የእኛ የአየር ንብረት ምላሽ

ሲያትል ውስጥ በመኪናዎች ወይም በጭነት መኪናዎች የሚደረጉ ጉዞዎች ዋና የአየር ብክለት እና የአየር ንብረት ለውጥ ምንጮች ናቸው። የእነዚህ ጉዞዎች አብዛኛዎቹ ከሶስት ማይል ያነሱ ናቸው እና በሕዝብ መጓጓዣ፣ በብስክሌት ወይም በእግር በመሄድ ሊወሰዱ ይችላሉ። ያ ማለት እርስዎ የሚያደርጓቸው የጉዞ ምርጫዎች በወደፊት የተፈጥሮ አካባቢያችን ላይ እንድ ትልቅ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። የሲያትል መጓጓዣ መምሪያ (SDOT) ቀጣይነት ያለው የመጓጓዣ አማራጮችን ለመደገፍ መንገዶቻችንን ለማሻሻል እየሰራ ነው። ፕላኔቷን የማይጐዱ የጉዞ መንገዶችን ለመምረጥ ቀላል፣ አስተማማኝ እና በዋጋ ተመጣጣኝ እንዲሆን እንፈልጋለን።

SDOT ዝቅተኛ ኃይል እና የጋራ የጉዞ መንገዶችን ለመምረጥ ቀላል ለማድረግ ከወዲሁ እየሰራ ነው። በማይበክሉ መንገዶች ለመጓዝ በመምረጥ፣ በሲያትል ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ፕላኔታችንን ለራሳችን፣ ለቤተሰቦቻችን እና ለኛ ጓደኞቻችን ጠብቆ ማቆየት ይችላል።

አስቀድመን በእቅዶቻችን፣ በፕሮጀክቶቻችን እና መንገዶቻችንን እንዴት እየቀየስን እንዳለን ላይ ለውጦችን እያደረግን ነው። የእኛ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ማዕቀፍ (CCRF) የበለጠ ቀጣይነት ያለው የጉዞ አማራጮችን እንድትመርጡ ለእርስዎ ቀላል ለማድረግ እንዴት እየሰራን እንዳለ ያሳያል። እና መንዳት በሚኖርብዎት ጊዜያት፣ ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች መቀየርን ቀላል ለማድረግ እየረዳን ነው።

በእኛ የአየር ንብረት ምላሽ አጠቃላይ እይታ (PDF) ውስጥ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ማንበብ ይችላሉ። 

ጥረቶቻችንን እያተኰርንበት ያለነው

ለተሻለ የወደፊት የአየር ንብረት አብሮ መስራት

የአየር ብክለትን ለመቀነስ እና የአየር ንብረት ለውጥን አስከፊ ተፅእኖ ለማስወገድ እና ከፍተኛ ጉዳት የሚደርስባቸውን ማህበረሰቦች ለመጠበቅ አሁኑኑ እርምጃ መውሰድ አለብን። ትክክለኛ መፍትሄዎችን ለማግኘት፣ ከአካባቢው ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከመጓጓዣ ፍትሃዊ እኩልነት የስራ ቡድንም ጋር ጨምሮ አብረን መስራታችንን እንቀጥላለን።

እኛ ማድረግ የምንፈልገው:

  • የአየር ንብረት ጥበቃ ተግባራችንን ማፋጠን።
  • ሃሳቦችን ለማውጣት ከማህበረሰቦች ጋር አብሮ መሥራት።

አጫጭር ጉዞዎችን አስተማማኝ፣ በዋጋ ተመጣጣኝ እና ዜሮ ብክለት ያላቸው ማድረግ

በሲያትል ውስጥ ብዙ ብክለት የሚመጣው ከ3 ማይሎች ያነሱ ርቀት ካላቸው አጭር ጉዞዎች ነው። በተለይ ለእነዚህ አጭር ርቀቶች በእግር ለመሄድ፣ በብስክሌት ለመጋለብ፣ ወይም ቀላል ሞተር ያላቸው ብስክሌቶችን/ ስኩተር ለመጠቀም ቀላል እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆኑ መንገዶቻችንን እና ፕሮግራሞቻችንን ለመፍጠር እና ለማሻሻል ከማህበረሰቦች ጋር እየሰራን ነው።

እኛ ማድረግ የምንፈልገው:

  • መንገዶችን በእግር ለመሄድ፣ በብስክሌት ለመጋለብ፣ ወይም ቀላል ሞተር ባላቸው ብስክሌቶች/ ስኩተሮች ለመጓዝ ለእያንዳንዱ ሰው ሁሉ የተሻለ ማድረግ።
  • ይበልጥ ሰዎች ብስክሌት እና የኤሌትሪክ ቀላል ሞተር ያላቸው ብስክሌት/ ስኩተር በመጋራት በአነስተኛ ወጪ እንዲጠቀሙ መርዳት።
  • ለብስክሌቶች፣ ቀላል ሞተር ላላቸው ብስክሌቶች/ ስኩተሮች እና ለሌሎች የመጓጓዣ ዘዴዎች ተጨማሪ የማቆሚያ ቦታ ማቅረብ።
  • ዝቅተኛ የአየር ብክለት ያለባቸው አካባቢዎችን ለመፍጠር ከማህበረሰቦች ጋር መሥራት።
  • በመጓጓዣ መረጃ እና አገልግሎቶች የማህበረሰብ እና የተንቀሳቃሽነት ማዕከሎችን መፍጠር።
  • ሰዎች ከስቴቱ የሚደረጉ ቅናሾችን በመጨመር፣ ኢ-ቢስክሌቶችን እንዲገዙ ለመርዳት ፕሮግራም ስለመጀመር ማሰብ።

የሕዝብ መጓጓዣን የተሻለ ቀላል ምርጫ ማድረግ

የሕዝብ መጓጓዣ ለረጅም ጉዞዎች በጣም ዘላቂ ምርጫ ነው፣ እና እርስዎን በተሻለ ለማገልገል አዲስ የቀላል ባቡር ጣቢያዎች ሲከፈቱ እና አውቶቡሶች አቅጣጫ ሲቀየሩ የበለጠ የተሻለ ይሆናል። ወደ አውቶቡሶች፣ ቀላል ባቡር፣ እና የመንገድ መኪናዎች የሚደርሱበትን መንገድ ማሻሻል ትልቅ የእቅዳችን አካል ነው።

እኛ ማድረግ የምንፈልገው:

  • በአውቶቡስ መስመሮች እና በተሻሉ ምልክቶች የሕዝብ መጓጓዣን ፈጣን እና አስተማማኝ ማድረግ።
  • በሳውንድ ትራንዚት (Sound Transit) ላይ ያሉ አጋሮቻችን ቀላል ባቡርን እንዲሰፋ መርዳት።
  • ተጨማሪ የአውቶቡስ አገልግሎትን በሲያትል የሕዝብ መጓጓዣ መለኪያ መደገፍዎን መቀጠል።
  • የሕዝብ መጓጓዣን ለመጠቀም ቀላል የሚያደርጉ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ማበረታታት።

ለአየር ንብረት ተስማሚ የጉዞ አማራጮችን ማበረታታት

በእግር መሄድ፣ ብስክሌት መጋለብ እና የሕዝብ መጓጓዣን የሚያበረታቱ ፕሮግራሞችን ማደግ እንቀጥላለን። እነዚህ ምርጫዎች ለጤናዎ የተሻሉ፣ መንገዶችን ደህንነታቸው ይበልጥ የተጠበቀ ያደረጉ፣ የአካባቢ ሱቆችን የሚደግፉ፣ ለእርስዎ ገንዘብ የሚቆጥብ እና የአየር ብክለትን የሚቀንሱ ናቸው።

እኛ ማድረግ የምንፈልገው:

  • ይበልጥ ብዙ ሰዎችን ከጉዞ ፕሮግራሞቻችን ጋር ማገናኘት።
  • ብዙ ሰዎች በተቀነሰ ታሪፎች እና አዲስ የክፍያ አማራጮች ለሕዝብ መጓጓዣ ተመጣጣኝ ዋጋ መርዳት።

ማድረሶችን ማሻሻል

ሸቀጦችን ማንቀሳቀስ እና ለአየር ንብረት ተስማሚ በሆኑ መንገዶች ማድረስ ለፕላኔቷ እና ለንግድ ስራዎች መልካም ነው። ከሁሉ ይልቅ ምርጥ የሆኑ መፍትሄዎችን ለማግኘት ከንግዶች እና የአቅርቦት አገልግሎቶች ጋር መስራት እንፈልጋለን።

እኛ ማድረግ የምንፈልገው:

  • ትክክለኛው የአቅርቦት ተሽከርካሪዎች መጠን ማበረታታት።
  • ዝቅተኛ የአየር ብክለት አቅርቦት አማራጮችን ለመጠቀም ቀላል እና ርካሽ ማድረግ።
  • ለንግዶች ተጨማሪ የጭነት ቀጠናዎችን/ ዞኖችን መጨመር።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መጨመር

አንዳንድ ጉዞዎች በመኪና ወይም በጭነት መኪና መሆን አለባቸው። እስከተቻለ መጠን ከእነዚህ ጉዞዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲሆኑ እንፈልጋለን። ከሌሎች ጋር በመሆን የባትሪ መሙያ ጣቢያዎችን በማስቀመጥ እና ማበረታቻዎችን በመስጠት ከከተማችን ተሽከርካሪዎች ጋር ለሌሎች ምሳሌ ለመሆን እየሰራን ነው።

እኛ ማድረግ የምንፈልገው:

  • ሰዎች ወደ ኤሌክትሪክ የግል ተሽከርካሪዎች እንዲቀይሩ መርዳት።
  • ንግዶች ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲቀይሩ ማገዝ።
  • ወደ ኤሌክትሪክ አውቶቡሶች መቀየርን መደገፍ።
  • ሁሉንም የከተማ መኪናዎች ኤሌክትሪክ ማድረግ።

ሲያትል አረንጓዴ ሆና እንድትቆይ እንዴት መርዳት ይችላሉ?

  • እንዴት እንደሚዘዋወሩ ማሰብ። ከመንዳት ይልቅ በእግር መሄድ፣ ብስክሌት መጋለብ ወይም የሕዝብ መጓጓዣ መጠቀም ይችላሉ? በጉዞዎን ይገልብጡ ላይ የእርስዎን የጉዞ ልማዶች ከእኛ ጋር እንዴት መቀየር እንደሚችሉ ማየት።
  • ስላሏቸው ንጹህ የጉዞ አማራጮች ሁሉ ለእርስዎ ቤተሰብ እና ለጓደኞችዎ መንገር! እና ከዚያ፣ እነርሱን ለጉዞው ይዞ መምጣት!
  • መጓጓዣ ለእርስዎ እና ለእርስዎ ማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥን እንዴት እንደሚጎዳ ውይይቱን መቀላቀል። በSDOT የአየር ንብረት እርምጃዎች ላይ ወቅታዊ መረጃ እያገኙ ለመቆየት ይህንን ገጽ ዕልባት ያድርጉበት።
  • ከሁሉም በላይ ጠቃሚነት ያለው፣ ተስፋ ያለ መቁረጥ! የአየር ንብረት ለውጥን ማስተካከል እኛ ብቻችንን አንችልም፣ ግን እያንዳንዱ ጉዞ ይታሰባል እና እርስዎም የለውጡ አካል መሆን ይችላሉ - በአንድ ጊዜ አንድ ጉዞ።

Transportation

Greg Spotts, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.