ኣነስተኛ የንግድ ድርጅት ማረጋግያ

በኮቪድ-19 (Genzeb) ተጽዕኖ ለደረሰባቸው የ 2020 ነስተኛ የንግድ ድርጅት ማረጋግያ ፈንድ

የስያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት (OED) በኣነስተኛ የንግድ ድርጅት ማረጋግያ ፈንድ ኣማካኝነት ኣነስተኛ የንግድ ድርጅቶችን  ለማረጋጋት ተጨማሪ 4 ሚልዮን ዶላር ኢንቨስት እያደረገ ነው። የኣነስተኛ የንግድ ድርጅት ማረጋግያ ፈንድ (SBSF) በኮቪድ-19 ተጽዕኖ ለደረሰባቸው በስያትል ከተማ ለሚገኙ ኣነስተኛ የንግድ ድርጅቶችና በጎ ኣድራጊ ተቋማት የ10,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ያቀርባል። እርዳታው በከፍተኛ የመፈናቀል ኣደጋ ላሉ ወይም ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው፣ በጣም ኣነስተኛ የንግድ ድርጅቶች፣ በፈጠራ ዘርፍ የተሰማሩ፣ እንዲሁም ከፍተኛ ኢኮኖምያዊ ተጽዕኖ የደረሰባቸው የንግድ ድርጅቶችን ቅድሚያ ይሰጣል።

ፈንዱ በተጨማሪ ቅድሚያ የሚሰጠዉ ደወመዝ ላለመቀነስና ከኮቪድ-19 ክስተት በፊት ለሰራተኞች ይሰጥዋቸው የነበሩ ጥቅማጥቅሞች ላለማቋረጥ ቁርጠኝነተ ላላቸዉ የንግድና በጎ ኣድራጊ ድርጅቶች ነዉ። የስያትል የኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ቢያንስ የእርዳታው ሁለት ሶስተኛ በሎተሪ መልክ አምስት ወይም ከዛ በታች ቅጥር ሰራተኛ ላላቸውና በ ከተማዉ የዘርና ማህበረዊ እኩልነት መጠቆሚያ (City’s Race and Social Equity Index) መሠረት የመፈናቀል ከፍተኛ ስጋት ያላቸው ወይንም በከፍተኛ የተጎዱ ተብለዉ የተለዩ  ቦታዎች ለሚገኙ ድርጅቶች የሚሰጥ መሆኑን ያረጋግጣል።

ብቁነት

 • የንግድ ድርጅቱ በስያትል ከተማ ክልል ውስጥ ይገኛል። (በኪንግ ካዉንቲ ከተማዎች ወሰን (unincorporated) ዉጪ ባሉ ቦታዎች ያሉ ንግድ ድርጅቶች ለ SBSF ብቁ አይደሉም)
 • እስከ ማርች 2020 ባለዉ ግዜ 25 የሙሉ ግዜ ሠራተኞች (“FTEs”) ወይንም ያነሰ ያለቸዉ
 • $2 ሚሊዮን ወይ ከዛ በታች ዓመታዊ ገቢ ያላቸው
 • ብቁ (Valid) የስያትል ከተማ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
 • የንግድ ድርጅቱ ከሁለት የበለጠ የስራ ቦታ የሌለዉ
 • ቢያንስ ለ12 ወራት በንግድ ስራ የተሰማራ
 • ከዚህ ቀደም የኣነስተኛ ንግድ ማረጋግያ ፈንድ ያልተቀበለ
 • ለትርፍ የሚሠረ ድርጅት (501c3 or ሌለ 501 ለትርፍ የማይሠራ ድርጅት ያልሆነ)
 • ድርጅቱ ንግድ የሚያካሂድበት ቋሚ አድራሻ ያለው (ለፈጠራ ኢንዱስትሪዎች ወይም ተንቀሳቃሽ የምግብ መኪና ካልሆነ በስተቀር)
 • በ Seattle Municipal Code 6.270 መሠረት እንደ “አዋቂዎች መዝናኛ” ድርጅትነት ቁጥጥር ከሚደረግባቸዉ በቀር ደንበኞቻቸዉ 18 ዓመትና ከዚያ በላይ እንድሆኑ የገደቡ ንግድ ድርጅቶች ብቁ ናቸዉ።

የአነስተኛ ንግድ ድርጅቶች ማረጋግያ ገንዘብ ማመልከቻ ኖቬምበር 9 ጀምሮ እስከ ኖቬምበር 30 2020 ድረስ ክፍት ይሆናል።

ስለ ኣነስተኛ የንግድ ድርጅት የማረጋግያ ፈንድ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች፡

እርዳታ እና ትርጓሜ

ማመልከቻው ለመሙላት እገዛ ካስፈለግዎት እባክዎን ወደ oed@seattle.gov ኢመይል ይላኩ ወይም የኢኮኖምያዊ ልማት ጽ/ቤት (206) 684-8090 ጋ በመደወል የሚቀጥሉትን መረጃ ያሉበት መልእክት ይተዉ።

 • ስምዎ
 • ስልክ ቁጥር
 • የሚፈልጉትን ቋንቋ በእንግልዝኛ
 • ምን ዓይነት እገዛ እየፈለጉ እንደሆን

በተቻለ መጠን ኣማርኛ የሚናገር ሰው ቶሎ ብሎ ይደውልልዎታል።

መረጃ የሚሰጡባቸው የወቢናር ቀናት

የኢኮኖምያዊ ልማት ጽ/ቤት (OED) እንዴት በተሳካ መልኩ ለ SBSF ማመልከት እንደሚችሉ መረጃ የሚሰጥት ሶስት ስብሰባ ያስተናግዳል።

 • ኖቬምበር  12 2020 12pm-1pm 
 • ኖቬምበር  18 2020 12pm-1pm 

እዚህ ይመዝገቡ፥ https://register.gotowebinar.com/rt/3529591065459961359

እስከ ዛሬ ኣነስተኛ የንግድ ድርጅት የማረጋጋት ፈንድ ተጠቅመው እርዳታ ያገኙ ኣነስተኛ የንግድ ድርጅቶች 469 የማረጋግያ ፈንዱ በወጣበት በመጋቢት 2020 የኢኮኖምያዊ ልማት ጽ/ቤት (OED) ከ 9000 በላይ ማመልከቻዎች ተቀብለዋል። የእርዳታ ፍላጎቱ ከቀረበው ዓቅም በላይ ስለነበረ የማመልከት ሂደቱ መልሶ ኣልተከፈተም። በሚቀጥሉት ዙሮች እርዳታ ያገኙ ድርጅቶች ኣስቀድሞ ከተቀበልናቸው ማመልከቻ ብቁ ናቸው ከተባሉት በዕጣ ነበር።

የማረጋግያ ፈንድ የተቀበሉት ሙሉ ዝርዝር እዚህ ማየት ይቻላል

የማረጋግያ ፈንድ የተቀበሉት ሙሉ ዳታ ዳሽ ቦርድ