This content has been professionally translated in other languages.
Este contenido ha sido traducido profesionalmente a otros idiomas.
此內容已被專業翻譯成其他語言。
Nội dung này đã được dịch chuyên nghiệp sang các ngôn ngữ khác.
Qoraalkan waxaa si xirfad leh loogu turjumay luqado kale.
Ang nilalamang ito ay propesyonal na isinalin sa ibang mga wika.
이 콘텐츠는 전문적으로 다른 언어로 번역되었습니다.
ይህ ይዘት በሙያዊ በሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሟል።
የንግድ ፈቃዶች
- የንግድ ፈቃድ ረዳት (Business Licensing wizard) :- ስለ አዲሱ የንግድ እንቅስቃሴዎ (ለምሳሌ በሲያትል ከተማ ስለሚከፈት ምግብ ቤት) ጥቂት ጥያቄዎችን በመመለስ ለድርጅትዎ የሚሆን ዝርዝር መመሪያ ማግኘት ይችላሉ። መመሪያው ምን ዓይነት ፈቃዶች እንደሚያስፈልግዎት፣ ማንን ማነጋገር እንዳለብዎ እና ንግድዎን ለመጀመር የትኞቹን ቅጾች መሙላት እንዳለብዎ ያስረዳዎታል።
- የንግድ ፈቃዶች:- በሲያትል ውስጥ የንግድ ሥራ የሚሠራ ማንኛውም ሰው የሲያትል የንግድ ፈቃድ ግብር የምስክር ወረቀት (እንዲሁም የንግድ ፈቃድ ወይም አጠቃላይ የንግድ ፈቃድ በመባል የሚታወቅ) ፈቃድ ሊኖረው ይገባል። ይህንን የምስክር ወረቀት በየዓመቱ እስከ ታህሳስ (December) 31 ድረስ ማደስ አለብዎት። በFileLocal በኩል በኦንላይን ወይም በፖስታ ወይም በአካል በመቅረብ ማመልከት እና ማደስ ይችላሉ።
- የንግድ ፈቃድ ግብር (B&O ግብር):- የሲያትል የንግድ ፈቃድ ግብር ንግድዎ በሚያገኘው ጠቅላላ ገቢ ላይ የተመሰረተ ነው። እንዲሁም የንግድ እና ሥራ ግብር (B&O ግብር) ወይም የጠቅላላ ደረሰኝ ግብር ተብሎም ይጠራል። ይህንን ግብር የሚከፍሉት የንግድ እንቅስቃሴ ካለዎት እና ለዓመቱ የታክስ የሚከፈልበት ጠቅላላ ገቢዎ $100,000 ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ብቻ ነው። ገቢዎ ዜሮ ቢሆንም እንኳ ጠቅላላ ገቢዎን ለሲያትል ከተማ ሪፖርት ማድረግ አለብዎት። የሲያትል የንግድ ፈቃድ ግብር ከዋሽንግተን ግዛት B&O ግብር የተለየ ነው፣ ስለዚህ የሲያትል ግብሮችዎን ከግዛት ግብሮችዎ ለይተው ማቅረብ አለብዎት።
ግብሮች
- የመግቢያ ግብር:- የመግቢያ ግብር በሲያትል ውስጥ ለመዝናኛ ቦታዎች ወይም ዝግጅቶች ለመግባት ታዳሚዎች በሚከፍሉት የቲኬት ዋጋ ወይም ሌላ ክፍያ ላይ ይጨመራል ።
- በንግድ የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) የሚከፈል ግብር:- በንግድ የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) የሚከፈል ግብር አሽከርካሪዎች በንግድ ማቆሚያ ቦታዎች ለማቆም በሚከፍሉት ክፍያ ላይ ይጨመራል ።
- የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች ግብር:- የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች ግብር በሲያትል ከተማ ውስጥ የጦር መሳሪያዎችን ወይም ጥይቶችን በችርቻሮ ለሚሸጥ ማንኛውም ሰው ይጣላል።
- የቁማር ግብር:- የቁማር ግብር ከቢንጎ፣ ራፍልስ (raffles)፣ ፑል-ታብስ (pull-tabs)፣ ፓንች ቦርድ (punch boards) እና የመዝናኛ ጨዋታዎች ከሚገኘው ገቢ ላይ ይከፈላል።
- የሲያትል B&O ግብር:- የሲያትል የንግድ እና ሥራ ግብር (B&O ግብር ወይም የንግድ ፈቃድ ግብር በመባል የሚታወቅ) ንግዶች በሚያገኙት ጠቅላላ ገቢ ላይ ይተገበራል።
- የጣፋጭ መጠጦች ግብር:- የጣፋጭ መጠጦች ግብር ወደ ሲያትል በሚሰራጩ ጣፋጭ መጠጦች ላይ ይተገበራል።
- የሕዝብ አገልግሎት (ዩቲሊቲ) ታክስ:- የሕዝብ አገልግሎት (ዩቲሊቲ) ታክስ የሕዝብ መሠረታዊ አገልግሎቶችን (Public Utility Services) በሚያቀርቡ የንግድ ተቋማት ላይ የሚጣል ግብር ነው።
የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች የቆሻሻ እና የውሃ ደንቦች
- የውሃ መስመሮች መደበላለቅ ቁጥጥር እና የኋላ ፍሰት መከላከያ (Cross-Connection Control and Backflow Protection) :- የሲያትል ከተማ የመጠጥ ውሃ በህንፃዎች ውስጥ ባሉ ቧንቧዎች ውስጥ ሲያልፍ ንፁህ ሆኖ እንዲቆይ በማድረግ ጥበቃ ያደርጋል። የመስመር መደበላለቅ (Cross-connection) ማለት ጎጂ የሆኑ ነገሮች ወደ መጠጥ ውኃ ቧንቧ ውስጥ የሚገቡበት ችግር ነው። ይህንን ለመከላከል፣ የዋሽንግተን ግዛት እና የሲያትል የህዝብ መገልገያ (SPU) ደንበኞች የኋላ ፍሰት መከላከያዎችን (backflow preventers) እንዲጭኑ እና በየዓመቱ እንዲፈትሹ ያስገድዳሉ።
- የኋላ ፍሰት መስፈርቶች ግንባታው ከመጠናቀቁ በፊት መሟላት አለባቸው፣ ስለዚህ SPUን ቀደም ብለው በ spu_backflow@seattle.gov ማነጋገር የተሻለ ነው።
- የኋላ ፍሰት መገጣጠሚያ ለመትከል በኪንግ ካውንቲ የሕዝብ ጤና ጥበቃ በኩል የቧንቧ ሥራ ፈቃድ (Plumbing permit) ማውጣት ያስፈልጋል።
- ስብ፣ ዘይት እና ቅባት:- ማንኛውንም ዓይነት የምግብ ዝግጅትና መስተናግዶ የሚያካሂድ ድርጅት የስብና ቅባት ማጣሪያ መሣሪያ (Grease Interceptor) የመትከልና በየጊዜው የጥገና ክትትል የማድረግ ግዴታ አለበት። የወተት እና የወተት ተዋጽኦዎችን የሚያቀርቡ የቡና ቤቶች (ካፌዎች) ያሉ አነስተኛ የምግብ አገልግሎት ሰጪዎች እንኳን ቢሆኑ ስብ፣ ዘይት እና ቅባት ወደ ፍሳሽ ማውረጃው/ቧንቧው ውስጥ እንዳይገቡ ለመከላከል የስብና ቅባት ማጣሪያ የመትከል ግዴታ አለባቸው።
- የምግብ ማሸጊያ፣ የፕላስቲክ ፌስታል ከረጢቶች እና የምግብ ማቅረቢያ መሣሪያዎች መስፈርቶች፦
- የፕላስቲክ ከረጢት ክልከላ:- የሲያትል ህግ የግሮሰሪ እና የችርቻሮ መደብሮች ቀጭን የፕላስቲክ ከረጢቶችን እንዳይጠቀሙ ይከለክላል። መደብሮች ለእያንዳንዱ ትልቅ የወረቀት ከረጢት ስምንት ሳንቲም እና ለእያንዳንዱ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ከረጢት 12 ሳንቲም ማስከፈል አለባቸው።
- የምግብ ማሸጊያ እና የመምጠጫ (straw) መስፈርቶች:- በሲያትል ከተማ ሕግ መሠረት የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ከፎም (ስፖንጅ) የተሠሩ የምግብ መያዣዎችን፣ የፕላስቲክ መምጠጫዎችን (Straws) እና የፕላስቲክ የመመገቢያ ቁሳቁሶችን መጠቀም የተከለከለ ነው። እዚያው ተቀምጠው ለሚመገቡ ደንበኞች የሚሰጡ ማሸጊያዎች ወደ ማዳበሪያነት የሚቀየሩ (Compostable) መሆን አለባቸው።
- የምግብ ቆሻሻ መስፈርቶች፦ የሲያትል ሕግ የንግድ ድርጅቶች የምግብ ተረፈ ምርቶችን፣ ወደ ማዳበሪያነት የሚቀየሩ ወረቀቶችን እና የጓሮ/የአትክልት ቦታ ቆሻሻዎችን በመደበኛው የቆሻሻ መጣያ (ጋርቤጅ) ውስጥ እንዳይጥሉ ይደነግጋል። ሁሉም ምግብ እና በምግብ የቆሸሹ የወረቀት ምርቶች እንደ የወረቀት ፎጣዎች፣ የወረቀት ናፕኪኖች እና ካርቶን ኮምፖስት መደረግ አለባቸው።
- የእንደገና ጥቅም ላይ ማዋል (Recycling) ደንቦች:- የሲያትል ህግ ንግዶች እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ቁሳቁሶችን በመደበኛው የቆሻሻ መጣያቸው (ጋርቤጀ) ውስጥ እንዳያስገቡ ይደነግጋል። እንደ ወረቀት፣ ያልተበከለ ካርቶን፣ ጠርሙሶች፣ ኩባያዎች፣ ማሰሮዎች እና ጣሳዎች ያሉ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ቁሳቁሶች እንደገና ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው።
- የዝናብ ውሃ ደንቦች፡- የሲያትል የህዝብ መገልገያ (SPU) የተለያዩ በካዮች ወደ ዝናብ ውሃ ፍሳሽ ማስወገጃዎች እንዳይገቡ ለማረጋገጥ ንግዶችን ይፈትሻል። የሲያትል የዝናብ ውሃ ኮድ ንግዶች በጣቢያቸው እንቅስቃሴዎች ላይ በመመስረት የምንጭ መቆጣጠሪያዎችን፣ እንዲሁም ምርጥ የአስተዳደር ልምዶች (BMPs) ተብለው የሚጠሩትን እንዲጠቀሙ እና እንዲጠብቁ ይደነግጋል። ምርጥ የአስተዳደር ልምዶች የዝናብ ውሃ ከብክለቶች ጋር እንዳይገናኝ የሚከላከሉ እርምጃዎች ናቸው። ምሳሌዎች የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የተጋለጠ አፈርን መሸፈን፣ የቆሻሻ መያዣዎችን ከዝናብ ውሃ ፍሳሽ ማስወገጃዎች ማራቅ እና የፈሳሽ መፍሰስ መቆጣጠሪያ መሳሪያ (spill kit) ዝግጁ ማድረግን ያካትታሉ።