዛኞቹ ፕሮጀክቶች በዚያኑ ቀን
- የፈቃድ ዋጋ፦ $52.45 እና በየአንዳንድ ፕሮጀክት ተጨማሪ ወጪዎች
የሜካኒካል ፈቃድ
በማሞቂያ፣ በማቀዝቀዝ ወይም በአየር ማሰራጫ ስርዓቶች ላይ ለውጦችን ማድረግ ከፈለጉ ሜካኒካል ፈቃድ ያስፈልግዎታል።
- ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል፦ 2 - 9 ሳምንታት
- የፈቃድ ዋጋ፦ ብዙውን ጊዜ ወጪው በግንባታው የፈቃድ ወጪዎች ውስጥ ይካተታል
የእሳት አደጋ ማስጠንቀቂያ፣ የእሳት ማጥፊያ መርጫ እና የኩሽና ከላይ ማፈኛ ክዳን ፈቃዶች
የእሳት አደጋ ማስጠንቀቂያዎችን ወይም የእሳት ማጥፊያ መርጫ ለመጨመር ወይም ለመለወጥ ፈቃድ ያስፈልግዎታል።
አዲስ ኩሽና የሚያስገቡ/ የሚሠሩ ከሆነ ወይም ኩሽና ምድጃ እና ከላይ ኮፈያውን ለውጦች ካደረጉ፣ የኩሽና ኮፈያ ማፈኛ ፍቃድ ያስፈልግዎታል። እነዚህን ፈቃዶች ከሲያትል የግንባታ እና ምርመራ መምሪያ (SDCI) ያገኛሉ።
አንዴ ካመለከቱ በኋላ፣ SDCI የእርስዎን እቅዶች እና ስዕሎች ወደ የእሳት አደጋ መምሪያ ይልካል። ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ ዕቅዶችዎን ያዩታል።
እንዲሁም ከኪንግ ካውንቲ የቧንቧ ስራ ፈቃድ እና ከሲያትል የህዝብ መገልገያዎች መሥሪያ ቤት በቂ ውሃ እንዳለ የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ሊያስፈልግዎት ይችላል። ለአዲስ የውሃ መርጫ ሥርዐቶች፣ እሳት ቢነሳ በቂ ውሃ በሥርዐቱ ውስጥ የሚፈስ መሆኑን ለመፈተሽ "hydrant flow test (የውሀ መርጫ ፍሰት ሙከራ)" ማድረግ ያስፈልግዎ ይችላል።
- ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል፦ እስከ 5 ሳምንታት
- የፈቃድ ዋጋ፦ ለሰራተኞች ጊዜ $400 ዶላር በሰአት
የቧንቧ ሥራ፣ የጋዝ፣ ወይም የወደኋላ ፍሰት ፍቃድ
የሚከተሉትን የሚያደርጉ ከሆነ የቧንቧ፣ ጋዝ ወይም የወደኋላ ፍሰት ፍቃድ ያስፈልግዎታል፦
- ገንዳ መጨመር ወይም ቦታ መቀየር
- የጋዝ ምድጃ ማስገባት
- የወደኋላ ፍሰት መከላከያ ማስገባት
- በቧንቧ ሥራ ወይም ጋዝ ስርዓቶች ላይ ሌሎች ለውጦችን ማድረግ
የምግብ ንግዶች ብዙ ጊዜ የቧንቧ ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል። እነዚህ ፎቶዎች ንግዱ አንድ የቡና ኤስፕሬሶ ማሽን መጨመር እንዲቻል አዲስ የወለል መውረጃ ማስገባቱን ያሳያሉ፦

የእርስዎን ፍቃድ ከማግኘት በፊት ዕቅዶችን ለማስገምገም ማመልከቻ ማስገባት ያስፈልግ እንደሆነ ለማየት የቧንቧ እና ጋዝ በቦታው መያዝ እና አጠቃቀም መመሪያን (PDF) ይመልከቱ። እንደዚያ ከሆነ፣ የእርስዎ እቅዶች ብቃት ባለው ባለሙያ መዘጋጀት እና የቧንቧ ወይም የጋዝ ስርዓቱን ማሳየት አለባቸው። የአርኪቴክቸር ንድፍ ስዕሎች ተቀባይነት አይኖራቸውም። ጥያቄዎች ካልዎት፣ ወደ planreviewinfo@kingcounty.gov ኢሜል ይላኩ።
- ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል፦ ለአንዳንድ ፕሮጀክቶች በዚያኑ ቀን፤ የዕቅድ ግምገማ ለሚያስፈልጋቸው ፕሮጀክቶች ከ4-6 ሳምንታት
- የፍቃድ ወጪ፦ $132 ዶላር የመሠረት ክፍያ በተጨማሪ ለአንድ የተገጠመ ዕቃ ወይም የሀይል ማውጫ $26 ዶላር
- የዕቅድ ግምገማ ዋጋ (የሚመለከተው ከሆነ)፦ ለሠራተኞች ጊዜ $264 ዶላር በሰዓት
የቧንቧ ሥራ፣ የጋዝ ወይም የወደኋላ ፍሰት ፈቃዶች
ለምግብ አገልግሎት ዕቅዶች ግምገማ
የእርስዎ ንግድ ምግብ ወይም መጠጥ ያለው ከሆነ፣ ከመገንባቱ ወይም ከመታደሱ በፊት ከሕዝብ ጤና - ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ ግምገማ ያስፈልገዋል። ቦታው ከ90 ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ተዘግቶ ከነበረ እና ምንም ለውጦች ከሌሉ፣ ግምገማ ላያስፈልግ ይችላል። በ (206) 263-9566 አግኟቸው ወይም በehfoodandfacilitiesplan@kingcounty.gov ኢሜል ይላኩ።
- ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል፦ አማካይ የመጀመሪያ እቅድ ግምገማ ከ4-6 ሳምንታት ነው
- የፈቃድ ዋጋ፦
- አዲስ ግንባታዎች፦ $1,008
- እድሳቶች፦ $756
- የእርስዎ ግምገማ ከተለመደው ጊዜ በላይ ከወሰደ ወይም እቅዱን እንደገና መሥራት እና እንደገና እንዲገመገም ከፈለጉ፣ ተጨማሪ ጊዜ በሰዓት $242 ያስከፍላል
- እባክዎ እነዚህ ወጪዎች የእርስዎን እቅድ እንዲገመገሙ ለማድረግ መሆኑን ልብ ይበሉ። በኋላ፣ ከመክፈትዎ በፊት፣ የተለየ አመታዊ የስራ ማካሄጃ ፍቃድ ክፍያ ይከፍላሉ::
ሌሎች ሊያስፈልጉዎት የሚችሉ ፈቃዶች
የመጠጥ ፍቃድ
አልኮል ለመሸጥ፣ የዋሽንግተን ስቴት የመጠጥ ፍቃድ ያስፈልግዎታል።
- ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል፦ እስከ 90 ቀናት
- የፍቃድ ዋጋ፦ ከ$200-2,000
ምልክት ወይም የማስታወቂያ መብራት ፈቃዶች
ምልክት ወይም የማስታወቂያ መብራት ካልዎት፣ ፈቃድ ሊያስፈልግዎት ይችላል።
- ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል፦ ብዙውን ጊዜ ወደ 2 ሳምንታት
- የፈቃድ ዋጋ፦ ከ$181.40 ጀምሮ
የውጭ መመገቢያ ቦታ
ውጭ በህዝባዊ ቦታ ለማስቀመጥ፣ ከሲያትል የትራንስፖርት መምሪያ ፈቃድ ያስፈልግዎታል።
- ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል፦ ወደ 50 ቀናት ገደማ
- የፈቃድ ዋጋ፦ መጀመሪያ $1,317 ዶላር፣ ለዓመታዊ እድሳት $635 ዶላር
የመንገድ አጠቃቀም ፈቃዶች
የሚከተሉትን የሚያደርጉ ከሆነ የመንገድ አጠቃቀም ፈቃድ ሊያስፈልግዎት ይችላል፦
- በመንገዶች ውስጥ፣ በሰፈር ውስጥ መተላለፊያዎች ወይም በእግረኛ መንገዶች ላይ ግንባታዎችን መሥራት።
- በእግረኛ መንገድ ወይም በመትከያ ቁራጭ መሬት ላይ የግንባታ መሳሪያዎችን ወይም አቅርቦቶችን ማቆየት።
- የእግረኛ መንገዱን የግንባታ መሳሪያዎች ይዞ መሻገር፣ ወይም የእግረኛ መንገድን ወይም የመንገድ መስመርን መዝጋት ካስፈለገ።
- ከእርስዎ ንግድ ውጭ በእግረኛ መንገድ፣ በመንገድ፣ በሰፈር ውስጥ መተላለፊያ ወደ መንገዱ ወይም በሕዝብ አካባቢ የሚዘረጋ ማንኛውንም ነገር ማስገባት። ይህ እንደ የደህንነት መዝጊያዎች፣ ድንኳኖች፣ መቀመጫዎች፣ የሸቀጣሸቀጥ ማሳያዎች፣ ወዘተ ያሉ ነገሮችን ያካትታል።
ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል፦ ለረጅም ጊዜ ፈቃድ 5-ተጨማሪ ሳምንታት፤ ለግንባታ አጠቃቀም ፈቃድ 8-ተጨማሪ ሳምንታት፤
የፍቃድ ዋጋ፦ ይለያያል፤ ለእርስዎ ፕሮጀክት የክፍያ ግምት መስጫ ይጠቀሙ
የእርስዎን ንግድ ለመክፈት ሌሎች እርምጃዎች
ትክክለኛውን ቦታ መምረጥ የእርስዎን ገንዘብ፤ ጊዜ እና ራስ ምታት ይቆጥባል። ክፍት ቦታዎችን እንዴት እንደሚያገኙ እና የንግድ ውል መደራደር እንደሚችሉ ያጥኑ።
ከመከፈቱ በፊት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የምርመራ ቀጠሮዎች ያስይዙ።
ለፈቃድ ሥልጠና ይመዝገቡ
አንድ የንግድ ቦታን ለማጥናት፣ ቦታውን ለመጠቀም ምን ጥገና ወይም እድሳት እንደሚያስፈልግ ለመረዳት እና የግንባታ ፈቃዶችዎ ላይ እገዛ ለማግኘት ለነጻ እርዳታ ለንግድ ቦታ ፈቃድ ማግኛ ማሰልጠኛ ብቁ መሆንዎን ይመልከቱ/ ይፈትሹ።