This content has been professionally translated in other languages.
Este contenido ha sido traducido profesionalmente a otros idiomas.
此內容已被專業翻譯成其他語言。
Nội dung này đã được dịch chuyên nghiệp sang các ngôn ngữ khác.
Qoraalkan waxaa si xirfad leh loogu turjumay luqado kale.
Ang nilalamang ito ay propesyonal na isinalin sa ibang mga wika.
이 콘텐츠는 전문적으로 다른 언어로 번역되었습니다.
ይህ ይዘት በሙያዊ በሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሟል።
ነሐሴ 2026 የተሻሻለ
የእኛ የአነስተኛ ንግድ መመሪያ መጽሐፍ እንደ አነስተኛ ንግድ ባለቤትነትዎ እርስዎን ለመደገፍ፣ እንዲያድጉ እና እንዲበለጽጉ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ይህ መመሪያ መጽሐፍ በሲያትል፣ እንዲሁም በኪንግ ካውንቲ እና በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ ንግድ ለማካሄድ የሚያስፈልጉ ደንቦችን እና መስፈርቶችን ያብራራል። አዲስ ንግድ ለመጀመርም ሆነ ነባር ንግድዎን ለማስፋፋት በሚፈልጉበት ጊዜ የሚረዱ አማራጭ የመረጃ እና የድጋፍ ምንጮችን ያቀርባል።
እርስዎን ለማገልገል እና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማቅረብ ዝግጁ ነን። ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት ወይም ከየት እንደሚጀምሩ ካላወቁ፣ እባክዎ ቢሯችንን ያነጋግሩ።
የሲያትል ከተማ፣ እያንዳንዱን ሰው በፕሮግራሞቹ እና በእንቅስቃሴዎቹ እንዲሳተፍ ያበረታታል። እርዳታ፣ ትርጉም፣ ለአካል ጉዳተኞች የሚደረጉ ማስተካከያዎች ወይም በተለየ ቅርጽ የተዘጋጁ ሰነዶች ከፈለጉ፣ እባክዎ ጽሕፈት ቤታችንን በ206-684-8090 ወይም በOED@seattle.gov ያነጋግሩ።
(ማሳሰቢያ-፡ ይህንን መረጃ በዓመት አንድ ጊዜ እናዘምነዋለን። እባክዎ የተሳሳተ መረጃ ካገኙ ቢሯችንን ያነጋግሩ።)