የሲያትል ፊልም ኮሚሽን (SFC) የሲያትልን የፊልም ኢንደስትሪ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ወደፊት በሚያስኬዱ ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች ላይ ለሲያትል ከተማ ምክር እና የሃሳብ አቅራቦቶችን ይሰጣል። ግቡ ለአካባቢው የፊልም ኢንዱስትሪ ንግዶች እና ሰራተኞች የእድገት እድሎችን መስጠት፣ የተሰጥኦ ችሎታዎችን ከጥራት ስራዎች ጋር ማገናኘት፣ በኢንዱስትሪው ውስጥ የዘር እኩልነትን ማሳደግ እና ሲያትልን ለፊልም አምራችነት ማራኪ ቦታን ማድረግ ነው።
ለሲያትል ፊልም ኮሚሽን ማመልከቻዎች እና የእጩ ምርጫዎች እስከ መጋቢት 12 ቀን 2023፣ ከምሽቱ 11፡59 ድረስ ይቀበሏል።
ማመልከቻው እና የሚሰጡ የምክር ሀሳብ ቅጾች የሚቀርቡት በእንግሊዝኛ መሆን አለባቸው። የእርስዎን ቅጾች ለመሙላት ወይም ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲረዱዎት የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሰራተኞች ይገኛሉ። የትርጉም ወይም የአስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለመጠየቅ፣ እባክዎን (206) 684-8090 ይደውሉ።
ለማመልከት ፍላጎት አለዎት? |
እባክዎን ይህን አጭር ማመልከቻ ይሙሉ: የሲያትል ፊልም ኮሚሽን አባል ማመልከቻ ቅጽ። የስራ/ ትምህርት ታሪክ ማስረጃዎን እና አጭር የግብ መግለጫን ማካተት ያስፈልግዎታል። |
አንድ የፊልም ኢንደስትሪ ባለሙያን እጩ መምረጥ ይፈልጋሉ? |
በዚህ አገናኝ አማካይነት የአስተያየት ምክሮችን ማስገባት ይችላሉ: የሲያትል ፊልም ኮሚሽን የአባል የምክር ሀሳብ ቅፅ። |
የማመልከቻ እና የእጩ መምረጥ ሂደት |
ቅጾቹ መግባት ያለባቸው በእንግሊዝኛ ነው። የእርስዎን ቅጾች ለመሙላት ወይም ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲረዱዎት የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሰራተኞች ይገኛሉ። የማስገቢያው ክፍለ ጊዜ መጋቢት 12 ቀን 2023 ከተዘጋ በኋላ፣ የከንቲባው ጽ/ቤት እና የከተማው ምክር ቤት በሲያትል ፊልም ኮሚሽን ላይ የሚቀመጡትን አባላትን ይመርጣሉ። |
እርዳታ ይፈልጋሉ ወይም ጥያቄዎች አለዎት? |
እባክዎን ለእርዳታ (206) 684-8090 ይደውሉ እና በድምጽ መልእክት መቀበያዎ ውስጥ የሚከተሉትን መረጃ ያስተውሉ: ስም፣ የስልክ ቁጥር፣ የተመረጠው ቋንቋ፣ እና የተፈለገው የድጋፍ አይነት። |
ያሉ የተመራጭ የሥራ ደረጃዎች |
የሲያትል ፊልም ኮሚሽን 11 ከፊልም ጋር የተዛመዱ የሙያ ዘርፎችን የሚወክሉ 11 አባላት ያሉት የተለያዩ የፊልም ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ቡድን ይሆናል።
|
በቀጣይነት የሚኖሩ ፕሮግራሞች ወይም እርዳታ |
ስለ ሌሎች ፕሮግራሞች ከኢኮኖሚ ልማት ጽህፈት ቤት ዝመናዎችን ለማግኘት እባክዎ ለጋዜጣችን ይመዝገቡ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይከተሉን: @SeattleEconomy በ Twitter፣ Instagram፣ እና Facebook። |
የሲያትል ከተማ እያንዳንዱ ሰው ሁሉ በፕሮግራሞቹ እና በእንቅስቃሴዎቹ እንዲሳተፍ ያበረታታል። ለተጨማሪ ጥያቄዎች፣ ለትርጉም ወይም ለትርጓሜ፣ ለቴክኒካዊ ድጋፍ፣ ለአካል ጉዳተኝነት ማስተናገጃዎች፣ ተለዋጭ ይዞታዎች ላላቸው ቁሳቁሶች ወይም የተደራሽነት መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤትን በ (206) 684-8090 ወይም oed@seattle.gov ያግኙ።