የፍጆታ አገልግሎት ክፍያዎን ይቀንሱ

የሲያትል ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (Seattle City Light፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት) እና የሲያትል የህዝብ አገልግሎቶች (Seattle Public Utilities፣ የውሃ፣ የፍሳሽ እና የቆሻሻ አገልግሎቶች) የፍጆታ ክፍያዎን እንዲቆጣጠሩ የሚያግዙ ፕሮግራሞችን ያቀርባሉ።

ለሚከተሉት ፕሮግራሞች ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፦

  • የፍጆታ አገልግሎት ቅናሽ ፕሮግራም (Utility Discount Program)፦ በየወሩ ከ50-60% የሚሆን የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ ቅናሽ
  • የሂሳብ ክፍያ እርዳታ፦
    • የሲያትል ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (Seattle City Light)፦ ለኤሌክትሪክ ክፍያ በየዓመቱ ከ$250 እስከ $750 ወይም ከዚያ በላይ
    • የሲያትል የህዝብ አገልግሎቶች (Seattle Public Utilities)፦ ለውሃ፣ ፍሳሽ እና ቆሻሻ ክፍያ በየዓመቱ $500 ወይም ከዚያ በላይ

የፍጆታ አገልግሎት እርዳታ ለማግኘት ብቁ መሆንዎን ያረጋግጡ።

ያለብዎትን ቀሪ ሒሳብ ለመክፈል እርዳታ ያግኙ

የክፍያ ዕቅድ ያዘጋጁ

የሲያትል ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (Seattle City Light) እና የሲያትል የህዝብ አገልግሎቶች (Seattle Public Utilities) ሒሳብዎን ለመክፈል ተጨማሪ ጊዜ እንዲያገኙ የሚያስችሉ የክፍያ ዕቅዶችን ያቀርባሉ።

አገልግሎትዎ ሊቋረጥ እንደሆነ የሚያሳውቅ ማሳወቂያ ደርሶዎታል?

በ (206) 684‑3000 ይደውሉልን (ከሰኞ – አርብ፣ ከ 7:30 ኤ.ኤም – 6 ፒ.ኤም)።

የትርጉም አገልግሎት ያለምንም ወጪ እናቀርባለን።

ለበለጠ መረጃ የሲያትል ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (Seattle City Light) እና የሲያትል የህዝብ አገልግሎቶች (Seattle Public Utilities) ድረ-ገጾችን ይጎብኙ።

  • በስምዎ የተመዘገበ የሲያትል ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (Seattle City Light) ወይም የሲያትል የህዝብ አገልግሎቶች (Seattle Public Utilities) አካውንት ይኑርዎት
  • አገልግሎቱን ለማግኘት የሚጠቀሙበት አድራሻ የመኖሪያ ቤት መሆን አለበት (የንግድ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ብቁ አይደሉም)
  • አጠቃላይ የቤተሰብ ገቢዎ በፕሮግራሙ የተወሰኑ የገቢ መስፈርቶች ውስጥ መሆን አለበት

የገቢ ትርጓሜዎች

  • የቤተሰብ ገቢ (ከግብር በፊት)፦ በቤትዎ ውስጥ የሚኖሩ ሁሉም ሰዎች ከግብር በፊት የሚያገኙት ጠቅላላ ገቢ።
  • የቤተሰብ አባላት ብዛት፦ ከእርስዎ ጋር የሚኖሩ ሁሉም ሰዎች (የቤተሰብ አባላት፣ አብረውዎት የሚኖሩ ሰዎች እና ሌሎች)፣ ዝምድና ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም።

የ 2026 የገቢ መመሪያዎች

የፍጆታ አገልግሎት ቅናሽ ፕሮግራም

ለኤሌክትሪክ እና ለውሃ ክፍያዎች የሚደረግ ቀጣይነት ያለው ወርሃዊ ቅናሽ።

የቤተሰብ አባላት ብዛት ወርሃዊ ገቢ (ከግብር በፊት) ዓመታዊ ገቢ (ከግብር በፊት)
1 $4,269 $51,228
2 $5,582 $66,984
3 $6,895 $82,740
4 $8,209 $98,508
5 $9,522 $114,264
6 $10,836 $130,032
7 $11,082 $132,984
8 $11,328 $135,936
9 $11,575 $138,900
10 $11,821 $141,852
ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ሰው +$247 +$2,964

የአስቸኳይ ጊዜ የክፍያ እርዳታ እና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፕሮግራም (Emergency Bill Assistance and Emergency Assistance Program)

ለኤሌክትሪክ እና ለውሃ ክፍያዎችዎ እርዳታ ያግኙ።

የቤተሰብ አባላት ብዛት ወርሃዊ ገቢ (ከግብር በፊት) ዓመታዊ ገቢ (ከግብር በፊት)
1 $4,878 $58,536
2 $6,379 $76,548
3 $7,881 $94,572
4 $9,382 $112,584
5 $10,883 $130,596
6 $12,384 $148,608
7 $12,665 $151,980
8 $12,947 $155,364
9 $13,228 $158,736
10 $13,509 $162,108
ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ሰው +$281 +$3,372

የፕሮጀክት ሼር (Project Share)

ለኤሌክትሪክ ክፍያ የሚደረግ ተጨማሪ እርዳታ።

የቤተሰብ አባላት ብዛት ወርሃዊ ገቢ (ከግብር በፊት) ዓመታዊ ገቢ (ከግብር በፊት)
1 $7,680 $92,160
2 $8,784 $105,408
3 $9,876 $118,512
4 $10,960 $131,520
5 $11,840 $142,080
6 $12,720 $152,640
7 $13,596 $163,152
8 $14,484 $173,808
9 $15,348 $184,176
10 $16,225 $194,700
ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ሰው +$875 +$10,500

የገቢ መስፈርቶች በየዓመቱ ይዘመናሉ።

ብቁ ነዎት? ለፍጆታ አገልግሎት እርዳታ አሁኑኑ ያመልክቱ

አንድ ማመልከቻ ብቻ በመሙላት ለተለያዩ ፕሮግራሞች መመዝገብ ይችላሉ።

  • በኦንላይን ያመልክቱ (በብዙ ቋንቋዎች ይገኛል)
  • የወረቀት ማመልከቻ ቅጽ (PDF) ያውርዱ</1> እና በፖስታ፣ በፋክስ ወይም በኢሜይል ያስገቡ።
  • 810 3rd Ave, Suite 440, Seattle, WA 98104 ላይ የሚገኘውን የሰብዓዊ አገልግሎቶች መምሪያ - ማዕከላዊ ሕንጻ (Human Services Department - Central Building) ይጎብኙ (ከሰኞ - አርብ፣ ከ 8 - 10 ኤ.ኤም እና ከ12 - 2 ፒ.ኤም)። የትርጉም አገልግሎት ያለምንም ክፍያ ማግኘት ይችላሉ።

የአካውንት መረጃዎን ያረጋግጡ

  • ስምዎ በፍጆታ አገልግሎት ሒሳቡ (Bill) ላይ መኖሩን ያረጋግጡ። ካልሆነ፣ የአካውንት ባለቤቱን እንዲያመለክት ይጠይቁ።
  • የአካውንት ቁጥርዎን ያግኙ፦

ሰነዶችዎን ያዘጋጁ

  • በቤትዎ ውስጥ ለሚኖሩ 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሁሉም አዋቂዎች የፎቶ መታወቂያ
  • 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሁሉም አዋቂዎች የገቢ ሰነዶች
    • የስናፕ (SNAP) እርዳታ ተጠቃሚ ነዎት? ስምዎ በሲቲ ላይት (City Light) ሒሳብ መጠየቂያ ላይ የሚገኝ ከሆነ እና የስናፕ (SNAP) ተጠቃሚ ከሆኑ፣ የዲ.ኤስ.ኤች.ኤስ (DSHS) የድጋፍ ደብዳቤዎን ብቻ ማቅረብ ይበቃል። ለማመልከት ሌሎች የገቢ ሰነዶች አያስፈልጉም።

ሰነዶችዎን በሚከተሉት ቦታዎች ያለምንም ክፍያ ስካን ማድረግ፣ ኮፒ ማድረስ፣ ማተም ወይም በፋክስ መላክ ይችላሉ፦

ከማመልከቻዎ ጋር፣ በቤትዎ ውስጥ ለሚኖሩ 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሁሉም አዋቂዎች የፎቶ መታወቂያ ያቅርቡ።

ተቀባይነት ያላቸው የፎቶ መታወቂያ (ID) ዓይነቶች፦

  • የስቴት መንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ
  • ፓስፖርት
  • የአሜሪካ ወታደራዊ መታወቂያ
  • የጎሳ (ትራይባል) መታወቂያ
  • የቋሚ ነዋሪነት ካርድ

የመታወቂያውን የፊት ገጽ ወይም የፓስፖርቱን የፎቶ ገጽ ቅጂ ብቻ ማቅረብ በቂ ነው። ባለፈው 1 ዓመት ውስጥ ጊዜው ያለፈባቸውን መታወቂያዎችም እንቀበላለን።