This content has been professionally translated in other languages.
Este contenido ha sido traducido profesionalmente a otros idiomas.
此內容已被專業翻譯成其他語言。
Nội dung này đã được dịch chuyên nghiệp sang các ngôn ngữ khác.
Qoraalkan waxaa si xirfad leh loogu turjumay luqado kale.
Ang nilalamang ito ay propesyonal na isinalin sa ibang mga wika.
이 콘텐츠는 전문적으로 다른 언어로 번역되었습니다.
ይህ ይዘት በሙያዊ በሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሟል።
ኪንግ ካውንቲ
- የንግድ ፈቃድ መረጃ (ይህ የሚያስፈልገው ባልተደራጀ የኪንግ ካውንቲ አካባቢ የሚሰሩ ከሆነ እና ንግድዎ ከተዘረዘሩት ቁጥጥር የሚደረግባቸው ተግባራት አንዱ ከሆነ ብቻ ነው፡፡)
- የምግብ ንግድ ፈቃዶች
- የምግብ ሰራተኛ ካርዶች
- የቧንቧና ፍሳሽ ስራ ፈቃዶች (የተበከለ ውሃ ወደ ዋናው መስመር እንዳይመለስ የሚከላከሉ መሣሪያዎችን (Backflow Assembly) ለመግጠም በህዝብ ጤና መምሪያ በኩል የቧንቧ ስራ ፈቃድ ማግኘት ግዴታ ነው)
- የንብረት ታክስ መረጃ
የዋሽንግተን ግዛት ዋና ጸሐፊ መሥሪያ ቤት (Washington Secretary of State)
- የንግድ ተቋምዎ የኮርፖሬሽን፣ የኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር (Limited Partnership)፣ የኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (LLC) ወይም የኃላፊነቱ የተወሰነ የሙያ አጋርነት ማህበር (LLP) ህጋዊ ሰውነት ያለው ከሆነ፣ ለንግድ ፈቃድ ማመልከቻ ከማስገባትዎ በፊት ከስቴት ዋና ጸሐፊ መሥሪያ ቤት (Secretary of State) ዘንድ ቅድመ-ምዝገባ ማከናወን አለብዎት፡፡
የዋሽንግተን ግዛት የገቢዎች መምሪያ
- የንግድ ፈቃዶች (በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ ለሚሰሩ ሁሉም ንግዶች ያስፈልጋል)
- የዳግም ሽያጭ ፈቃዶች (Reseller Permits)
- የልዩ ስራ ፈቃድ ማረጋገጫዎች (እንደ ሲጋራ ቸርቻሪዎች፣ የትምባሆ ምርቶች፣ ሊሙዚኖች ወይም የታክስ ተመኖች ያሉ)
- የግዛት ታክሶች እና መስፈርቶች
- የግዛት ንግድ እና የስራ ታክስ (እንዲሁም B&O ታክስ በመባል ይታወቃል)
- የግዛት አነስተኛ ንግድ B&O ታክስ ክሬዲት
- የግዛት ስራ አጥነት ኢንሹራንስ (አንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰራተኞችን የሚቀጥሩ ከሆነ ያስፈልጋል)
የዋሽንግተን ግዛት የሰራተኛ እና ኢንዱስትሪዎች መምሪያ
- የሰራተኞች ካሳ ኢንሹራንስ
- ታዳጊዎችን፣ ወጣቶችን እና የተለማማጅ ሠራተኞችን (ኢንተርኖችን) መቅጠር
- የምግብ መኪናዎች እና ተጎታች ቤቶች/ጋሪዎቸ (trailers)
የዋሽንግተን ግዛት ማህበራዊ እና ጤና አገልግሎቶች መምሪያ
- የዋሽንግተን ግዛት ህግ አሰሪዎች አዳዲስ እና እንደገና የተቀጠሩ ሰራተኞችን በሙሉ ስራ ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ በ20 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርጉ ያስገድዳል። እንደገና የተቀጠረ ሰራተኛ ማለት ቢያንስ ለ60 ተከታታይ ቀናት ለእርስዎ ያልሰራ ሰው ነው። የዕድሜ፣ የጾታ ወይም የሥራ ሰዓት ልዩነት ሳይደረግ የሁሉንም ሠራተኞች መረጃ በሪፖርት ማካተት ግዴታ ነው።
የዋሽንግተን ግዛት የስራ ስምሪት ደህንነት መምሪያ
- የስራ ስምሪት ደህንነት መምሪያ ለስራ ፈላጊዎች እና ለአሰሪዎች የስራ ኃይል አገልግሎቶችን ከመስጠት በተጨማሪ የግዛቱን የስራ አጥነት ኢንሹራንስ እና የሚከፈልበት የቤተሰብ እና የህክምና ፈቃድ ፕሮግራሞችን ያስተዳድራል።
የዋሽንግተን ግዛት የቁማር ኮሚሽን
- በንግድዎ ውስጥ ለማካሄድ ያቀዱት ማንኛውም የቁማር እንቅስቃሴ በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ ለመስራት ፈቃድ ይፈልጋል።
የዋሽንግተን ግዛት የአልኮል እና የካናቢስ ቦርድ
የዋሽንግተን ሎተሪ
- የሎተሪ ቲኬቶች እንደ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ምርቶች ይቆጠራሉ እና የሚሸጡት እና የሚተዳደሩት በዋሽንግተን ግዛት ሎተሪ እና ወኪሎቹ ነው። የዋሽንግተን ሎተሪ ቸርቻሪ ፈቃድ ዓላማ በRCW 67.70.040(1) ስር የተቋቋመ ሲሆን፣ የሎተሪ ኮሚሽኑ ቲኬቶችን እንዲሸጡ ወይም እንዲያከፋፍሉ ቸርቻሪዎችን የመፍቀድ ስልጣን እና ሃይል ይሰጣል።
የአገር ውስጥ ገቢዎች አገልግሎት
- የአሰሪ መለያ ቁጥር
- የፌዴራል የንግድ ታክስ ዓይነቶች (የሚያካሂዱት የንግድ አይነት ምን አይነት ታክስ መክፈል እንዳለብዎ እና እንዴት መክፈል እንዳለብዎ ይወስናል)