የንግድ ማህበረሰብ ባለቤትነት

Business Community Ownership Fund, National Development Council, and Office of Economic Development logos on a beige background.

 

መዋዕለ ነዋይ አደረገ። ማነቃቃት ሰጠ። የተመሠረተበት ሥር።

የንግድ ማህበረሰብ ባለቤትነት የገንዘብ ድጋፍ ለሲያትል የንግድ ድርጅት ባለቤቶች የራሳቸውን የወደፊት ሥራዎቻቸውን እንዲቆጣጠሩ መሳሪያዎችን ይሰጣቸዋል።

የንግድ ማህበረሰብ ባለቤትነት (BCO) የገንዘብ ድጋፍ አብዛኛውን ጊዜ በቀለም ሰዎች፣ በስደተኞች፣ በሴቶች፣ እና በLGBTQ+ ባለቤትነት የተያዙ ሰፈሮችን እና ንግዶችን ዘወትር ተጽእኖ የሚያሳድር፣ በሲያትል ውስጥ እየጨመረ ያለውን የንግድ ኪራይ ዋጋ የሚፈታ አዲስ የመዋዕለ ነዋይ ተምሳሌነት ነው። እነዚህ ማህበረሰቦች በስርዓታዊ ኢፍትሃዊነት፣ ዘረኝነት፣ እና ተያያዥ መሰናክሎች ምክንያት ኣነስተኛ የካፒታል ተደራሽነት እያገኙ ቀጥለዋል።

የንግድ ማህበረሰብ ባለቤትነት (BCO) የገንዘብ ድጋፍ፣ ለንግድ ሥራ ባለቤቶች ቋሚና በዋጋ ተመጣጣኝ የቤት ኪራይ እንዲኖራቸው ያደርጋል። ይህ የፊናንሳዊ መረጋጋት በአሁኑ ወቅት ያሉ የጎረቤት ንግዶችን በቦታቸው እንዲቆዩ ያደርጋቸዋል እንዲሁም የተፈናቀሉ የንግድ ባለቤቶችን ወደ ማህበረሰባቸው እንዲመለሱ ያደርጋል።

ከንግድ ማህበረሰብ ባለቤትነት (BCO) የገንዘብ ድጋፍ ጋር የሚተባበሩ የንግድ ባለቤቶች የሚከተሉትን ጥቅማጥቅሞች ይቀበላሉ:

 • የንግድ የመሬት/ ቤቶች የጋርዮሽ ባለቤትነት።
 • የተረጋጋ፣ በዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ የመኖሪያ ወጪዎች።
 • ከሌሎች የንግድ ባለቤቶች ጋር የድጋፍ ማህበረሰብ።
 • እድገታቸውን የሚደግፉ መሳሪያዎችን እና የውሂብ/ መረጃ ሀብቶችን መድረስ።

የገንዘብ ድጋፉ አንዴት ነው የሚሰራው?

 1. የንግድ ማህበረሰብ ባለቤትነት (BCO) በሲያትል ሰፈሮች ውስጥ በንግድ መሬት/ ቤቶች ላይ መዋዕለ ንዋይ ያውላል፣ ስለሆነም በከፍተኛ የመፈናቀል አደጋ ላይ ያሉ ንግድ ባለቤቶችን ከመንገድ ፊት ለፊ ካሉ መደብሮች ቦታ እንዲኖራቸው ያደርጋል።
 2. የገንዘብ ድጋፉ በእያንዳንዱ ፕሮጀክት ላይ መዋዕለ ንዋይ ለማዋል ሐላፍነቱ የተወሰነ ኩባንያ (LLC) ይፈጥራል። እነዚያ ንግዶች የሚይዙትን የንግድ ንብረት የሚገዙ፣ በርካታ የንግድ ድርጅቶች ባለቤቶች ሐላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ (LLC) አባል ሊሆኑ ይችላሉ። የገንዘብ አሰጣጡ በብሔራዊ ልማት ምክር ቤት (NDC) እንደ አንድ የሥራ አስኪያጅ አባል ደኅንነቱ የተጠበቀ ይሆናል።
 3. የግብር ጥቅማ ጥቅሞች እና የገንዘብ ፍሰት የንግድ ባለቤቶቹን ይጠቅማሉ።

የንግድ ማህበረሰብ ባለቤትነት (BCO) የገንዘብ ድጋፉ የሚያልመው እንደሚከተለው ነው:

 • በአሁኑ ወቅት ያሉትን የጥቁር፣ የአገሬው ተወላጆች፣ እና የቀለም ሰዎች ባለቤትነት ትናንሽ ንግዶችን በሲያትል ሰፈሮች ውስጥ ማቆየት።
 • በሲያትል ውስጥ በንግድ የኪራይ ዋጋዎች መጨመር ምክንያት ለተፈናቀሉ ወይም የንግድ ሥራ መሰረት መጣል ላልቻሉ ንግዶች የንግድ መሬት/ቤቶች ንብረቶች የደኅንነት ዋስትና የሚጠበቅበትን መንገድ መፍጠር።
 • የንግድ ባለቤቶችን የፋይናንስ ደህንነት ጥበቃ እና ኢኮኖሚያዊ ነፃነት መገንባት።
 • ለባለቤቶቹ የረጅም ጊዜ መረጋጋት እና ቁጥጥር በመስጠት የንግድ ገቢን እና እሴትን መጨመር።

የንግድ ማህበረሰብ ባለቤትነት (BCO) የገንዘብ ድጋፍ በሲያትል ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ (OED) እና በብሔራዊ ልማት ምክር ቤት (NDC) መካከል የሚከናወን ትብብር ነው። አሁንም በሙከራ ደረጃ ላይ ያለ እና የፕሮጀክት ሃሳቦችን በንቃት እየፈለገ ነው።

የገንዘብ ድጋፉ ቁልፍ የሆኑ የማህበረሰብ እና የንግድ አላማዎችን የሚያሟሉ፣ ለምሳሌ የመሬት ወለል ንግድን ወደ ሰፈር በማቀናጀት፣ ከባህላዊ ተቀባይነት ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን እቃዎች እና አገልግሎቶችን ማቅረብ፣ እና የንግድ ስራ ዘላቂነት እና ለሴቶች እድገትን፣ LGBTQ+፣ የጥቁር፣ የሀገሬው ተወላጅ፣ እና ሌሎች ነጭ ላልሆኑ የንግድ ስራ ባለቤቶች ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው የንግድ ፕሮጀክቶችን እየፈለገ ነው። በመዋዕለ ንዋይ መመዘኛዎች እና በፕሮጀክቱ በተገለፀው የማህበረሰብ ጥቅም ላይ በመመስረት ፕሮጀክቶች ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ይደረጋሉ።

ከንግድ ማህበረሰብ ባለቤትነት (BCO) የገንዘብ ድጋፍ ጋር በሽርክና ለመሥራት ፍላጎት ያለው የመሬት/ ቤቶች ፕሮጀክት ተጠሪ ነዎት? የፕሮጀክት የገንዘብ ደጋፊ ተጠሪዎች የመሬት/ ቤቶች ንብረት አልሚዎች/ባለቤቶች፣ የአጎራባች የንግድ ወረዳ ድርጅቶች፣ ወይም ሌሎች የማህበረሰብ የገንዘብ ደጋፊ ተጠሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ። የገንዘብ ድጋፉ በሚቀጥሉት 12 ወራት ውስጥ ግንባታ የሚጀምሩ እና ከፍተኛ የመፈናቀል ስጋት ባለባቸው ሰፈሮች ውስጥ ግንባታ ሊጀምሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን ይፈልጋል።

የፕሮጀክት ምክረ ሀሳቦች

 • እኩልነት
  • የገንዘብ ድጋፍ የዘረኝነት እና የማህበራዊ እኩልነት የቅድሚያ ቦታዎች በሚሰጣቸው ፕሮጀክቶች ላይ መዋዕለ ንዋይ ያደርጋል።
  • የጥቁሮች፣ ተወላጆች፣ እና ሌሎች የቀለም ሰዎች (BIPOC)፣ አዲስ ሰፋሪዎች፣ ሴቶች እና የLGBTQ+ ባለቤትነት ንግዶችን ጨምሮ፣ ቅድሚያ ለከፍተኛ የመፈናቀል አደጋ ንግዶችን ለሚደግፉ ፕሮጄክቶች።
 • ተጽዕኖ
  • አነስተኛ፣ በአካባቢው በባለቤትነት ለተያዙ ንግዶች እንዳይፈናቀሉ የሚረዱ ወይም የተፈናቀሉ የንግድ ድርጅቶችን እንደገና ወደ ሌላ አካባቢ እንዲመለሱ የሚረዱ ፕሮጀክቶች።
  • ፕሮጀክቶች እና/ወይም የንግድ ባለቤቶች የማህበረሰብ ጥቅማጥቅሞችን የሚያቀርቡ እና አወንታዊ የተጎራባች ተፅእኖ እያሳዩ ያሉት። ቅድሚያ በርካታ ንግዶችን ለሚደግፉ ፕሮጀክቶች።
 • አዋጭነት
  • የንግድ ስራ ዘላቂነት እንደ ታሪካዊ ሽያጮች፣ የተጣራ ገቢ፣ የንግድ ስራ ልምድ እና ቆይታ፣ እና የቤት ኪራይ የመክፈል አቅም ያሉ።
  • ለ10 እና ከዚያ በላይ ዓመታት እየሰሩ ያሉ ንግዶች ቅድሚያ ከግምት ውስጥ በማስገባት አሁን ባሉ ንግዶች ላይ ያተኩሩ።
 • የፕሮጀክት ዝግጁነት
  • መሰረታዊ የፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ተለይቷል እና ደህንነቱ የተጠበቀ (የንግድ ቦታ ድርሻውን ሳይጨምር)
  • ፕሮጀክቱ የተጠናቀቀው የመጀመሪያ ደረጃ የቅድመ-ልማት ደረጃ እና የመጀመሪያ ንድፍ እና ወጪ አለው።
  • ፕሮጀክቱ የፍቃድ ማግኘት፣ የፋይናንስ፣ እና ግንባታን በተመለከተ የተወሰነ የጊዜ ሰሌዳ ዝርዝር አለው።
  • የልማት ቡድኑ ከህዝብ ዘንድ ለመድረስ እና የንግድ ስራ ሥፍራን በተመለከተ ስልታዊ ቅኝት ለማድረግ በቦታው መገኘት አለበት።

ፕሮጀክቶች በማንኛውም ጊዜ ሊቀርቡ ይችላሉ እና በሚንከባለል ተራ ላይ ተመስርቶ ይገመገማሉ። የፕሮጀክት ሀሳብዎን እዚህ ያቅርቡ።

ስለ የንግድ ማህበረሰብ ባለቤትነት (BCO) የገንዘብ ድጋፍ የበለጠ ለማወቅ ፍላጎት ያለው በሲያትል የአነስተኛ የንግድ ድርጅት ባለቤት ነዎት? የበለጠ ለማወቅ ፍላጎት ካልዎት፣ ከንግድ ማህበረሰብ ባለቤትነት የገንዘብ ድጋፍ ጋር መስራቱ ለንግድዎ ቀጣይ እርምጃ ትክክለኛው እርምጃ መሆኑን ለማየት ይህንን አጭር ቅጽ መሙላት ይችላሉ: የንግድ ፍላጎት ማሳያ ቅጽ

ጥያቄዎች?

የቋንቋ ትርጉም እርዳታ

 • ቅጾቹ ገቢ መሆን ያለባቸው በእንግሊዝኛ ነው። ቅጹን ለመሙላት እና ማንኛውንም ጥያቄ ለመመለስ እንዲረዳዎ የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሰራተኞች ይገኛሉ። የትርጉም ወይም የአስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለመጠየቅ፣ እባክዎን (206) 684-8090 ይደውሉ።

የሲያትል ከተማ፣ እያንዳንዱን ሰው በፕሮግራሞቹ እና በእንቅስቃሴዎቹ እንዲሳተፍ ያበረታታል። ለተጨማሪ ጥያቄዎች፣ ለትርጉም ወይም ለትርጓሜ፣ ለቴክኒክ ድጋፍ፣ ለአካል ጉዳተኝነት ማስተናገጃዎች፣ ተለዋጭ ይዞታዎች ላላቸው ቁሳቁሶች ወይም የተደራሽነት መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤትን በ (206) 684-8090 ወይም oed@seattle.gov ያግኙ።

Economic Development

Markham McIntyre, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 5752, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 94708, Seattle, WA, 98124-4708
Phone: (206) 684-8090
Phone Alt: (206) 684-0379
Fax: (206) 684-0379
oed@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Economic Development

The mission of the Office of Economic Development (OED) is to help create healthy businesses, thriving neighborhoods, and community organizations to contribute to a robust economy that will benefit all Seattle residents and future generations.