Amharic / አማርኛ

በሲያትል ምርጫዎች ላይ ድምፅዎ እንዲሰማ ያድርጉ

የዲሞክራሲ ቫውቸሮች የሲያትል ነዋሪዎች በሲያትል ከተማ ምርጫ ላይ ለሚደግፏቸው እጩዎች የገንዘብ መዋጮ የሚያደርጉበት መንገድ ነው። ፕሮግራሙ በመርጫ ሂደት በጸደቀ የንብረት ታክስ አማካኝነት የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ሲሆን፣ ይህም አማካይ የንብረት ባለቤት የሆነውን ግለሰብ በዓመት $13 ዶላር ያህል ያስወጣዋል።

የዲሞክራሲ ቫውቸር ምንድን ነው?
የሲያትል ከተማ ለነዋሪዎች የዲሞክራሲ ቫውቸሮችን የሚሰጥ ሲሆን፣ እነዚህም በአካባቢው ለሚካሄዱ የምርጫ ቅስቀሳዎች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የሚያገለግሉ የምስክር ወረቀቶች ናቸው። በ2026 ዓ.ም ላይ የዲስትሪክት 5 የሲያትል ነዋሪዎች ሁለት የ$50 ዶላር የዲሞክራሲ ቫውቸሮችን ያገኛሉ።

የዲሞክራሲ ቫውቸሮችን ለምን ይጠቀማሉ?
ተሳትፎዎ ለውጥ ያመጣል። የዲሞክራሲ ቫውቸር ፕሮግራሙ ለምርጫ ቅስቀሳዎች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ እና ለምርጫ የሚወዳደሩ የሲያትል ነዋሪዎችን ቁጥር እና ብዝሃነት ለመጨመር ረድቷል። 

የዴሞክራሲ ቫውቸር መቀበል የሚችሉት የትኛዎቹ እጩ ተወዳደሪዎች ናቸው?
ለ2026 ዓ.ም ዘመቻዎቻቸውን ለመደገፍ ቫውቸሮችዎን መቀበል የሚችሉት የሲያትል ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ደረጃ ቦታን ለማግኘት የሚወዳደሩ ተሳታፊ እጩዎች ብቻ ናቸው።

ስለ እጩ ተወዳዳሪዎቹ እንዴት ማወቅ እችላለሁ? 
ተሳታፊ እጩ ተወዳዳሪዎችን በ እጩ ተወዳዳሪዎች ገፁ ላይ ማግኘት ይችላሉ። ስለ እጩዎቹ የበለጠ ለማወቅ የእጩ ተወዳዳሪ መግቢያዎቻቸውን ያንብቡ።

ቀጣዩ የሲያትል ከተማ ምርጫ የሚካሄደው መቼ ነው?
ቀጣዩ የሲያትል ከተማ ምርጫ የሚካሄደው 2026 ዓ.ም ላይ ነው። የዲሞክራሲ ቫውቸሮች ከተቀበሏቸው ጊዜ ጀምሮ እስከ ኖቬምበር 30 ቀን 2026 ዓ.ም ድረስ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

የሚከተሉትን መስፈርቶች ካሟሉ የዲሞክራሲ ቫውቸሮችን ማግኘት ይችላሉ፦

  • የሲያትል ነዋሪ ከሆኑ፣
  • ዕድሜዎ ቢያንስ 18 ዓመት ከሆነ፣ እና
  • የዩ.ኤስ ዜጋ፣ አሜሪካዊ ወይም ሕጋዊ ቋሚ ነዋሪ ከሆኑ።

የዲሞክራሲ ቫውቸሮችን ለመቀበል የተመዘገበ መራጭ መሆን አይጠበቅብዎትም። ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ከሆነ ቫውቸሮችን ለመቀበል ማመልከት ይችላሉ።

ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ ካለዎት እባክዎ ወደ (206) 727-8855 ይደውሉ። ነጻ የአስተርጓሚ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።