ውል ከመፈረምዎ በፊት ምን መታወቅ እንዳለበት
ውል ከመፈረምዎ በፊት፣ እርስዎ እነዚህን ጥያቄዎች መልስ መስጠት እንደሚችሉ ያረጋግጡ፦
- በአሁኑ ወቅት ቦታው/ አድራሻው ምን ዓይነት ፈቃዶች አሉት?
- በቦታው ላይ ምንም አይነት ትልቅ ለውጥ ማድረግ ያስፈልግዎታል?
- ምን ያህል ያስከፍላል?
ቦታውን/ አካባቢውን ሲመለከቱ፣ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ እርስዎን እንዲረዳ አንድ አርኪቴክት መቅጠር ወይም የእኛን የነጻ የንግድ ቦታ ባለሙያዎች ማነጋገር ይችላሉ። አስቀድሞ የእርስዎን ንግድ አይነት ፈቃድ ያለው ቦታ ለማግኘት ይሞክሩ።
ጠቃሚ ምክር፦ ምንም እንኳን የእርስዎ ቦታ ከዚህ በፊት የንግድ ቦታ የነበረ፣ ፍቃድ ላይኖረው ይችላል! አንዳንድ ጊዜ ንግዶች ያለ ትክክለኛ ፈቃድ ይሰራሉ። የኪራይ ውል ከመፈረምዎ በፊት ምን ጊዜም ከዚህ በፊት የእነሱን “Certificate of Occupancy” ("የይዞታ ሰርተፍኬት") ደግመው ማረጋገጥ አለብዎት። ይህ ውድ የሆኑ ማሻሻያዎችን እና ያልታሰቡ ነገሮችን ለማስወገድ ይረዳል።
ያለፈውን የቦታውን “ይዞታ” ለማየት የሲያትል የመስመር ላይ መሳሪያን መጠቀም ይችላሉ፣ ለምሳሌ ምግብ ቤት ወይም ሳሎን የመሆን ፍቃድ እንዳለው ለማየት። ይህንን መረጃ በፈቃድ መዝገቦች ውስጥ በጣም የቅርብ ጊዜ "የይዞታ የምስክር ወረቀት" ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
ምሳሌ የሚሆኑ ፕሮጀክቶች

አዲስ ሕንፃዎች
በፊኒ ሪጅ (Phinney Ridge) ውስጥ Ben’s Bread (የቤን ዳቦ ቤት) የዳቦ ቤታቸውን እና ምግብ ቤቱን በአዲስ ባዶ ቦታ ውስጥ ነው የገነቡት። የፎቶ ዕውቅና: ሮበርት ሀቺሰን (Robert Hutchison) አርኪቴክቸር

ነባር ሕንፃዎችን ማደስ
በምዕራብ ሲያትል የሚገኘው The Missing Piece (ዘ ሚሲንግ ፒስ) እንድ አሮጌ ፋርማሲን ወደ ጌም ካፌያቸው ለወጡት። አንድ አዲስ ቦታ ላይ እያደሱም ሆነ አዲስ እየገነቡ፣ የግንባታ ፈቃድ ያስፈልግዎታል።
መታሰብ ያለባቸው ጠቃሚ የቦታ ገጽታዎች
- የመኪና ማቆሚያ ቦታ ፍላጎቶች፦የቦታውን አጠቃቀም ለመቀየር እያሰቡ ከሆነ፣ ተጨማሪ የመኪና ማቆሚያ መገንባት ሊያስፈልግ ይችላል።
- የባህር ዳርቻ ደንቦች፦ ቦታዎ ከባህር ዳርቻ በ200 ጫማ ርቀት ላይ ከሆነ፣ የባህር ዳርቻ ደንቦች ተፈጻሚ መሆናቸውን ያረጋግጡ።
- ታሪካዊ ቦታዎች፦ ህንጻው ለታሪክ ምልክትነት ወይም እንድ ታሪካዊ ወረዳ ውስጥ መሆኑን ያጥኑ።
- ተደራሽነት፦ ቦታው የተደራሽነት መመዘኛዎችን የሚያሟላ መሆኑን ያረጋግጡ፣ ለምሳሌ ለተሽከርካሪ ወንበሮች የመንገድ መወጣጫ።
- የእሳት እና የደህንነት ስርዓቶች፦ ለእርስዎ ንግድ ስራ ዓይነት የሚፈለግ የእሳት ማስጠንቀቂያ እና የውሃ መርጫዎች ቦታው አስቀድሞ እንዳሉት ያጥኑ። ምግብ ቤቶች ብዙ የእሳት አደጋ ጥበቃ ደህንነት ገጽታዎች ያስፈልጓቸዋል፣ ስለዚህ ቀደም ሲል እነዚህን ገጽታዎች ያካተተ ቦታ መፈለግ ከሁሉ የተሻለ ነው።
- የመገልገያ አገልግሎቶች፦ለእርስዎ ፍላጎቶች በቂ የውሃ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳለ ያረጋግጡ።
ከባለሙያዎች እርዳታ ያግኙ
የአካባቢውን ባለሙያዎች ያነጋግሩ፦ ከእርስዎ የሰፈር የንግድ ሥራ ማህበር ጋር ይነጋገሩ እና አንድ ደላላ ይቅጠሩ። እነርሱ እጅግ በጣም ጥሩ የሆኑ ክፍት ቦታዎችን ለማግኘት ሊረዱዎት ይችላሉ።
የሲያትል ከተማ ድጋፍ፦ መስፈርቶችን ለመረዳት ከአካባቢ ባለሙያዎች አንድ-ለአንድ እርዳታ ለማግኘት ያመልክቱ።
ውልዎን ይደራደሩ
ዲዛይነር ያነጋግሩ
ውል ከመፈረምዎ በፊት፣ ከዲዛይነት ወይም አርክቴክት ጋር መስራት ጥሩ ነው። እነርሱ ማንኛውም ግንባታ ምን ያህል ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል እና ቦታው ከእርስዎ ፍላጎት እና በጀት ጋር የሚጣጣም ከሆነ ለማወቅ እርስዎን ሊረዱ ይችላሉ።
ከጠበቃ ጋር ይነጋገሩ
የእርስዎን የኪራይ ውል አንድ ጠበቃ እንዲመለከት ማድረግ አስፈላጊ ነው። እነርሱ ዝርዝሮችን ሁሉ ለመረዳት ይረዳሉ፣ ስለዚህ በኋላ ምንም ያልተጠበቁ ነገሮች አይኖሩም። እንዲሁም ለምሳሌ ንግድዎን እስኪከፍቱ ድረስ ነጻ ኪራይን የመሳሰሉ ጥሩ የሊዝ ውሎችን ለመደራደር ሊረዱ ይችላሉ።
ነፃ እርዳታ ያግኙ
እርስዎ የውል ሂደቱን ለመረዳት እንዲረዳዎት የነጻ ምክር ለማግኘት ብቁ መሆንዎን ይመልከቱ።
ንግድዎን ለመክፈት የሚቀጥሉት እርምጃዎች
የእርስዎን አካባቢ/ ቦታ ዲዛይን ያድርጉ እና ንግድዎን ለመገንባት ወይም ለማስፋት ፈቃዶችን ያግኙ።
ከመከፈቱ በፊት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የምርመራ ቀጠሮዎች ያስይዙ።
ለፈቃድ ማሰልጠኛ ይመዝገቡ
አንድ የንግድ ቦታን ለማጥናት፣ ቦታውን ለመጠቀም ምን ጥገና ወይም እድሳት እንደሚያስፈልግ ለመረዳት እና የግንባታ ፈቃዶችዎ ላይ እገዛ ለማግኘት ለነጻ እርዳታ ለንግድ ቦታ ፈቃድ ማግኛ ማሰልጠኛ ብቁ መሆንዎን ይመልከቱ/ ይፈትሹ።