Amharic Language Information from Emergency Management
ቤትዎንና ቤተሰብዎን ያዘጋጁ
ኣደጋዎች(መቅዘፍቶች) ማስጠንቀቅያ ሳይሰጡ ሊከሰቱ ይችላሉ። ኣስቀድመው እቅድ በማውጣትም እራስዎን እና ቤተሰብዎን እርስ በእርስ እንድትጠባበቁ ማድረግ ኣስፈላጊ ነው። ሶስት እርምጃዎችን በመውሰድ በዚህ ረገድ ለውጥ ለማምጣት እገዛ ማድረግ ይቻላል።
- እቅድ ማውጣት - ኣደጋ( መቅዘፍት) በሚከሰትበት ጊዜ ሁሉም የቤተሰብ ኣባል በኣንድነት ላይኖር ይችላል። ስለዚህ ኣስቀድሞ ወደ ኣስተማማኝ ቦታ እንዴት መሄድ እንደሚቻል ፡ ብምን ዓይነት መልኩ መግባባት እንደሚቻል ፡ እንዲሁም ከአደጋው በሁዋላ የት መገናኘት እንደሚቻል ማቀድ ያስፈልጋል።
- ለአደጋ ጊዜ የሚጠቅሙ ነግሮችን ኣስቀድሞ ኣዘጋጅቶ መቆየት -ሊከሰት ከሚችሉ ኣደጋዎች ለማምለጥ የሚያስችሉ ኣስፈላጊ ነገሮች መሟላታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ቢያንስ እንኳን ውሃ፡ ምግብ፡ ባትሪ (ላምባዲና)ብርድን ለመከላከል እና እርጥበት እንዳይከሰት የሚያስችሉ ተጨማሪ ልብሶችና ብርድ ልብሶች፡ እንዲሁም የመጀመሪያ እርዳታ ለመስጠት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ኣስቀድሞ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።
- እርስ በእርስ መረዳዳት -ከጓደኛዎት እና ጎረቤትዎ ጋር ኣስቀድመው እቅድ በማውጣት የምትረዳዱበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት ይቻላል። የሚከተሉት ሊንኮች እርሶና ቤትሰብዎ ከእንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣሉ።
በኣማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ የኢመርጀንሲ ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን(የድንገተኛ ኣደጋ ሲጋጥም ምን እርምጃ መወሰድ እንዳለበት የሚገልጽ መረጃ)
- ለቤተሰብ የሚሆን ዝርዝር ዕቅድ (Family Plan)
- ኣደጋው ከደረሰበት ኣካባቢ ውጭ ያለ የቅርብ ሰው የቴሌፎን ቁጥር (Out of Area Contact)
- የመሬት መንቀጥቀን ሲደርስ ከኣደጋው ለመዳን ምን ማድረግ ይቻላል (How to be safe in an Earthquake)
- የድንገተኛ ኣደጋ በሚደርስበት ወቅት ምን መደረግ ኣለበት፡ የቤተሰብ የሚጠቅም ፕላን ወይም እቅድ እና ድንገት ኣደጋ ቢክሰት መያዝ ያለባቸው ኣስፈላጊ ነገሮች (Emergency Go Kit)
- ለኣደጋ ጊዜ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በዝርዝር ለማዘጋጀት ቃል መግባት (Preparedness Promise)
- ለኣደጋ ጊዜ የሚያስፈልግ ውሃ ኣዘጋጅቶ መቆየት-በሊትሮች (Storing Emergency Water - Liter)
- ለኣደጋ ጊዜ የሚያስፈልግ ውሃ ኣዘጋጅቶ መቆየት-በጋሎኖች (Storing Emergency Water - Gallon)
- የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰት ለመዳን እንዲቻል የሚጠቅም መጽሓፍን ክለር መቅባትን በሚመለከት (Quakesafe Coloring Book)
- ካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ ወይም ወደ ውስጥ ቢተንፍሱት የሚጎዳ ኣየር (Carbon Monoxide Safety)