ስለ ኣነስተኛ የንግድ ድርጅት የማረጋግያ ፈንድ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች፡

1. ይህ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ዙር ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ለአዲስ አመልካቾች ክፍት ነው?

የሲያትል ከተማ ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ማመልከቻዎችን ከአሁን በኋላ አይቀበልም።

2. ማመልከቻዎች ለመቼ ናቸው?

ማመልከቻዎች ህዳር 14 ቀን 11:59 ከሌሊቱ ድረስ መግባት አለባቸዉ። የዘገዩ ማመልከቻዎችን አንቀበልም።

3. ስንት ሰዎች በቀደሙት ዙሮች አመልክተዋል፣ እና ስንቱን የእርዳታ ስጦታዎች ከፍለዋል?

የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ በመጋቢት 2020 ሲከፈት የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት በመጀመሪያው ዙር ወደ 9,000 የሚጠጉ ማመልከቻዎችን ተቀብሏል። በህዳር 2020 በሁለተኛው የማመልከቻ ዑደት ወቅት፣ ከ4,000 በላይ ማመልከቻዎች ቀርበዋል።

እስከዛሬ ድረስ፣ በመላው ሲያትል በወረርሽኙ በተከሰተው የኢኮኖሚ ውድቀት ለተጎዱ እስከ 1,500 የሚጠጉ አነስተኛ ንግዶች የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ከ$10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ አበርክቷል።

ለተጨማሪ መረጃ የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ የስጦታ ተሸላሚዎችን የውሂብ ጎታ ይጎብኙ።

4. ለማረጋጊያ ፈንድ የዕርዳታ ስጦታዎች የገንዘብ ምንጩ ምን ነበር?

የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ባለፉት አምስት ዙሮች በሲያትል ከተማ አጠቃላይ ፈንድ እና በፌዴራል የማህበረሰብ ልማት የተዋሰኑ የፋይናንስ ተቋሞች የገንዘብ ድጋፍ (CDBG) መዋጮ የተደረገላቸው። ስድስተኛው ዙር የማረጋጊያ ፈንድ በአሜሪካ የማዳኛ ዕቅድ ሕግ (ARPA) መሠረት በተቋቋመው የኮሮናቫይረስ አካባቢያዊ የፊስካል ማገገሚያ ፈንድ (CLFR) ገንዘብ ነው ድጋፍ የተደረገለት።

5. የብቁነት መስፈርቶች ምንድን ናቸው?

ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ብቁ ለመሆን ብቁ የሆኑ ንግዶች መሆን ያለባቸው:

  • በCOVID-19 ወረርሽኙ ምክንያት እንደ የንግድ መቋረጦች ወይም መዘጋቶች ያሉ እና ተዛማጅ የጤና እና ደህንነት ገደቦች የተጐዱ።
  • አሁን የሚሠራ የሲያትል የንግድ ሥራ ፈቃድ ያልዎት።
  • የከተማ የንግድ እና ሙያ (B&O) ግብሮችን አስገብተው እና ዕዳ ካለባቸው ግብራቸውን ሙሉ በሙሉ የከፈሉ።
  • ሁሉንም የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ ህጎች እና ደንቦችን አክብረው የተገኙ።
  • በአንድ ንግድ፣ አድራሻ፣ ቤተሰብ፣ የሰራተኛ መለያ ቁጥር (EIN)፣ ወጥ የሆነ የንግድ መታወቂያ ቁጥር (UBI) እና/ወይም የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር አንድ ማመልከቻ ብቻ ያስገቡ።

ቦታ:

  • በሲያትል ከተማ ወሰኖች ውስጥ ያሉ።
  • በቀረበው የንግድ እና ሙያ (B&O) የግብር ተመላሾች በኩል በሚረጋገጠው፣ አካላዊ አድራሻ እና በሲያትል ውስጥ የሚሠራ ያለው። የንግድዎ የግብር ተመላሾች የሲያትል አድራሻውን ካልጠቀሰው፣ ብቁ እንዳልሆኑ ይቆጠራሉ።
    • የተለየ ሁኔታ: የፈጠራ ሠራተኞች፣ የጭነት የምግብ መኪኖች እና የአርሶ አደሮች ገበያ ሻጮች። እነዚህ ንግዶች በአሁኑ ጊዜ በሲያትል ከተማ ውስጥ የንግድ ሥራ መሥራት እና በጣም ተደጋጋሚ የሆነውን የሲያትል አድራሻቸውን ማቅረብ አለባቸው።
  • ከሁለት ቦታዎች ያልበለጠ ያላቸው።

መጠን:

  • እስከ 50 የሚደርሱ የሙሉ ጊዜ አቻ ሠራተኞች ያለው።
  • እስከ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ($2,000,000 ዶላር)፣ ነገር ግን ቢያንስ አንድ ሺህ ዶላር ($1,000 ዶላር) በዓመት የተጣራ ገቢ ያለው፣ ብቸኛ ባለቤት፣ ሲ (C)-ኮርፖሬሽን፣ ኤስ (S)-ኮርፖሬሽን፣ የጋርዮሽ ንግድ፣ ወይም የውስን ተጠያቂነት የጋርዮሽ ኩባንያ የሆነ።
    • የሲያትል ፋይናንስ እና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች መምሪያ ይህንን ኪሳራ በንግድ ሥራው የ2019 እና 2020 የንግድ እና ሙያ (B&O) ግብሮች ውስጥ የገቢ ዘገባ በኩል ይወስናል።

ክወናዎች:

  • በአሁኑ ጊዜ ለንግድ ክፍት እና የሚሠራ ይሁኑ።
  • ከጥቅምት 19 ቀን 2019 በፊት መሥራት የጀመረ።
  • በግል ባለቤትነት የተያዘ፣ ልዩ የመሸጥ ፈቃድ ያልሆነ (non-franchise) እና ሰንሰለት-አልባ የሆነ ንግድ።

የገቢ ኪሳራ:

  • በከተማ የንግድ እና ሥራ (B&O) መረጃ መሠረት የተተገበረውን ዓመታዊ የተጣራ ኪሳራ ወይም ጠቅላላ የእርዳታ ስጦታውን መጠን የሚበልጥ ያለው።

ለትርፍ ያልተቋቋመ አካላት ተጨማሪ መመዘኛዎች:

  • የተውነት ጥበባት፣ የባህላዊ ተቋም ወይም የንግድ ቴክኒካዊ ድጋፍ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሆነ።
  • ከዋሽንግተን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር የሚሠራ ለትርፍ ያልተቋቋመ የአቋም ሁኔታ ያለው።

6. የትኞቹ ንግዶች ናቸው ለማመልከት ብቁ የማይሆኑ?

ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ለማመልከት ብቁ ያልሆኑ ንግዶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • ባልተቋቋመ የኪንግ ካውንቲ ውስጥ የሚገኙ ንግዶች።
  • ንግዶቹ በፌዴራል፣ በክልል ወይም በአከባቢ ሕግ ሥር/ መሠረት በማንኛውም ሕገ-ወጥ በሆነ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሰማራ።
  • የሚከተሉት የ1099 ገለልተኛ ተቋራጮች:
    • የአጭር ወይም የረጅም ጊዜ የኪራይ ባለቤቶች ወይም የኢንቨስትመንት ንብረት (Airbnb፣ Vrbo፣ ወዘተ ጨምሮ)።
    • የግል ሰፊ የቤት ሕንፃ (ገለልተኛ አከራዮች)።
    • የተሳፋሪ አክሲዮኖችን፣ ታክሲዎችን፣ የምግብ ማቅረቢያ አገልግሎትን እና (እንደ ኡበር፣ ሊፍት፣ ቢጫ ካቢ፣ የበር ዳሽ (Door Dash)፣ የኡበር ምግቦች፣ ወዘተ ያሉ) የመኪና አገልግሎቶችን
  • ከሥነ ጥበብ፣ የባህል ተቋማት እና የንግድ ቴክኒካዊ ድጋፍ ሰጪ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች በስተቀር ለትርፍ ያልተቋቋሙ የ501 (c)(3)፣ 501 (c)(6) ወይም 501 (c)(19) አካላት።

7. ብቃት ያላቸው ተሸላሚዎች እንዴት ይመረጣሉ?

የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ከተዘጋ በኋላ የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት ህዳር 15 ቀን 2021 ማመልከቻዎችን መገምገም እና የገንዘብ ድጋፍ ስጦታ ተቀባዮችን መምረጥ ይጀምራል።

አመልካቾች የተጠናቀቀ ማመልከቻን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ማስገባት አለባቸው። ያልተሟሉ ማመልከቻዎች እና በመጀመሪያው ግምገማ ላይ የመነሻ ዝቅተኛ የብቁነት መስፈርቶችን የማያሟሉ ማመልከቻዎች ብቁ እንዳልሆኑ ተደርገው እና ከተጨማሪ ግምት ይወገዳሉ። የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት አንድ ማመልከቻ ብቁ መሆን አለመሆኑን ለመወሰን ማብራሪያ የመፈለግ እና ማንኛውንም ቁሳዊ ያልሆኑ ጉድለቶችን ወይም መደበኛ ያልሆኑ ጉዳዮችን የመቀበል ወይም የመተው መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ አባል ሠራተኞች የከተማ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ እና ሥራ (B&O) ግብር መተግበሩን ለማረጋገጥ እርስዎን ሊያገኝዎት ይችላሉ። በዚህን ጊዜ፣ አመልካቾች ለዕርዳታ ስጦታ ገንዘብ ለመታሰብ ተግባራዊነትን ለማረጋገጥ 48 ሰዓታት ይኖርዎታል። ሠራተኛ አመልካቾችን በ 206 የአከባቢ የስልክ ኮድ ወይም በ @seattle.gov የሚያበቃ ኢሜይል ያገኙአቸው ይሆናል። ንግዶች በ (206) 684-8090 ቢሮአችን በመደወል ወይም በድህረገጻችን የቡድናችንን ማውጫ ገጽ በመጎብኘት የሰራተኞችን ማንነት ማረጋገጥ ይችላሉ።

ከፍተኛውን የኢኮኖሚ ተፅእኖ ያጋጠማቸውን አነስተኛ ንግዶችን ለመደገፍ፣ የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት ከሚከተሉት ከሚገባቸው በታች አገልግሎት የተሰጣቸውን ማኅበረሰቦች ንግዶች ቅድሚያ መሰጠቱን ያረጋግጣል:

  • በጥቁር፣ በነባር ተወላጅ እና ነጭ ባልሆኑ ሰዎች (BIPOC) የተያዙ ትናንሽ ንግዶች።
  • በሴት ባለቤትነት የተያዙ አነስተኛ ንግዶች።
  • በጣም በተጨናነቀ የሕዝብ ቆጠራ የተወሰነ ስፋት ያለው መሬት ውስጥ የሚገኙ ቢያንስ 30% ድህነት ወይም ከ60% መካከለኛ ገቢ ያልበለጠ አነስተኛ ንግዶች።
    • ማሳሰቢያ: እነዚህ አካባቢዎች በፌዴራል አነስተኛ ንግድ አስተዳደር (SBA) “ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ማህበረሰቦች” (LICs) ፍቺን ያሟሉ፣ እና አነስተኛ ንግድ አስተዳደሩ ለ COVID የችግር ማቃለያ ፋይናንስ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ማህበረሰቦች ቅድሚያ ሰጥቷል።

አመልካቾች ሁሉ እስከ ጥር 31 ቀን 2022 ድረስ ያሉበት ሁኔታ ይነገራቸዋል።

8. የተመረጡት ንግዶች የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ብቁ መሆናቸውን እንዴት እናውቃለን?

የንግድ ባለቤቶች ለእርዳታ ገንዘብ ብቁ መሆናቸውን በራስ-ሰር የሚወስኑ ተከታታይ ጥያቄዎችን ያጠናቅቃሉ። በማመልከቻው ውስጥ የቀረቡ የመረጃዎችን ሰነድ ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት ከገንዘብ እና አስተዳደር አገልግሎቶች መምሪያ ጋር ይሠራል።

9. ተሸላሚዎችን የመምረጥ ሂደቱ ፍትሃዊ እና ከአድልዎ ነፃ ነውን?

አዎ። የሲያትል ከተማ የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት በጾታ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በብሔር፣ በጾታ ዝንባሌ፣ በጾታ ማንነት፣ በቤተሰብ ሁኔታ፣ በትውልድ አገር፣ በአካል ጉዳተኝነት ወይም በሌሎች የስነሕዝብ ምድቦች ላይ ተመስርቶ የንግድ አመልካቾችን አይለይም ወይም ብቃት የለሽ አያደርግም።

10. ከተሰጠ በታች የተወከሉ እና እንግሊዝኛ የማይናገሩ የንግድ ባለቤቶች የእርዳታ ገንዘብ ድጋፍ የማግኘት ፍትሐዊ ዕድል እንዳላቸው እንዴት ያረጋግጣሉ?

  • የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት ከኢሚግሬሽን እና ከስደተኞች ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት፣ ከአጎራባች የማህበረሰብ ግንኙነቶች መምሪያ እና ከሌሎች የማኅበረሰብ አጋሮች ጋር በመሆን ለመድረስ አስቸጋሪ ለሆኑ የንግድ ባለቤቶች የማረጋጊያ ፈንድ የመክፈቻ እና የማመልከቻ ጊዜውን ለማሳወቅ የግንኙነት እና የቴክኒክ ድጋፍ ለመስጠት እየሠራ ነው።
  • ፕሮግራሙ ከእንግሊዝኛ ሌላ ቋንቋዎችን ለሚናገሩ ማህበረሰቦች የዚህን የመረጃ ሀብት መዳረሻ ማግኘት እንዲችሉ ለማረጋገጥ አስፈላጊ የማመልከቻ ቁሳቁሶችን ይተረጉማል።
  • የአነስተኛ ንግድ ልማት ቡድን ጥቅምት 21 ቀን ከሰዓት በኋላ በ2 ሰዓት ላይ ለማረጋጊያ ፈንድ እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ምናባዊ የመረጃ ክፍለ ጊዜን ያስተናግዳል። የሁለት ቋንቋ ትርጓሜ እና በጽሑፍ የተተረጎሙ ቁሳቁሶች በአማርኛ፣ በቻይንኛ፣ በኮሪያ፣ በሶማሌ፣ በስፓኒሽ፣ በታይ እና በቬትናምኛ ይኖራሉ።
  • አመልካቾች የኮምፒተር ወይም አስተማማኝ የበይነመረብ መዳረሻ ከሌላቸው የኦንላይን ማመልከቻውን በማስገባት አባል ሠራተኛ እንዲረዱዋቸው የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤትን መድረስ ይችላሉ። ሁሉም የሲያትል የህዝብ ቤተመፃሕፍት ቅርንጫፎች ለኮምፒዩተር እና እንዲሁ ለበይነመረብ መዳረሻ ይገኛሉ።
  • የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ይህንን ብቁ አመልካቾችን ማመልከቻ በማጠናቀቅ ለመደገፍ የቴክኒክ ድጋፍ፣ የቋንቋ ተደራሽነት አገልግሎቶች፣ የአካል ጉዳተኞች የመስተናገጃ ቦታዎችን፣ በተለዋጭ ቅርፀቶች ቁሳቁሶችን እና ስለ ተደራሽነት መረጃ ይሰጣል። ንግዶች በ (206) 684-8090 በመደወል ወይም oed@seattle.gov ኢሜል በማድረግ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

11. ንግዶች ምን ያህል ገንዘብ ይቀበላሉ?

የዕርዳታ ስጦታዎች በ$5,000 ዶላር፣ በ$10,000 ዶላር እና በ$20,000 ዶላር መጠን ይሸለማሉ።

12. የዕርዳታ ስጦታው በምን ላይ ሊውል ይችላል?

የዕርዳታ ስጦታ ገንዘብ ለተሸለሙት ንግዶች የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች ብቻ መጠቀም ይቻላል። የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች እንደ የቤት ኪራይ፣ የሠራተኛ ደመወዞች እና ሌሎች የንግድ የሥራ ማስኬጃዎች ያሉ የንግዱን የዕለት ተዕለት ተግባሮችን ማለት ነው።

13. የንግድ ድርጅቶች የፋይናንስ መረጃን መጋራት ያለባቸው ለምንድን ነው?

የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት የንግዱን ፍላጎት እና የወደፊት የገንዘብ ድጋፍ አስፈላጊነት ለመገምገም፣ አነስተኛ የንግድ ሥራን አሟልቶ መገኘትን እና የንግድ የፋይናንስ ፍላጎት መሟላቱን እና የንግድ ሥራው በCOVID-19 ምክንያት የደረሰበትን የኢኮኖሚ ጉዳት ለማረጋገጥ የንግድ እና ሥራ (B&O) ግብር እና ሌሎች ወርሃዊ የሂሳብ ግምቶችን ይሰበስባል።

14. ማመልከቻዎች እና የፋይናንስ መዝገቦች ለሕዝብ ይፋ ለመሆን የተጋለጡ ናቸው?

በአጠቃላይ፣ የማመልከቻ ይዘቶች/ ቁሳቁሶች ለሕዝብ ይፋ ይሆናሉ። ሆኖም፣ የዋሽንግተን ስቴት ሕግ የአመልካቾችን ግላዊነት ለመጠበቅ የተወሰኑ የግል እና የፋይናንስ መረጃዎችን ከማሳወቅ እንዲከለከል ይፈቅዳል።

15. በማረጋጊያ ፈንድ በመጀመሪያዎቹ አምስት ዙር የገንዘብ ድጋፍ የተሸለመ ንግድ ለዚህ የማረጋጊያ ፈንድ የዕርዳታ ድጋፍ ስጦታ እንደገና ማመልከት ይችላል?

አዎ፣ በማረጋጊያ ፈንድ በመጀመሪያዎቹ አምስት ዙር የዕርዳታ ስጦታዎች የተሸለሙ ንግዶች ለዚህ ዙር ለማመልከት ብቁ ይሆናሉ። ሁሉም ብቁ አመልካቾች፣ ቀደምት ተሸላሚዎች እና ቀደም ሲል ያመለከቱ ንግዶችን ጨምሮ የኦንላይን ማመልከቻ ማስገባት አለባቸው።

16. አንድ ንግድ አሁን ጥሬ ገንዘብ የሚያስፈልገው ከሆነ፣ ተጨማሪ የንዋይ ሀብቶች አሉ?

ከከተማው የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ በተጨማሪ በ COVID-19 ቀውስ ተጽዕኖ ለደረሰባቸው አነስተኛ ንግዶች በርካታ የክልል፣ የፌዴራል እና የበጎ አድራጎት ድጋፍ ምንጮች አሉ። የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለእነዚህ የንዋይ ሀብቶች ለሚያመለክቱ ንግዶች የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤ የበለጠ ለማወቅ የእኛን የመረጃ ምንጭ ገጽ ይጎብኙ።

17. የተንቀሳቃሽ ንግዶች ምሳሌዎች ምንድናቸው?

ለዚህ የእርዳታ ድጋፍ ስጦታ አካላዊ የጡብ እና የሞርታር ሕንፃ ቦታ የማይፈልጉ የተንቀሳቃሽ ንግዶች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፣ ግን በዚህ አይወሰኑም:

  • ገበሬዎች የገበያ አቅራቢዎች።
  • ምግብ አቅራቢዎች።
  • የምግብ ጭነት መኪኖች።
  • የግል አሰልጣኞች።
  • የጽዳት አገልግሎቶች።
  • ቆሻሻ ማስወገድ።
  • የሚንቀሳቀሱ አገልግሎቶች።

እባክዎ አመልካቾች ሁሉ አንድ ወቅታዊ የሲያትል ከተማ የንግድ ፈቃድ ሊኖረው እንደሚገባው ያስታውሱ። የንግድ ፈቃድዎን የአቋም ሁኔታ በ filelocal-wa.gov ላይ ማረጋገጥ ይችላሉ።

18. እንደ የፈጠራ ኢንዱስትሪዎች ንግድ የሚያስመድበው ምንድነው?

ለዚህ የእርዳታ ድጋፍ ስጦታ አካላዊ የጡብ እና የሞርታር ሕንፃ ቦታ የማይፈልጉ የፈጠራ ኢንዱስትሪዎች ንግዶች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፣ ግን በዚህ አይወሰኑም:

  • ፊልም (አስማጭ ቴክኖሎጂን ጨምሮ፣ ብዙሀን ሚዲያ እንደ AR/VR/MR/XR/CGI/እንቅስቃሴ ቀረፃ/መጫወትን/እንስሳዊ ምስል፣ ስርጭት፣ ኤግዚቢሽን፣ ወዘተ)።
  • ሙዚቃ (ሙዚቀኞችን፣ የሙዚቃ መድረኮችን፣ የመቅጃ ስቱዲዮዎችን፣ የድምፅ ቴክኒሻኖችን፣ የኪነጥበብ አስተዳደርን፣ የመዝገብ ስያሜዎችን፣ የቦታ ማስያዝን፣ ወዘተ) ጨምሮ።
  • ልዩ ክስተቶች።
  • ስነ ፎቶግራፍ።
  • የፈጠራ ወኪሎች (ማስታወቂያ፣ ግራፊክ ዲዛይን፣ የይዘት ፈጠራ፣ ወዘተ)።
  • ፋሽን፣ ልብስ እና ጨርቃ ጨርቅ።
  • ሥነ ጽሑፍ (ማተም፣ ጋዜጠኝነት፣ ጽሑፍ፣ የቅጂ አርትዖት፣ ወዘተ)።

19. የፈጠራ ኢንዱስትሪዎች ንግዶች ግለሰብ አርቲስቶችን ያካትታሉ?

ግለሰብ አርቲስቶች የፈጠራ ኢንዱስትሪዎች ንግዶች ናቸው እና ለማረጋጊያ ፈንድ ብቁ ናቸው።

20. የቤተሰብ አባላት በንግድ ሥራዬ ቢሠሩ፣ እንደ የሙሉ ጊዜ አቻ ሠራተኛ (FTE) ላካትታቸው እችላለሁ?

የቤተሰብ አባላት በደመወዝ ክፍያ ላይ ከሆኑ ታዲያ እንደ የሙሉ ጊዜ አቻ ሠራተኞች አድርገው ያካትቷቸዋል።

21. ሥራዬ መጋቢት 1 ቀን 2020 ከ 50 በላይ የሙሉ ጊዜ አቻ ሠራተኞች (FTE) ቢኖሩትስ፣ ነገር ግን በወረርሽኙ ምክንያት ሠራተኞቼን መቀነስ ከነበረብኝሳ? የእኔ ንግድ ብቁ ነው?

መጋቢት 1 ቀን 2020 ከ 50 በላይ የሙሉ ጊዜ አቻ ሠራተኞች የነበሯቸው ንግዶች ብቁ አይሆኑም። ንግድዎ እስከ 50 የሙሉ ጊዜ አቻ ሠራተኞች ሊኖሩት ይገባል።

22. በንግድ ሥራ ውስጥ ቢያንስ ለ24 ወራት እንዲኖረኝ ከተፈለገብኝ የሥራ ማስኬዱን የተቆረጠ መጀመር ያለብኝ ቀን አለ?

ከቅምት 19 ቀን 2019 በፊት መስራት የጀመሩ ንግዶች የ 24 ወር ዝቅተኛውን ያሟላሉ።

23. የእኔ ንግድ በአሁኑ ጊዜ በኮቪድ ምክንያት ተዘግቷል፣ ለማመልከት ብቁ ነኝ?

በኮቪድ ምክንያት መዝጋት የነበረባቸው ንግዶች አሁንም ሌሎች መስፈርቶችን ካሟሉ እና የሚሠራ የሲያትል የንግድ ፈቃድ ካላቸው ለማመልከት ብቁ ናቸው። ንግዱ በቋሚነት ከተዘጋ፣ ለማረጋጊያ ፈንድ ለማመልከት ብቁ አይደሉም።

24. እንደ ኡበር ወይም ሊፍት ያለ መኪና የምጋራ ሾፌር ከሆንኩ፣ ብቁ ነኝ?

መኪና የሚጋሩ አሽከርካሪዎች ብቁ አይደሉም።

25. የቀን መዋዕለ ሕጻናት ብቁ ናቸው?

አዎ፣ የቀን እንክብካቤዎች/ መዋዕለ ሕጻናት ብቁ ናቸው።

26. ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ብቁ ናቸው?

አንዳንድ ለትርፍ ያልተቋቋሙ አካላት ብቁ ናቸው። ለትርፍ ያልተቋቋሙ ብቁ የሆኑ የሚተውኑ ጥበባትን፣ ባህላዊ ተቋማትን እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ የንግድ ቴክኒካዊ ድጋፍ ድርጅቶችን ያካትታሉ።

27. ሰራተኞቼ አሁን በስልክ እየሰሩ ከሆነ፣ ያ እንደ ተጨማሪ የሥራ ቦታ ይቆጠራል?

አይ፣ በርቀት የሚሰሩ ሠራተኞች ለተጨማሪ ሥፍራ አስተዋፅኦ አያደርጉም።

28. የአንደኛ ደረጃ ምድቦች አከፋፈል ምንድነው?

  • ግብርና ወይም የተፈጥሮ ሀብቶች (የደን ልማት፣ እርሻ ማረስ፣ ማዕድን፣ ዓሳ ማጥመድ)
  • የንግድ አገልግሎቶች (ሕጋዊ፣ የሂሳብ ሥራ፣ ግብይት፣ ለንግዶች ማማከር)
  • የሕፃናት እንክብካቤ ወይም መዋዕለ ሕጻናት
  • የግንባታ ወይም ከባድ የጣቢያ ሥራ (ሥራ ተቋራጮች፣ ከባድ ሲቪል፣ መኖሪያ)
  • የፈጠራ ኢንዱስትሪዎች (ፊልም፣ የምሽት ሕይወት፣ ልዩ ዝግጅቶች፣ የፎቶግራፍ ኪነት፣ ማስታወቂያ፣ የአቀራረጽ ንድፍ፣ የይዘት ፈጠራ፣ ፋሽን፣ ልብስ እና ጨርቃ ጨርቅ፣ ሥነ ጽሑፍ፣ ህትመት፣ ጋዜጠኝነት፣ የቅጂ ማስተካከያ)
  • የትምህርት አገልግሎቶች (ስልጠና፣ የርቀት ትምህርት)
  • ፋይናንስ፣ ኢንሹራንስ ወይም የርስት/ ቤቶች ሀብት (ባንኮች፣ የኢንቨስትመንት ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ደላሎች፣ የርስት/ ቤቶች ሀብት ደላሎች)
  • የጤና እንክብካቤ (የሕክምና ቢሮዎች፣ ክሊኒኮች፣ የአዛውንቶች ማስታመሚያ ቤቶች፣ የእሽት ቴራፒስቶች፣ የጥርስ ሐኪሞች)
  • መስተንግዶ (ሆቴሎች)
  • የምግብ አገልግሎቶች: ምግብ ቤቶች
  • የምግብ አገልግሎቶች: መጠጥ ቤቶች ወይም የመጠጥ ቤቶች
  • የሕይወት ሳይንስ ወይም የስነ ሕይወት ተክኖሎጂ (biotech) (ምርምር እና ልማት፣ የመድኃኒት አምራቾች፣ የህክምና መሣሪያዎች)
  • ማምረት፡ ኤሮስፔስ (የበረራ አቅራቢዎች)
  • ማምረት፡ የምግብ እና የመጠጥ ምርት (የምግብ አምራቾች፣ የባህር ምግብ ማቀነባበሪያዎች፣ ቢራ ፋብሪካዎች፣ የወይን ጠጅ አምራቾች፣ የመጠት ማጣሪያዎች)
  • ማምረት፡ የባህር/ የመርከብ (የመርከብ እና የጀልባ ግንባታ እና ጥገና)
  • ማምረት፡ ሌላ
  • የግል አገልግሎቶች (የውበት፣ የአካል ብቃት፣ የሕፃናት እንክብካቤ፣ ደረቅ ጽዳት፣ የግል ወይም የሸማች አገልግሎቶች)
  • የጽሑፍ ማተሚያ ወይም ሌላ መረጃ (ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ መጽሐፍ ማተም፣ የተንቀሳቃሽ ፊልም ምርት)
  • ሙያዊ ወይም ቴክኒካዊ አገልግሎቶች (የስነ ሕንፃ ድርጅቶች፣ የምህንድስና ኩባንያዎች)
  • የችርቻሮ ንግድ፡ መደብር
  • ችርቻሮ ንግድ፡ መደብር ያልሆነ ወይም ኢ-ኮሜርስ (የኦንላይን ንግድ)
  • ማህበራዊ አገልግሎቶች (የተቋማት የምግብ አገልግሎቶች፣ መኖሪያ ቤት፣ የድንገተኛ ጊዜ አገልግሎቶች፣ የማህበራዊ ሥራ)
  • ሶፍትዌር (የኮምፒዩተር ፕሮግራም፣ በደመና ላይ የተመሰረቱ (cloud-based) ምርቶች እና አገልግሎቶች፣ ወይም ቴሌኮሙኒኬሽኖች (ሶፍትዌር፣ ኮምፒዩተይ ክላውድ (cloud) ማስላት፣ የበይነመረብ አቅራቢዎች፣ የቴሌኮም አቅራቢዎች)
  • መጓጓዣ ወይም የማከማቸት ሥራ (የጭነት መጓጓዣ፣ የባቡር ሐዲድ፣ የጭነት ማስተላለፍ፣ አየር መንገዶች፣ ማከማቻዎች፣ የመሬት ማጓጓዣ፣ መልእክት አመላላሾች)
  • መጓጓዣ: በውሃ ላይ (መርከቦች፣ በውሃ ላይ የተመሠረቱ ጉብኝቶች፣ ጭነት)
  • የቆሻሻ አገልግሎቶች (የቆሻሻ ሥራ ማካሄድ)
  • የጅምላ ሻጮች፣ የጅምላ ነጋዴዎች

29. የእኔ ንግድ በመጋቢት 2020 እና በህዳር 2020 አመልክቷል፤ ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ለስድስተኛው ዙር እንደገና ማመልከት አለብኝ? 

በመጋቢት እና በህዳር 2020 ያመለከቱ የንግድ ድርጅቶች ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ስድስተኛው ዙር እንደገና ማመልከት ይኖርባቸዋል። ብቁ አመልካቾች ሁሉ የኦንላይን ማመልከቻ ማስገባት አለባቸው።

30. ንግዴን ከላይኛው የፍለጋ አሞሌ ውስጥ ባላገኝስ? 

በላይኛው የፍለጋ አሞሌ ውስጥ ንግድዎን ማግኘት ካልቻሉ በንግድ ስምዎ፣ በአድራሻዎ፣ ወጥ የሆነ የንግድ መለያ መታወቂያ (UBI) ቁጥር ወይም በከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር ገጹን እንደገና ማደስ እና ንግድዎን ለመፈለግ ይሞክሩ። 

ማሳሰቢያ: የከተማው የንግድ ፈቃድ ቁጥር (የከተማው የደንበኛ ቁጥር) ገጹ ከታደሰ ወይም የስህተት መልእክት ከደረሰዎት በኋላ ካልታየ ንግድዎ ያለማሟላት ዕድል አለው። ለመረጃ እባክዎን አስፈላጊ የሰነድ ክፍልን ያጣቅሱ፣ የከተማዎን የንግድ ፈቃድ ቁጥር ለመፈለግ የንግድ ሥራ ፍለጋ መሣሪያን ይጎብኙ እና የንግድዎን የግብር አቋም ሁኔታ ለመፈተሽ ወዲያውኑ tax@seattle.gov ኢሜይል ያድርጉ።    

በላይኛው የፍለጋ አሞሌ ውስጥ ንግድዎን ማግኘት ካልቻሉ አሁንም ለእርዳታ የድጋፍ ስጦታው ማመልከት ይችላሉ፤ እባክዎን ንግድዎን እና የእውቂያ መረጃዎን በማመልከቻው መግቢያ ውስጥ በእጅ ያስገቡ።

31. የእኔ ንግድ የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ተቀበለ። የ1099 ቅጼን እንዴት እቀበላለሁ? 

የሲያትል ከተማ ፋይናንስ እና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች በጥር ወር መጨረሻ በ W-9 ላይ ለተዘረዘሩት አድራሻዎች 1099 ቅጾችን በፖስታ ልኳል። ይህ የሲ(C)-ኮርፖሬሽኖችን፣ ኤስ(S)-ኮርፖሬሽኖችን ወይም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን አያካትትም። የ1099 ቅጾቻቸውን ያልተቀበሉ ወይም በተሳሳተ ቦታ ያደረጉ ንግዶች፣ ለኢሜይል ቅጂ ኪም ሮበርትስ (Kim Roberts)ን በ Kim.Roberts@seattle.gov ያግኙዋት። 

32. የክትባት ማረጋገጫ የአቋም መምሪያን በማስተግበር ተጨማሪ የተሰባሰበ ገንዘብ ለመቀበል ብቁ የሆነ ማነው? 

ከጥቅምት 25 ጀምሮ፣ ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በኪንግ ካውንቲ ውስጥ የተወሰኑ የቤት ውስጥ እና የውጭ ዝግጅቶችን እና ተቋማትን ለመግባት ሙሉ የ COVID-19 ክትባት ማረጋገጫ ወይም አሉታዊ የሙከራ ውጤት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። ተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖዎችን ለማካካስ እንዲያግዝ ይህ ደንብ ለማስፈፀም ለአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ ማመልከት በሚፈለጉ ንግዶች እና ድርጅቶች ይህንን ደንብ መተግበር፣ እና በሚከተሉት ዘርፎች ውስጥ ያሉ ትናንሽ ንግዶች እና ድርጅቶች እስከ $1,000 ዶላር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ብቁ ይሆናሉ።

ለዚህ ተጨማሪ ገንዘብ ዘርፎች ምግብ ቤቶችን፣ የተውነት ጥበቦች እና የባህል ተቋማትን፣ የምሽት ህይወት ቦታዎችን እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ/የቤት ውስጥ እንቅስቃሴ መዝናኛ ቦታዎችን (እንደ የቦውሊንግ ማንከባለልያ፣ ጂም፣ የጨዋታ መገልገያዎች፣ ወዘተ) ያካትታሉ።

የንግድ ድርጅቶች የተለየ ማመልከቻ ማስገባት አይጠበቅባቸውም።  

ጥያቄዎች?

የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ይህንን ብቁ አመልካቾችን ማመልከቻ በማጠናቀቅ ለመደገፍ የቴክኒክ ድጋፍ፣ የቋንቋ ተደራሽነት አገልግሎቶች፣ የአካል ጉዳተኞች የመስተናገጃ ቦታዎችን፣ በተለዋጭ ቅርፀቶች ቁሳቁሶችን እና ስለ ተደራሽነት መረጃ ይሰጣል። ንግዶች (206) 684-8090 በመደወል ወይም oed@seattle.gov ኢሜይል በማድረግ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

Economic Development

Markham McIntyre, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 5752, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 94708, Seattle, WA, 98124-4708
Phone: (206) 684-8090
Phone Alt: (206) 684-0379
Fax: (206) 684-0379
oed@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Economic Development

The mission of the Office of Economic Development (OED) is to help create healthy businesses, thriving neighborhoods, and community organizations to contribute to a robust economy that will benefit all Seattle residents and future generations.